ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ላሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ ማራቶን የብር ሜዳሊያ አገኘ – እጁን ወደላይ በማጣመር ለትግሉ ያለውን አጋርነት አሳየ


 

lalisa-1

(ዘ-ሐበሻ) በሪዮ ኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አገኘች:: ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ላሊሳ በኬኒያዊው አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጌ ተቀድሞ 2ኛ ቢገባም ውድድሩን በሚያጠናቅቅበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለፈው 10 ወራት ካለማቋረጥ እየተጠቀመበት ያለውን እጅን ወደላይ ማጣመር በማሳየት ለትግሉ ያለውን አጋርነት አሳይቷል::

በዚህ የማራቶን ውድድር አሜሪካዊው ግሌን ሩፕ 3ኛ ሲወጣ ኤርትራዊው አትሌት ግርማይ ገብረስላሴ 4ኛ ሆኖ አጠናቋል::

ኬንያዊው አትሌት ውድድሩን ለመጨረስ 2:08:44 ሲፈጅበት ኢትዮጵያዊው ፈይሳ 2:09:54 ገብቷል:: 3ኛ የወጣው አሜሪካዊው ግሌን 2:10:05 በመግባት 3ኛ ሆኗል::

ፈይሳ ዛሬ በብዙ ሚሊዮኖች በተከታተሉት የኦሎምፒኩ ሜዳ ላይ እጁን ወደላይ አጣምሮ መንግስትን መቃወሙና ከሕዝብ ጎን አጋርነቱን ማሳየቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በሕዝቦች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያና የሰብ አዊ መብት ጥሰት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት እንዲያደርጉበት የራሱን ጫና ያሳድራል::

lalisa

 

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s