ሰበር ዜና : አሁን ላይ ቡሬ በተኩስ እየተናጠች ነዉ


# ሰበር ዜና # አሁን ላይ ቡሬ በተኩስ እየተናጠች ነዉ፤ቁጥራቸዉን በዉል ባናዉቅም የሞቱ ሰዎችም አሉ።ጎበዝ የገረመኝ እና በህይወቴ ያዘንኩበት ያለቀስኩበት ቀን ቢኖርልጆቻቸዉ የሞቱባቸዉን እናቶች የሲቃ ለቅሶ የሰማሁባትን በዛሬዋን መሪር ቀን ነዉ።እናቶች በልጆቻቸዉ ሞት እኛንም ጨምሩን እያሉ መርት ወድቀዉ ሲያለቅሱ ሳያቸዉ ጎበዝ ብታምኑም ባታምኑም እንባ አዉጥቼ እልቅሻለሁ። ለቅሶዬ ሰዉ ሆኜ ስለተፈጠርኩ እንጂ ለቅሶ በራሱ በነፃነት የምንተነፍስበት አየር ይሰጠናል ብዬ አይደለም። ከህዝብ በተፈጠሩ በአርያ ስላሴ ሰዉ ሆነዉ ነገር ሰዉ በላ በሆኑ አጋዚዎች ለምን ይሄን ያክል ጭካኔ? ለምን ይሄን ያክል ጥፋት? ብዬ ጥያቄ ዉስጥ ገብቼ አመረርኩ። በአመርም ባለቅስም ለዛሬ መልስ የለዉም። ምን አልባት ጊዜና መስዋእት የሚፈታዉ ጉዳይ ይሆናል።በነገራችን ላይ ዛሬ በቡሬ ላይ ሞት ብቻ አይደለም የተስተናገደዉ ብዙዎችም ተደብድበዉ ቆስለዋል። ከተማዋ በሰዉ በላ አጋዚዎችና መከላከያ ወታደሮች ተጥለቅልቃለች። ሚካኤል አካባቢ ያለዉን ህዝብ ለመበተን እየጣሩ ነዉ ህዝቡ ግን አሁንም ተቃዉሞዉን አጠናክረን ቀጥለናል። ከወዲህ ከወዲያም የተኩስ ድምፅ እያስተጋባ ይገኛል። በእኛ ላይም አስለቃሽ ጋዝና የባሩድ ጭስ አልብሶናል። ጎበዝ እንያ በልጆቻቸዉ ሞት የሚያለቅሱ እናቶች ድምፅ ጆሮዬ ዉስጥ ገብቶ ግን ለምን እያልኩኝ አሁንም እያስለቀሰኝ ነዉ። ልጆቻቸዉም ለአንዴ ላይመለሱ አሽልበዋል።voice Of Amhara!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s