Archive | November 2016

በሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ጦርነት ሲካሄድ ዋለ

ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ታች አርማጭሆ  ሳንጃ እና በጠገዴ ወረዳ ግጨው እንዲሁም ልዩ ስሙ ሃመረ በተባለ ቦታ ላይ የነጻነት ሃይሎች እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ሲካሄድ በዋለው ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህወሃት /ኢህአዴግ ወታደሮች መገደላቸው ታውቛል።

ከሁመራ ወደ ቀራቀር በሚወሰደው መንገድ ላይ ቁስቋም ማሪያም አካባቢ በሚገኝ ዳገት ላይ፣ በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አባል በነበረውና ሊያዝ ሲል በማምለጥ ጫካ በገባው ጎቤ መልኬ በሚመራው የነጻነት ሃይሎች ጦርና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል በተደረገው ከፍተኛ ውጊያ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።

ከነጻነት ሃይሎች በኩል ከጎንደር እስር ቤት ሰብሮ በመውጣት ታጋዮችን የተቀላቀለውና በተዋጊነቱ ተደናቂ የነበረው ሞላ አጃው የተሰዋ ሲሆን፣ 2 ሌሎችን ጓደኞችም መሰዋታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች በድንገት በተከፈተባቸው ውጊያው በመደናገጥ ገደል ገብተው  ማለቃቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በግጨው አካባቢ በአርበኞች ግንቦት7 እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል ሲካሄድ በዋለው ጦርነት ደግሞ  በርካታ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች አልቀዋል። ከሳምንት በፊት ወደ አካባቢው  የመጡ ወታደሮች ውጊያውን መቋቋም ስላቃታቸው ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ  ከጎንደር በ14 ኦራል መኪኖች የተጫኑ ወታደሮች ትክል ድንጋይን አልፈው ወደ  ሳንጃ እየተጠጉ ነው ፡፡

ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮችን እያገዘ ሲሆን  ፣ የቆሰሉ አርበኞችን በማንሳት እና በመርዳት ድጋፍ እየሰጠ ነው ፡፡ በቋራ ገለጎ እና ክልል 6 በተደረገው ወጊያም አገዛዙ ከፍተኛ ወታደራዊ  ኪሳራ ደርሶበታል ። የተገደሉት ወታደሮች  በ3 ትራክተሮች ተጭነው ቋራ ላይ ተቀብረዋል። አብዛኛው የሰሜን ጎንደር ከተሞች በሰሜን በሰሜን በኩል አማባ ጊዮርጊስ ፡ ገደብየ ፤ ዳባት ፤ደባርቅ ድረስ በምእራብ ሳንጃ ፤ አሸሬ ፤

ሰሮቃ ፤ ጠገዴ ፤ ማእራብ አርማጭሆ እንዲሁም በደቡብ በኩል አለፋ ፣ ሻውራ ፣ ደልጊ  እና ቋራ  በመሳሰሉት አካባቢዎች ላይ ውጥረቶች ያሉ በመሆኑ ሕ/ተሰቡ በነቂስ በመውጣት እነዚህን የነፃነት ታጋዮችን በማገዝ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ከነፃነት ታጋዮች እና ከአርበኞች ግንቦት 7 ለፍትህና ለነፃነት ንቅናቄ  ጥሪ ቀርቧል።

ገዢው ፓርቲ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ስለሚካሄደው ጦርነት ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ የሰጠው መግለጫ የለም።

አዲስ አበባና አዳማን ጨምሮ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤት ሰብሮ ማሰርና መሰወር ተባብሶ ቀጥሏል

Photo File

(ቢቢኤን) በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ እጅግ እየተባባሰ መምጣቱን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰበብ የሚደረገው የእስር እና የአፈና ዘመቻ መበርታቱን የጠቆሙት መረጃዎች፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በአዳማ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ሰዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ እንደ መረጃዎች ገለጻ ከሆነ፣ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተሰማሩት የአስቸኳይ ጊዜ አስፈጻሚ ወታደሮች የሚፈጸመው ግፍ እጅግ ጨምሯል፡፡
ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤት ሰብሮ መግባት፣ ሰዎችን አፍሶ መውሰድ፣ ወስዶም ወዳልታወቁ ስፍራዎች መሰወር የሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ከሆነ የሰነባበተ ሲሆን፣ በርካቶችም እንደ ቀልድ ወጥው የሚቀሩበት ሁኔታ በብዛት እየተፈጠረ ነው፡፡ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በተለይም ሰሜን ጎንደር አካባቢ ባሉ የገጠር ቀበሌዎች ያለውን አለመረጋጋት የተመለከቱ እማኞች፣ መንግስት እንደሚለው ሀገሪቱ ወደቀድሞ ሰላሟ እየተመለሰች እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት-እማኞቹ፡፡ እንደዚሁም በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች የተሰማሩ ወታደሮች ሰላማዊ ዜጎችን እያሸበሩ ነው ተብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ ለሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቦች መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ ሀገሪቱ እየተረጋጋች ስለመጣች አዋጁ ሊነሳ ይችላል ሲሉ ገልጸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ አጋጣሚ ሀገሪቱ መረጋጋቷን ይግለጹ እንጂ፣ ነባራዊው ሁኔታ ግን ፈጽሞ ከሚሉት ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን ጨምሮ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች፣ ከመረጋጋት ይልቅ የተባባሰ ሁኔታ እንደሚታይባቸው ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት፡

Ethiopia: Zone9 Blogger Befeqadu Hailu Re-Arrested

Ethiopian Security Re-Arrest Rights Activist, Zone9 Blogger Befeqadu Hailu

Addis Standard (Addis Ababa) — Security member of the command post established to oversee Ethiopia’s six-month State of Emergency have this morning re-arrested human rights activist and blogger Befeqadu Hailu, Addis Standard confirmed.Zone9 Blogger Befeqadu Hailu Re-Arrested

According to information, two security officers who have identified themselves as members of the command post have taken Befeqadu around 6:00 AM this morning. He is now detained at a police station known as 06 here in the capital Addis Abeba.

Befeqadu is a member of Zone9 blogging collective and was one of seven bloggers (one in absentia) and three independent journalists arrested in April. Three months after their arrest all ten of them were charged with Ethiopia’s infamous Anti-Terrorism Proclamation.

After a year and a half trail which was largely marked by several inconsistencies and prosecutor’s inability to provide concrete evidence, a federal court has cleared all of them in July 2015. However, upon appeals from the prosecutor Befeqadu and four of his co-defendants (Natnail Feleke, Atnaf Birhane, Abel Wabella & Soliyana Shimelis, the later in absentia) were re-appearing at the Federal Supreme Court. The hearing was adjourned for the fifth time until Tuesday Nov. 15.

Befeqadu was also facing another criminal charge for allegedly “inciting violence” to which he was released on bail. It is not clear if his re-arrest has anything to do with both cases.

Since Ethiopia declared a six-month state of emergency detentions of opposition party members, journalists and rights activists have increased significantly. Thousands of ordinary Ethiopians are also currently held in dire circumstances inside several detention camps throughout the country.

– See more at: http://ecadforum.com/2016/11/11/ethiopia-zone9-blogger-befeqadu-hailu-re-arrested/#sthash.Cna1Ylbb.dpuf

ሠአት እላፊ ከየት ወዴት?

ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
(በእውቀቱ ሥዩም፤ የመ.ሳ.ቁ =የመልክት ሣጥን ቁጥር፤ 26119 ኮድ 1000)

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ በውቀቱ ሥዩም ወደ ፌስቡክ ተመልሷል፡፡ በነገራችን ላይ“ የቁርጥ ቀን ልጅ” ማለት ቁርጥ በሚበላበት ቀን የተወለደ ልጅ ማለት ነው፡፡ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡
ሰሞኑን በምትገምቱት ነገር ምክንያት ስለፖለቲካ ላልጽፍ ወስኛለሁ፡፡ ቀን እስኪያልፍ ስለ ወሲብ እየተማማርን እንቆይ፡፡
ለወንዶች፤
ከሴት ጋር ወሲብ ሲያደርጉ በፍጥነት ይጨርሳሉ ?ገንዘብዎትን ማለቴ ነው፡፡ መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ በደመወዝ ማግስት በችቺኒያ በኩል አይንዱ፡፡
ግን የምር፤ ከፍቅረኛዎት ጋር ወሲብ ሲያደርጉ ለረጅም ጊዜ መቆየት ይፈልጋሉ? መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ ሲወስቡ፤ ሌላ ነገር ያስቡ፡፡ ለምሳሌ ስለ ጸረ-ሽብር ሕጉ ያስቡ፡፡ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስቡ፡፡ ይህንን ካደረጉ በፍጥነት የሚረጩት እንባዎትን ብቻ ነው፡፡ ለፍተሻ ምኝታቤትዎ የሚገባው ፖሊስ “ለዛሬው ይበቃል “ብሎ ማጅራትዎትን ጨምድዶ እስኪያላቅቅዎ ድረስ ከፍቅረኛዎት ገላ ላይ አይወርዱም፡፡

መንግሥትን “ እኛ ወደ ቤተመንግሥትህ ድርሽ እንደማንል ሁሉ አንተም ወደ ቤታችንና ወደ መስርያ ቤታችን ድርሽ አትበል! በቃ leave us alone ” ስንለው” ዲሞክራሲ ባንድ ጀንበር አልተገነባም “ ብሎ ይገግምብናል ፡፡ እንደ እግዜር አቆጣጠር አንድ ሺህ ዘመን አንድ ቀን ነው፡፡ እንደ መንግስት አቆጣጠር ሃያ አምስት አመት አንድ ጀንበር ነው፡፡ ሳይታገል የሚያታግለን ፓርቲ በበኩሉ ተነሡ ሲለን ስንነሣለት፤ ተደብደቡ ሲል የቆመጥ በረከት ስንቀበልለት ኖረን “ድሉ የታለ?” ስንለው“ ትንሽ አሥር ዓመት ታገሡ፤ ትግሉ ረጅምና መራራ ነው “ይለናል፡፡ መልካም ነገሮች ለመምጣት ረጅም ጊዜ የሚፈጂባቸውን ያክል ፤ክፉ ነገሮች ከቀጠሮው ሰአት ቀድመው የሚጠብቁን ለምን ይሆን?

ስኬት ድልና ጤና
ዳምጠው እንደሚባለው መኪና
ፈጥነው መቸም አይደርሱ
እድሜና ትግስት ሳያስጨርሱ
ችግር ደዌና አፈና ፤ የክፉ ሰውም ኢላማ
ፍጥነታቸው የብርሀን፤ ባሕርያቸው የጨለማ ፡፡

” አንገብጋቢ ችግር -አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት- አስቸኳይ ጊዜ አዋጂ- ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ደባሪ ነገሮች በሙሉ “ፈጣን”ናቸው፡፡ በፍጥነት መጥተው ደሞ በፍጥነት አይመርሹም ፡፡ ድንኳን ተሸክመው መጥተው ከተማቸውን በላያችን ላይ ሠርተውብን ይቀራሉ፡፡

በነገራችን ላይ ፤ የሽግግር መንግሥቱ ላልተወሰነ ጊዜ ተሸጋገረ የሚባለው ነገር እውነት ነው?በጣም የሚገርመው ነገር፤ በውጭ አገር የሚኖሩ ጮሌዎች የሽግግር መንግሥት ቻርተር ሲያረቁ ይውላሉ፡፡ አገር ቤት የሚኖረው ጮሌ ደግሞ ወደ ፈረንጅ አገር የሚሸጋገርበትን መንገድ ሲያረቅ ይውላል፡፡ እንዴው ምን ይሻላል?
ባለፈው ቅዳሜ በእኩለቀን ላይ አንዱ እዚህ እኛ ሠፈር ፤ ቤቱ ውስጥ ሆኖ፤
“አትነሣም ወይ ?!
አትነሣም ወይ
አትነሣም ወይ ?”
እያለ ቀወጠው፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ አካባቢውን የፖሊስ ብረት ለበስ መኪና ወረረው፡፡ አንድ አየር ወለድ ፖሊስ ባጃጅ ከምታክል አገር- በቀል ሄሊኮፍተር በገመድ ሲወርድ ታየ፡፡ የፖሊስ አዛዡ ተገን ይዞ፤ ባሊ በሚያክል የድምጽ ማጉያ “ ባለመፈክሮች ተከባችኋል፡፡ እጃችሁን ወደ ላይ ሰቅላችሁ ውጡ” በማለት አስጠነቀቀ፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጎረቤታችን አቶ ካሣ-ኖቫ ሙታንታ ብቻ እንደታጠቀ ፎጣ ካገለደመች ጨብራራ ሴት ጋር እጁን ዘርግቶ ወጣ፡፡

“ማን አባህን ነው አትነሣም እያልክ የምትቀሰቅሰው ?አለ የፖሊሱ አዛዥ ገና እንዳየው፤
“ብልቴን ነው ጌታየ!ትንሽ ቅሜ ስለነበር አልነሣም ብሎ ገገመብኝ ፡፡

ውድ አንባቢ እስካሁን የጻፍኩት መግቢያ ነው፡፡ አሁን ዋናው መጣጥፍ ይቀጥላል፡፡ ሠአት እላፊ ከየት ወዴት?
በቅርቡ እንደሚታወጅ የተነገረው ሰአት እላፊ ያዲሳባን የ”ምሽት ክለብ“ ወደ ቀትር ክለብነት ከመቀየር ያለፈ ጥቅም ሊኖረው ስለማይችል እንዲቀር ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡ ትዝ ይለኛል ፤ ልጅ እያለሁ ሰአት እላፊ ተቆጣጣሪዎች ሮንድ ይባሉ ነበር፡፡ በጊዜው አንድ ልጅ ተወልዶ የማይረባ ሆኖ ከተገኘ“አንተ በተጸነስክበት ቀን ምናለ አባትህ ሮንድ ቢያድር ኖሮ”ይባል ነበር፡፡ ብዙ አባዎራዎች ለእናታገራቸው ሰላምና ደህንነት ሲሉ ከሚስታቸው እቅፍ ተለይተው እንቅልፋቸውንና ምቾታቸውን ሲሰው ያድራሉ ብለን እናደንቃቸው ነበር፡፡ ዘግይቶም ቢሆን እንደተሸወድን ገብቶናል፡፡ አንዳንዱ አባዎራ ሮንድ አድራለሁ በሚል ሰበብ ቅምጡን አላስቀምጥ ሲል ያድር ነበር፡፡ በሮንድ ሰበብ ከቤት ለቤት እየተዘዋወረ ግብረስጋ ሲያደርግ የሚያደር ሮንድ በህዝብ ዘንድ በጅ-ሮንድ የሚል ማእረግ ይቀዳጃል፡፡

የሆነ ጊዜ ላይ በመንቆረር ከተማ፤ አንድ ሰውየ ሮንድ ለማደር ከዘራውንና ሦስት ጎራሽ ባትሪውን ታጥቆ ወጣ፡፡ ሚስትዮዋም ይህን ታሪካዊ አጋጣሚ በመጠቀም፤ ከጎረቤት የሚኖረውን ውሽማዋን ሰበር ግብዣ አደረገችለት፡፡ በሽቶ ሳሙና ተጣጥባ ሦስት ማእዘኗን ተለጫጭታ ጠበቀችው፡፡ ውሽምየውም መጥቶ፤ በዱባ ወጥ ራቱን በልቶ፤ ዙርያ ገባውን እየተመለከተ ቀጥሎ የሚያደርገውን በማሰብ ተጠመደ፡፡ መጀመርያ፤ጭድ ፍራሹ ላይ የእንግላል አደርጋለሁ ፤ቀጥየ አጎዛ የለበሰውን ሳንዱቅ አስደግፌ ጫንቃ- ሰበር አስከትላለሁ ፤ቀጥየ ብሎ ሳይቀጥል የኮቴ ድምጽ ከደጃፉ ግድም ተሰማ፡፡ ባልየው ብርዱ ጸንቶበት መመለሱ ነው፡፡

ሚስትዮዋ በጣም ከመደንገጧ የተነሣ ውሽምየውን እንደፋሲካ ዶሮ ቅርጫት ደፍታበት ቁጭ አለችበት፡፡ከዚያም ከፊቷ ያለውን እሳት መሞቅ ጀመረች፡፡ ባልየው ገብቶ ፤ በሚስቱና በምድጃው ፊትለፊት ተጎልቶ፤ በእግሮቿ ማህል አሻግሮ እየተመለከተ ስሜት በተጫነው ወፍራም ድምጽ “ ዛሬ ይሄንን መላጣ ስመልጠው ነው የማድር” በማለት አጉተመተመ፡፡ ቅርጫቱ ውስጥ ያደፈጠው ውሽምየ፤ ባጋጣሚ መላጣ ስለነበር፤ ዛቻው የተሰነዘረው ለርሱ መስሎት ቅርጫቱን ከነሴትዮዋ ገልብጦ ተፈተለከ፡፡ እና አሁን ይሄ ምን ለማስተላለፍ ነው?ሠኣት እላፊ ፤ዜጎች እላፊ ብልት እንዲለምዱ ከማድረግ ያለፈ አስተዋጽኦ አይኖረውም ለማለት ነው፡፡
በመጨረሻ ብዙ አንባቢዎቼ ፤ ከኮማንድ ፖስቱ በኋላ ፤ ምኡዝ ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እንድገልጽላችሁ ጠይቃችሁኝ ነበር፡፡

በቀደም ለታ ምኡዝና ሚስቱ ሄለን፤ በረከቦት ጎዳና ወክ ሲያደርጉ መታጠፍያው ላይ የሆነ ፖሊስ ቆሟል፡፡ ምኡዝ ፖሊሱን ሲያይ መንገድ ቀይሮ ለመሄድ ቃጣ፡፡ ፖሊሱ ትንሽ ጥርጣሬ ስለገባው ምኡዝን አስቁሞ መፈተሽ ጀመረ ፡፡ ሄለን “ ባለቤቴ ከማንም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ግኑኝነት የለውም፡፡ ሺህ ጊዜ ብትፈትሹት ምንም ነገር አታገኙም“ አለች በግብዳ ልበሙሉነት፡፡ ፖሊሱ ከምኡዝ ኪስ ውስጥ ሁለት ፓኮ ኮንደም እየጎለጎለ ሲያወጣ ስታይ ግን አይኗን ማመን አልቻለችም፡፡ “ አንት ሸሌ!አሁንም በኔ ላይ “እያለች የምኡዝን ፊት በጥፍሯ ግልገል ዝንጀሮ የላጠው ቀይሥር አስመሰለችው፡፡ ፖሊሱ እየሳቀ ትንሽ ከገላገለ በኋላ መንገዱን ሊቀጥል ሲል ምኡዝ እየሮጠ ደረሰበት፡፡
ፖሊሱ “ ምን ፈለግህ?” ሲለው ምኡዝ አንጀት በሚበላ ድምጽ ” በዚህ አይነት ሁኔታ ወደ ቤቴ እንድመለስ ከምትፈርድብኝ፤ አንድ ሳምንት በማሠር ለምን አትተባበረኝም ?ብሎ እጁን አመሳቅሎ የተቃውሞ ምልክት አሳየ፡፡

bewketu

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የካቢኒያቸውን አዳዲስ እጩ አባላት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያቀረቡ ነው።

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሉበት ይቀጥላሉ ያሏቸው የካቢኒ አባላት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ አህመድ አብተው፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ፣ የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ይናገር ደሴ፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ናቸው።

አዲስ የቀረቡት እጩ የካቢኒ አባላት፦

1. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

2. አቶ ታገሰ ጫፎ፦ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር

3. ዶክተር አብረሃም ተከስተ፦ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር

4. ዶክተር በቀለ ጉላዶ፦ የንግድ ሚኒስትር

5. ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ፦ የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር

6. ዶክተር ኢያሱ አብረሃ፦ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር

7. ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

8. አቶ አህመድ ሺዴ፦ የትራንስፖርት ሚኒስትር

9. ዶክተር አምባቸው መኮንን፦ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር

10. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፦ የኮንስትራክሽን ሚኒስትር

11. ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፦ የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር

12. አቶ ሞቱማ መቃሳ፦ የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር

13. ዶክተር ገመዶ ዳሌ፦ የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር

14. ዶክተራው ሽፈራው ተክለማርያም፦ የትምህርት ሚኒስትር

15. ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ፦ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር

16. ዶክተር ግርማ አመንቴ፦ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር

17. ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም፦ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር

18. ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቤሳ – የሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር

19. አቶ ርስቱ ይርዳው፦ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር

20. አቶ ከበደ ጫኔ፦ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊ ሚኒስትር

21. ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፦ የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ናቸው።

Image may contain: 1 person , suit and office