አዲስ አበባና አዳማን ጨምሮ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤት ሰብሮ ማሰርና መሰወር ተባብሶ ቀጥሏል


Photo File

(ቢቢኤን) በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ እጅግ እየተባባሰ መምጣቱን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰበብ የሚደረገው የእስር እና የአፈና ዘመቻ መበርታቱን የጠቆሙት መረጃዎች፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በአዳማ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ሰዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ እንደ መረጃዎች ገለጻ ከሆነ፣ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተሰማሩት የአስቸኳይ ጊዜ አስፈጻሚ ወታደሮች የሚፈጸመው ግፍ እጅግ ጨምሯል፡፡
ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤት ሰብሮ መግባት፣ ሰዎችን አፍሶ መውሰድ፣ ወስዶም ወዳልታወቁ ስፍራዎች መሰወር የሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ከሆነ የሰነባበተ ሲሆን፣ በርካቶችም እንደ ቀልድ ወጥው የሚቀሩበት ሁኔታ በብዛት እየተፈጠረ ነው፡፡ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በተለይም ሰሜን ጎንደር አካባቢ ባሉ የገጠር ቀበሌዎች ያለውን አለመረጋጋት የተመለከቱ እማኞች፣ መንግስት እንደሚለው ሀገሪቱ ወደቀድሞ ሰላሟ እየተመለሰች እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት-እማኞቹ፡፡ እንደዚሁም በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች የተሰማሩ ወታደሮች ሰላማዊ ዜጎችን እያሸበሩ ነው ተብሏል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ ለሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቦች መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ ሀገሪቱ እየተረጋጋች ስለመጣች አዋጁ ሊነሳ ይችላል ሲሉ ገልጸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ አጋጣሚ ሀገሪቱ መረጋጋቷን ይግለጹ እንጂ፣ ነባራዊው ሁኔታ ግን ፈጽሞ ከሚሉት ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን ጨምሮ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች፣ ከመረጋጋት ይልቅ የተባባሰ ሁኔታ እንደሚታይባቸው ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s