ስንት አይነት ባንዳ አለ?


corruption

Alemayehu Kidanewold

ስንት አይነት ባንዳ አለ? ብለህ ጠይቅ:: መልሱ ያስደነግጣል:: አንዳንዱ ነጋዴ ባንዳ ነዉ::አንዳንዱ ምሁር ባንዳ ነዉ::አንዳንዱ ዲያስፖራ ባንዳ ነዉ::ከሁሉም የከፋዉ ደግሞ የተቃዋሚ ባንዳ አለ::ሁሉም ባንዳዎች ግን የጋራ መገለጫ ባህሪያቸዉ አድር ባይነታቸዉን በምክንያት ለመሸፈን መታገላቸዉ ነዉ::የግል ባንዳዊ ፍላጎታቸዉን በህዝብ ደም እጃቸዉን እየታጠቡ የራሳቸዉን ድርጊት ተጠይቃዊ ለማድረግ መባዘናቸዉ ነዉ::ዛሬ አንድ ነገር አዉርተዉህ በሳምንቱ በስትራቴጅ እና በታክቲክ ስም ተገልብጠዉ እንደሰካራም ሳይጠጡ ቀድሞ የተናገሩትን ሀሳብ አጣጥለዉ ሌላ ሀሳብ አምጥተዉ ሊያወናብዱህ ሲሞክሩ ታገኛቸዋለህ::ዋና ግባቸዉ አንተን ማወናበድ እና ተስፋ ማስቆረጥ ነዉ::ወያኔ የሰጠቻቸዉን ተልዕኮ እየተወጡ መሆኑ ነዉ::

አሁን ህዝቡ ወያኔን መቃወም ብቻ ሳይሆን ባለጌዋን ወያኔን ጠመንጃ አንስቶ እየተፋለመ ነዉ::ወያኔ በሰላማዊ መንገድ እና በሀሳብ ክርክር እንደማትወርድ የተረዳዉ ህዝብ የመጨረሻዉን ዉሳኔ አሳልፎ ወያኔን በጠመንጃ ሀይል ለማዉረድ ጫካ ገብቶ እየተፋለመ ነዉ::ወያኔን ከመንበሯ ሳይፈነቅል ህዝቡ ከእንግዲህ ወደ ቤቱ አይመለስም:: ይሄን በመራራ ተጋድሎ ዉስጥ ያለ ህዝብ ወይ ተቃወም ወይም ደግፍ በማለት እጃቸዉን በደም የሚለቃለቁት እና በፖለቲካ ፓርቲ ስም ጀርባ ያደፈጡ እነ አበባዉ መሃሪ: እነ ዶክተር በዛብህ: እነ ልደቱ አያሌዉ ; እነ ትግስቱ አወል የወያኔን የፖለቲካ አላማ ለማስፈጸም ደፋ ቀና እያሉ ነዉ:: ይሄ ዋናዉ ከባንዳነትም በላይ ባንዳነት ነዉ::

ህዝባዊ ለመምሰል ወያኔ ያፈረሰቻቸዉን የፓርቲ ስሞች ሙጥኝ ብለዉ ህዝብን የሚያጭበረብሩት መስሏቸዉ በወያኔ ካርታ እየተጫወቱ ነዉ::መኢአድን: አንድነትን እና ሰማያዊ ፓርቲዎችን የሚመሩት ህጋዊ አመራሮችን ወያኔዎች ከፖለቲካ መድረኩ ገፍትረዉ አዉጥቷቸዋል::እናም የእነዚህ ፓርቲዎችን ስም ደግሞ ወያኔ ጠፍጥፋ ለሰራቻቸዉ ባሌጌ እና ባንዳ ግለሰቦች አስረክባቸዋለች:: እናም እነዚህ ባለጌ እና ባንዳዎች ሳያፍሩ እና ሳይሸማቀቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ፊት ቀርበዉ ህዝቡን ወይ ደግፍ ወይም ተቃወም የሚል አጀንዳ እያራመዱ ነዉ:: አሁን ደርሶ ተቃዋሚ ለመምሰል; ቁምጣ ያጠለቀ ጀግና ለመሆን ደፋ ቀና ሲሉ ለሚያያቸዉ ሰዉ የሚያሸማቅቅ ስሜት ያጭራል::ባንዳ እንዴት ነዉ ተቃዋሚ የሚሆነዉ? የሚል ጥያቄ ግን እህዝቡ ህሊና ዉስጥ እንደሚመላለስ በደንብ ያዉቃሉ::ሆኖም ወያኔ የምትሰጣቸዉን የቤት ስራ ባይሰሩ ወዮላቸዉ::

ሁሉን ሰብስቦ በአንድ የሚያታግል : መሪ ፖለቲከኛ እና መሪ ፓርቲ አጥቶ እንጅ ህዝቡ እማ ወያኔን ተቃዉሞ ብቻ ሳይሆን ወያኔን ሊዋጋ ያለዉ ጫካ እንደሆነ ያዉቃሉ::የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ልቡ ያለዉ ጫካ ነዉ:: የሁኔታዎችን መመቻቸት ብቻ የሚጠብቀዉ ሀይል ይበዛል::ባንዳ እና የወያኔ ተላላኪዎች ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ተቃዉሞ እና ተጋድሎ ላይ ይሳለቃሉ::ወይ ተቃወም ወይ ደግፍ እያሉ በህዝብ ላይ ሊሳለቁ ተነስተዋል::

ሌሎች ባንዳዎችም ሰሞኑን ተነስተዋል::ከወደ ዲያስፖራዉ አካባቢም ወያኔ የመለመለቻቸዉ ባንዳዎች አሉ::ወያኔ ፕሮጀችት ነድፋላቸዉ በዬ ኢንባሲዉ የፕሮጀችት ፈንድ የተስፋ ቃል ተገብቶላቸዉ ስለ ወያኔ ህጋዊነት እና ልማታዊነት እንዲሰብኩ የተዘጋጁ አሉ::እነዚህ የተማርን ነን ይላሉ::ይባስ ብለዉም የቴክኖሎጂ ባለሞያም ነን ይላሉ::አንዳንዶቹ እዉነትም ናቸዉ::አንዳንዶቹም ቁጭ ይበሉ ናቸዉ::ግን በቀን ዉስጥ አለ ወንጀላቸዉ በእምነት ቦታ ሽዎች ስለመገደላቸዉ ወይም ደግሞ ለሰላማዊ ተቃዉሞ ስለወጡ ብቻ በአስር ሽህዎች ስለመታሰራቸዉ እና ስለመቁሰላቸዉ ግድም አይሰጣቸዉም::ብቻ የፕሮጀችት ገንዘብ ይገኝ እንጅ እነሱ ከቶም የባንዳ እና የአድር ባይ ልባቸዉ ግድም አይላቸዉ::ባንዳ ምን አለበት::ከበላ በቂዉ ነዉ::ከሁሉም የሚያስተዛዝበዉ ደግሞ እነዚህ ወገኖች አንድ ሰሞን ተቃዋሚ ሆነዉ የሞቅታ ስሜት ዉስጥ በመገኘት ህዝባዊ ለመምሰል ሲወለጋገዱ የታዩ ጭምርም አሉበት::

ተጨማሪ ባንዳዎችን መቁጠር ይታክታል::አማራ ነን እያሉ አማራን የሚያሳርዱ ; ኦሮሞ ነን እያሉ ኦሮሞን የሚያሳርዱ : ኢትዮጵያዊ ነን እያሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚያስጠፉ ብዙ ባንዳዎችን መቁጠር ይቻላል::ዲሞክራሲን ባፋቸዉ እየሰበኩ በልባቸዉ ግን ሆዳቸዉን ተሸክመዉ የሚዞሩ:: እዚህ አሳይተዉ እዚያ የሚተኩሱ::በማህበራዊ ሚዲያዎች ሀገር ቤት ያለዉን ታጋይ አድፍጠዉ በመገናኘት እንዲሁም ጥቂት ሳንቲም በመላክ በወያኔ ቀለበት ዉስጥ ታጋዮች እንዲገቡ የሚያደርጉ ሞልተዋል::በማህበራዊ ሚዲያዉ ህዝባዊ መስለዉ እየጮሁ እና ሀገር ቤት ካሉ ታጋዮች ጋር ሚስጢር እየተለዋወጡ በመጨረሻም ሀገር ቤት ያሉትን ታጋዮች የሚያስጠልፉ ባንዳዎች በርክተዋል::ይባስ ብለዉም የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች እርስ በርሳቸዉ እንዲጠላሉ በማህበራዊ ሚዲያ አንዴ አንዱን ብሄረሰብ እየሰደቡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላዉን ብሄረሰብ የሚሳደቡ ባንዳዎች ብዙ ናቸዉ::

በባንዳነት ባይፈረጁም የባንዳዎችን ጎዳናም ቀላል እንዲሆን የሚያመቻቹ ሀይሎችም ሞልተዋል:: ነጻነት ቀልድ አይደለም::በአንንድ ሰሞን እሩጫ አይገኝም::ሁሉን አምኖ እና ከሁሉ ጋር እሮጦም አይገኝም::ብዙ እቅድ: ብዙ ጥናት: ብዙ ድካም እና የረዥም ጊዜ ስራ ይጠይቃል:: ሆኖም ይሄን እዉነት ለመሸከም ያልፈቀዱ ወይም የማይፈቅዱ እየተገኘበት ተቃዋሚ ጎራ ዉስጥ እየተመሰጉ የታገሉ የሚመስላቸዉን እና ነጻነት የሚናፍቁትን ወገኖች በባንዳነት ባንፈርጃቸዉም ቅሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ተጋድሎ እርምጃ ግን ዉስብስብ ባህሪዉን ይበልጥ የሚያወሳስቡት ሀይላት መሆናቸዉን ጠቁሞ ማለፍ ይገባል::

ነጻነትን ከኢትዮጵያ ጠላቶች እና ነጻነትን እራሱን ከማያዉቁ ምናምንቴዎች ጉያ ተሸጉጠዉ የሚናፍቁ ሆኖም ብዙ የሚደክሙና የሚለፉ ብኩኖችም ያዉ የባንዶቹን ዘወርዋራ ጎዳና እያገዙት ነዉ::ትግል ጥራት ይፈልጋል:: ከጠላት ጋር ተኝተህ ስለጠላት ማማት እንደማይቻል ሁሉ ለጠላት መግቢያ ቀዳዳዎችን አስር እና ሀያ ቦታም ሸንቁረህ ስታበቃ ስለ ትግል ሚስጥራዊነት ማዉራት በራሱ የባንዶቹ አጋዥ እንጂ የህዝባዊነቱ አካል አያደርግህም::የባንዳነት ዘርፉ ብዙ ነዉ ለማለት ያህል ብቻ ሳይሆን ብኋላም የሚያስጠይቅ እንደሆነና የሚያስከፍለዉም ዋጋ እንዳለ ለማመላከት ነዉ::

ሸንቁጥ አየለ

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s