በቆሼ ተቀብረው ነዋሪዎች ካለቁባቸው ቤቶች አብዛኛው ህጋዊ ምሪቶች ናቸው ተባለቅዳሜ ምሽት ሁለት ሰዓት በተፈጠረው የቆሻሻ ክምር መደርመስ ከተቀበሩት ቤቶች አብዛኛዎቹ በቀድሞ መንግስት ጊዜ በህጋዊ መንገድ በማህበር ተመርተው የተሰሩ መሆናቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች መረዳት ችያለሁ፡፡ዛሬ ረፋዱ ላይ በሥፍራው ተገኝቼ እየተደረገ ያለውን ፍለጋ ተመልክቼአለሁ፡፡የአካባቢውን ነዋሪዎች አነጋግሬ ባገኘሁት መረጃ መሠረት ‹‹ከተደረመሱት ቤቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ በቀድሞ መንግስት ዘመን በህጋዊ መንገድ ተመርተው የተሰሩ ህጋዊ ቤቶች መሆናቸውን ነግረውኛል፡፡ያለቀው ህዝብ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ገና ግሹም አልወጣም›› ሲሉም በእርግጠኝነት ይናገራሉ፡፡‹‹ከ30 ቤቶች በላይ ተብረዋል፡፡በእያንዳንዱ ቤት የሚከራዩ ቤቶች አሉ፡፡በአንድ ቤት ግቢ ብቻ 8 አባወራ ተከራዮች ነበሩ፡፡የዚህ ሁሉ አስክሬን መቼ ወጣ ሲሉ እንባ እያነቡ ይናገራሉ፡፡የመሬቱ መደርመስ መንስኤው እስካሁን ግልጽ አይደለም፡፡

Bezuayehu Wondimu Feysa

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s