Archive | April 2017

የጋሼ አሰፋ ሞቱ፤ ለመግባት ከቤቱ…! (በመስከረም አበራ)

Assefa Chabo

ጋሼ አሰፋ ጫቦ የኢትዮጵያን ፍቅር እንደማተብ በአንገቱ አስሮ፤እንደ እንደ መልካም ሽቶ ለሌሎችም ሲረጨው የኖረ ሰው ነው፡፡ ሃገሩን የሚወድበት ውድ የልክፍት አይነት ብርቱ ነበር፡፡ በሰው ሃገር ተኝቶ በኢትዮጵያ ሰማይ ምድር፣ በሃገሩ ወንዛ ወንዝ፣በጋሞ ጭጋጋማ ተራሮች ግርጌ፣ በሰላሌ ሜዳ፣ በጣና ገዳማት፣በሊማሊሞ አቀበት የሚያዞር ህልም የሚያሳልም የሃገሩ ፅኑ ፍቅር የወደቀበት ሰው ነበር፡፡ከህልሙ ነቅቶ ብዕር ሲያነሳ ያለ ሃገሩ እትብት የመጓተት ፖለቲካ ደዌ፣ገዳዳ የፍትህ ስርዓት፣የልመና አቁማዳ የሚያስነግት አዋራጅ ጠኔ፣ወልጋዳ ፕሮፖጋንዳ፤ ሌላ አይታየውምና እሱኑ ያነሳል ይጥላል፤ለሚሰማው የሚሻል የመሰለውን መንገድ ያሳያል፡፡ የጋሼ አሴን የሃገር ፍቅር ተራራ አይጋርደውም! ለዚህ ነው ምቹው የስደት ሃገር ያልተስማማው፤ስንቱ በእግር በፈረስ የሚሞክረው ስደት ለእሱ እንደ ምርግ ከብዶት ከሃገር ከአፈሩ፤ ከወፍ ከዛፉ ያላስማማው፤ባይተዋር ያደረገው፤ሞቱን ሳይቀር በድብቅ ለማድረግ ያስጨከነው!የሃገር ፍቅር ረሃብ በሰው ሃገር መልካም ምግብ አይጠረቃም፡፡ በቅንጡ ሆስፒታልም አይታከምም!

የጋሼ አሰፋ ነፍስ ለስጋዋ በተመቻት ቦታ ትረጋጋ ዘንድ እምቢ ብላ ‘ሃገሬን’ እያለች ስታስጨንቀው የኖረች ይመስለኛል፡፡መላ ስትዘይድም ያልተመቼውን ስጋዋን ገድላ ከሙት በቀር ህያው የማይወዱትን ነገስታት ጠመንጃ በሞት ተከልላ ሃገሯ ለመግባት መርጣ ይመስላል ጋሼ አሰፋን የተነጠቅነው፡፡እሱን የመሰለ ብዕረ-መልካም ሰው መነጠቅ በቀላሉ የሚተኩት ኪሳራ አይደለም፡፡ በወር አንድ ጊዜ እንኳን አንድ ገፅ የብዕሩን ቱፍታ ቢያጋራን ብዙ እናተርፍ ነበር፡፡ በልጅነት በጉልምስና የማያጠፋ የለምና ጥፋት ቢኖረው እንኳን ከጥፋቱ ሳይቀር የሚያስተምርበት ብዕሩን እንድንጠቀም በሚያደርግ መልኩ ሁሉን ማድረግ ይቻል ነበር-የቂም በቀል ክስ ፈብርኮ የማምሻ እድሜውን የሚያስፈጅ የቅጣት ድግስ ከመደገስ፡፡

እንደ መዥገር እላያችን ላይ የተጣበቁት ነገስታት ግን ለመንግስትነት የሚበቃ ምህረትም ሆነ አርቆ አስተዋይነት የላቸውምና እነሱ እጁን ይዘው የማይመሩት ሰው በሃገር አይኖርም፡፡ ይሄው እኩይነታቸው ወርቁን ሰው ጋሼ አሰፋን ከሚወዳት ሃገሩ ብን ብሎ በሰው ሃገር መዳብ ሆኖ ጎኑን ሳይመቸው እንዲኖር አደረገው፡፡ሃገራቸውን ‘ቅኝ ገዥ’ ብለው አነውረው ‘ለሰው ሃገር’ እንሙት የሚሉ፤ ርጋፊ የሃገር ፍቅር ያፈጠረባቸው የባንዳ ልጆች የማይወዷት ሃገር ባለቤት ሆነው ሃገሩን የሚወድ ሰው በስደት ምድር ነፍሱ እንድትራቆት ማድረጋቸው መራር ነው፡፡ ከሰው እንዳልተፈጠረ፣ወገን እንደሌለው፣ ቢያንስ በብዕሩ ለሃገር እንዳልጠቀመ በመጨረሻው ሰዓት ከሞት ጋር ሲተናነቅ እንኳን የኔ የሚለው ሰው በሌለበት እንዲሆን ከማድረግ ሌላ ምን የበቀል ጥግ ሊገኝ? የዚህ ቁጭትስ እንዴት ሆኖ ከወገን ሆድ ይወጣል?!ይህን ሁሉ ክፋት በክንዳቸው ብርታት ያደረጉ ለሚመስላቸው በቀለኛ ነገስታት የኛ በሃዘን ማረር የሃሴት ጊዜያቸው ነው፤አንድ ባለጋራ ወድቆላቸዋልና “ጎፈሬ” ያበጥሩ፤እኛ ብዙ የጎደለብን ደግሞ ብዙ እናልቅስ! ፈልገናቸው “የልባችን ናችሁ” ብለን አልሾምናቸወምና ሃዘናቸው እና ሃዘናችን ገጥሞ አያውቅም፡፡ዘር ቆርጥመው የሚበሉ ናቸውና ዘር እንዳይተርፍልን በክፋታቸው የዋኖቻችንን እድሜ አሳጥረው በታላላቆች መክሊት ሳንጠቀም እንዲሁ ቀረን!

ጋሼ አሰፋ በግል ህይወቱ ባህሪው ምን አይነት እንደሆነ አላውቅም፡፡ሰው ነውና እንከንም አይጠፋበትም፡፡በግል ባህሪው ወደድነው ጠላነው ባለ ወርቅ ብዕር እንደሆነ ግን ማንም አይክደውም፡፡ የብዕሩ ቱፍታ ለዛ የማይጠገብ፤የወርቅ ብዕሩ ክታብ የተጓዘበት ፍኖት ቢሄዱበት የማይሰለች፤ ቢያፈጡበት የማይደክም እንደሆነ በወዳጁም በጠላቱም ፊት የተሰወረ አይደለም፡፡በደልን የሚተው የይቅርታ ሰውነቱም የሚካድ አይደለም፡፡ አስራ አንድ አመት መታሰሩን አሁንም አሁንም እያነሳ የሞኝ ለቅሶ ሲያለቅስ አላየንም፡፡ ይልቅ “ያለፈው አለፈ አሁን የጋራቤታችንን እንዴት ገንብተን በምን እናሙቅ” በማለቱ ላይ ይበረታል:: ስለዚህ ነገሩ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ተገርሞ ‘አንተ ግን እንዴት ነው የአስር አመት እስርህን በመፅሃፍህ ላይ በለሆሳስ ያለፍከው’ ብሎ ጠይቆት ነበር፡፡ ‘አስሬ ባወራው ምን ይጠቅማል፤ደጋግሞ ማውራቱ የሆነን ነገር ከመሆን አይቀንስ አይጨምር ምን ዋጋ አለው፤ ይልቅ ትርፍ ስላለው የወደፊት ነገር ማውራቱ ይበጅ ይመስለኛል’ ሲል ነበር የመለሰው:: ጋሼ አሰፋ የኢትዮጵያ ፍቅር ያመጣበትን ለኢትዮጵያዊነት የመቆም ሙግት ሲያስረዳ ስሜትን ሳይሆን ምክንያትን ተላብሶ እንደሆነም አይካድም፡፡ በዚሁ የሚተቹት “ኢትዮጵያን ካላፈረስን” ባዮች በፊቱ ቆመው ከመሞገት ይልቅ ማዶ ሆነው ሽምግልናውን በማይመጥን ሁኔታ ስድብ የተሞላ አፋቸውን የሚከፍቱበት ምክንያት ስሜታዊነታቸው የምክንያታዊነቱን ጉልበት፤የግንዛቤውን ጥልቀት፤ የንባቡን ስፋት ይቋቋመው ዘንድ ስለማይችል ነው፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ ጋሼ አሰፋ የብሄር ፖለቲካን የሙጥኝ ቢል ኖሮ ይህን ሁሉ የስደት ስንክሳር ባላየ ነበር፡፡ እንደማንኛውም የጎሳ ፖለቲከኛ ያኔ አስራ አንድ አመት ሲታሰር የጋሞን ህዝብ ሁሉ ይዞ እስርቤት የገባ አስመስሎ፤ራሱን ህዝብ አሳክሎ ቢያላዝን ተከታይ እንዳይጠፋ ነው?! በጎሳ ፖለቲካ ተፀንሶ ተወልዶ ለዚህ የበቃው ህወሃትም ይህን አይጠላም ነበር፡፡ “በነጋ በጠባ የምበጥስ የምቀጥለው ማተብ የለኝም” የሚለው ጋሼ አሰፋ ግን አለማቀፍ ወዛደራዊነትን በዘመረበት አፉ በጋሞ ሸለቆዎች ብቻ በሚሽሎከሎክ ጥበት ኢትዮጵያዊነቱን ቸል ይል ዘንድ የግንዛቤው ስፋት በጄ አላላውም፡፡ ይልቅስ ጋሞነቱ ከኢትዮጵያዊነቱ ተጣልተውበት ሊያስታርቅ ቁጭ ብሎ እንደማያውቅ በብሩክ ብዕሩ አስነብቦናል፡፡ ነፍሰ-ስጋውን አልተመቼውም እንጅ ያልተበጠሰ ማተቡን በአንገቱ እንዳሰረ ማንቀላፋቱ ተገለባባጭ በበዛበት ምድር አርአያነት ነው፡፡ እኛ ብዕሩን የለመድን ግን ክፉ ጉዳት ተጎዳን!

ስለ ጋሼ አሰፋ የሰማሁት የተስፋየ ገብረአብን ተግተልታይ ማስታወሻዎች በማነብ ሰሞን ነበር፡፡ ሁለተኛውን ማስታወሻውን ካነበብኩ በኋላ ከጓደኞቼ ጋር ሰብሰብ ብለን ስላነበብናቸው መፃህፍት በምናነሳሳበት የማኪያቶ ሰርክል ከተስፋየ ማስታዎሻዎች ውስጥ የሳበኝ ነገር ቢኖር የአማርኛው ውበት እንደሆነ ገለፅኩ፤ ብዙዎች ተስማሙ፡፡ ከመሃላችን አንዱ “በቃ ተስፋየን ተንኮሏን ብቻ አሳቅፋችኋት ቀራችሁ ማለት ነው” ሲል “እንዴት?” አልኩኝ፡፡ “ተስፋየ የአማርኛ ውበቱን የቀዳው አንድ አሰፋ ጫቦ ከሚባል የአርባምንጭ አካባቢ ሰው ብዕር እንደሆነ ራሱ ተስፋየ እንደተናገረ የሆነ ቦታ አንብቤያለሁ” ብሎ ጀምሮ ስለ ጋሼ አሰፋ ብዙ አጫወተን፡፡ “እኛ እንዴት አናውቀውም ታዲያ?” ጥያቄያችን ነበር፡፡ “ተፈጥሮ ምቀኛ ሆነችባችኋ! ወያኔ ሲገባ እያንዳንድሽ ትምህርትቤት ከገባሽ አነሰሽና ነው ጋዜጣ አንባቢ የሆንሽው?” ብሎ ቀልዶ ጋሼ አሴን ያላወቅንበትን ሚስጥር አስረዳን፡፡  “እስኪ የፃፈው ነገር ካለ አውሰኝ” ብየ ለመንኩ፤ አባቱ የከዘኑትን የጋሼ አሰፋ በጋዜጣ መፅሄት የተዘራ ምርት፣ የሰጣቸውን አንድ ሁለት ቃለ ምልልሶች አምጥቶ ዘረገፈልኝ፡፡

የጋሼ አሰፋ ብዕር ከሰማሁት በላይ ሆኖ አገኘሁት፡፡ ብዕሩን ወደድኩት፤ርቱዕ አንደበቱን አደነቅኩ፤ቅልል ጥፍጥ ያለ ቋንቋው በመንፈስ የቅርቤ ሰው አደረገው!!!!! “አሁን ከወዴት አለ?” ብየ ጠየቅኩ ባስቀር የምወደውን የተዋስኩትን ጋዜጣ መፅሄት ስመልስ፡፡ “አሁን ያው ወያኔ የሽብርተኛ ህጉን ሳታወጣ የደበራትን በምትከስበት የሆነ አንቀፅ ተከሶ ድንገት እንደወጣ ቀረ፤ከዛም የገባበት እንደጠፋ  አባቴ ነግሮኛል” ሲል አጫወተኝ፡፡ ‘የገባበት ጠፋ’ ውስጥ ሞትም እንዳለ ጠረጠርኩ፤በአሉ ግርማ ትዝ አለኝ፤አለመታደል ተሰማኝ! የዋና እና የመደዴ፤የምርት እና የግርድ ቦታ ያቀያየረችው ሃገሬ መጨረሻ አሳዘነኝ፡፡ “ሞትም ይኖራል በለኛ” አልኩ ቅዝዝ ብየ፡፡ “ከሞተ እንኳን ይሰማ ነበር፤ካለም የበላው ጅብ አንድ ቀን ይጮሃል” ብሎኝ ተለያየን፡፡

የሞቱን ስጋት ሽውታ ችላ ብየ የበላው ጅብ በቶሎ እንዲጮህ ተመኘሁ፡፡ እግዜር ይስጠው ቶሎ ጮኽ! ጭራሽ “የትዝታ ፈለግ”ን እነሆ አለን፤ትልቅ ሆኖ ሳለ ከእኛ ጋር ወርዶ በፌስቡክ ሜዳ ላይ አብሮን ሰነበተ፤የቅርባችን ሆነ፤የሃገሩን ጠረን ሃገርቤት ባለን ወገኖቹ በኩል ማሽተት ጀመረ፤ሃገሩ የገባ ሳይመስለውም አልቀረም፡፡ በዚህ ነፍሱ ደስ እንዳላት በፌስ ቡክ መስኮት አጫውቶኛል፤በዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ!ጋሼ አሰፋ ራሱ እንዳጫወተኝ ሃገሩን አደራ የሚላቸው ወጣቶችን በመብራት ይፈልጋል፡፡ብዙ ባዝኖ ሲያገኝ ትቂቷን ጅማሬያቸውን አግዝፎ አይዟችሁ ይላል፡፡ ሞቱን ትከሻው ነግሮታል መሰል የተተኪ አሳቢ አሰላሳይ ነገር እጅግ ያሳስበው እንደነበረ፤አሁን ፌስቡክን ተቀላቅሎ ሲያይ ካሰበው በላይ ሃገሩ ደጀን እንዳላት በመረዳቱ በጣም እንደረካ ያጫውተኝ ነበር፡፡ እኔ ቀደም ብየ ልወቀው እንጅ እሱ ያወቀኝ ከአውስትራሊያው SBS ሬዲዮ ጋር የነበረኝን ቆይታ አዳምጦ “በርቺ በልልኝ” ሲል ለጋዜጠኛ ካሳሁን ኢሜል አድርጎ ካሳሁን ካደረሰኝ በኋላ ነው፡፡

ጋሼ አሴ እንደ አብዛኞቹ የዘመን አጋሮቹ ያሁኑን ትውልድ በመናቅ በመርገም አይነሳም፡፡ይልቅስ ልጆች ናቸው ብሎ ሳይንቅ ለመራመድ መውተርተራችንን እንደ ትልቅ ቆጥሮ በርቱ ይላል፡፡የራሴን ባወራ ትንሽ ቀላጤ ስፅፍ ከእውቀቱ በላይ የማውቅ ይመስል የሚያበረቱ ቃላት ከሽኖ ይልክልኛል፤ “ፅሁፍሽን ለማውቃቸውም ለማላውቃቸውም ሳጋራ፣እንዲያነቡ ስጋብዝ ሰነበትኩ፤እናንተን በማየቴ ሃገሬ አውላላ ሜዳላይ እንዳልቀረች አስባለሁና ነገ አያስፈራኝም” ይላል የሚወዳትን ሃገሩን በሁነኛ አደራ ተቀባይ መዳፍ ላይ ለማኖር ሲቃትት!

ምን ያደርጋል እንደተመኘው ሃገሩ ሻል ሳይላት እንደታመመች ቁርጧን ሳያይ፤ሰሚ ባልሆነ የፈርኦን ጆሮ ላይ “ኢትዮጵያን ማሯት” ሲል እንደለፈፈ፤ለእናት ምድሩ እንደማለደ፤ሰምቶ የሚመልስ ሳያገኝ ወደ ማይመለስበት ሄደ፡፡ ርቱዕ አንደበቱ ተዘጋ፡፡አይጠገብ ብዕሩ ድንገት ነጠፈ፡፡አቻቻይ ማንነቱ ተነነ፤ ኢትዮጵያዊነትን የሚያዜምበት በገናው ወደቀ፡፡ “የጋራቤታችንን” ማገር የሚያጠብቅበት የመልካም ሽማግሌ ድንቅ ምክሩ ሲያምረን ቀረ! ከእውቀቱ ጥልቅ የምንቀዳው ውሃ፤የምንቋጥረው ስንቅ ጎደለ፡፡የምንሰባሰብበት የኢትዮጵያዊነት አንድ ባንዲራ ወደቀ፡፡ ከእድሜው ድርና ማግ የምንሸምነው የእውቀት ቡልኮ አጠረ፡፡ከመውደቅ መነሳቱ፤ከ‘ትዝታ ፈለጉ’ የምንቀስመው የልምድ ሰፈፍ ተቆረጠ፡፡የሆነው ሆኖ በድኑ የናፈቃት ሃገሩ መጥቶ እንዲያርፍ እየተሞከረ ያለው ነገር ከተሳካ ጥሩ መፅናኛ ነው፡፡ አምላክ የትልቁን ሰው ውብ ነፍስ  በአፀደ ገነት እንዲያኖርልን፤ለእኛም መፅናናቱን እንዲሰጠን እየተመኘሁ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ የጋሼ አሴን ሞት አስመልክቶ የገጠማትን ከእንባ ጋር የምታታግል ግጥም አስከትየ ላብቃ!

Assefa Chabo

ናፍቆታል ሃገሩ፣ጥያሜው ጠረኑ
በስጋው ተሳዶ፣ይያት በአስከሬኑ፤

“አሻም!” በሉት ውጡ፣ አበባ ጎንጉኑ
ገላው ላይ በትኑ፣አፈሩን ዝገኑ….

የዕድሜ እንቆቅልሹ፣ የዘመን ትብትቡ
የትዝታው ፈለግ፣ፍቅር የሃገር-ሰቡ
ያንድነት ሃሳቡ፤ያብሮነት ረሃቡ…..

ይፈታለት ህልሙ፤
ይውጣለት ህመሙ
ናፍቆት ሰቀቀኑ
ይሁንለት መጥኑ፤

ሃገሩ መድረሱን፣በሰው መከበቡን
ቡና መወቀጡን፣ወጡ መወጥወጡን
ክረምትና በጋ
ቆላ ወይና ደጋ
በሃሴት መውቀጡን ሌሊቱ እስኪነጋ
ሰስቶ መታየት፣ማውጋት ከእንግዳ ጋ፤
ያውቀዋል አየሩን
ይረዳዋል ነፍሱ
ባያይ እንኳን ዐይኑ
ያውቃል ደመነፍሱ
ለመላ ነው ሞቱ
ለመግባት ከቤቱ፤
“አሻም!” በሉት ውጡ፣አበባ ጎንጉኑ
ገላው ላይ አብኑ፣አፈሩን ዝገኑ
ይብረድለት ሱሱ
ቃናዋ ነው ምሱ

ይቁረጥለት ጥሙ
አፈሯን ይቅመሰው
መለስ ይበል ቅስሙ
ቸሰስ ይበል ጅስሙ…

ሃሳቡን ትውረሰው፣
ገላውን ትጉረሰው
አገር ያጊጥበ፣ተጓትቶ ይልበሰው
ከበቀለበት ሰው፣ተሻምቶ ይቅመሰው፡፡

/ግጥም፡ በዮሐንስ ሞላ/

በመስከረም አበራ (meskiduye99@gmail.com)

የሶማሊ ልዩ የሚሊሺያ አባላት የደሞዝ ጭማሪ ጠየቁ። ታጣቂዎቹ ትእዛዝ ለመቀበል ፈቀዳኛ አለመሆናቸውንም አስታውቀዋል

 ኢሳት ዜና :- በቅርቡ ከ200 ያላነሱ የኦሮሞ ተወላጆችን በመግደላቸው እየተወነጀሉ ያሉት በአቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር የሚመሩት የሶማሊ ልዩ ሚሊሺያ አባላት ፣የደረሰባቸውን ጥቃት ተከትሎ፣ የጉዳት ካሳና ደሞዝ ካልተጨመራቸው ማንኛውንም አይነት ትእዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።
የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት ለመዝመት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወደ አካባቢው በቅርቡ የተጓዙት አዲስ የተሾሙት የደህንነት አባል መከላከያው የልዩ ሃይሉን ቦታ ተክቶ የኦብነግን ጥቃት እንዲከላከል አዘዋል።
የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት ለደረሰባቸው ጉዳት ከጠየቁት የጉዳት ካሳ በተጨማሪ፣ 7 ሺ ብር ወርሃዊ ደሞዝ ካልተከፈላቸው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለመንቀሳቀስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል። ሰራዊታቸው ለመታዘዝ ፈቃደኛ አለመሆኑን የተረዱት አቶ አብዲ፣ የግዛት ማስፋፋት እንቅስቃሴያቸውን ገትተው ከኦሮምያ አስተዳደር ጋር ድርድር ለማድረግና የሰላም ስምምነት በሚል ጊዜ መግዣ ስምምነት ለመፈራረም መገደዳቸውን የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል። የልዩ ሚሊሺያ አባላት የጠየቁት ጥያቄ ተመልሶላቸው ትእዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ፣ አቶ አብዲ የጀመሩትን ጥቃት ሊቀጥሉ እንደሚችሉ እነዚህ ወገኖች ይናገራሉ።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአካባቢው የተነሳውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመፍራት እነሱም በኦብነግ ላይ ለመዝመት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ህወሃት ራሱ የሚተማመንባቸውን የሰራዊት አባላት በኦብነግ ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ እንደላካቸው ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ለወራት የኢትዮጵያን የደህንነት አባላት ከአገሯ አስወጥታ የነበረችው ሶማሊላንድ ሰሞኑን ሁለት የደህንነት አባላት ወደ አገሯ እንዲገቡ ፈቅዳለች። ሶማሊላንድ በግዛቷ በተጠለሉ ኢትዮጵያውያን ላይ የህወሃት አገዛዝ ያለ ፈቃድ የሚወሰደውን እርምጃ እንዲሁም የመንግስቷን ተቃዋሚ መርዳቱ ያበሳጫት ሶማሊላንድ፣የደህንነት አባላቱ ከአገር እንዲወጡ ካዘዛች በሁዋላ፣ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን የጨመረ ድርድር በሁለቱ አገራት መካከል ሲካሄድ ቆይቷል።
ከአካባቢው ዜና ሳንወጣ በቅርቡ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የደህንነት ሰራተኞች በአብዛኛው የህወሃት/ኢህአዴግን የሶማሊያ ወረራ ሲቃወሙ ከነበሩ ጎሳቸው የተውጣጡ መሆናቸው ገዢው ፓርቲን ያሳሳበ ጉዳይ ሆኗል።
የአለማቀፍ ደጋፍ እንደጠበቀው ባለማግኘቱ ሰራዊቱን ከሶማሊያ በማስወጣት ላይ ያለው የኢህአዴግ አገዛዝ፣ በሶማሊያ ያለው የደህንነት መዋቅሩ እየፈራረሰ መምጣቱን ሲያሳስበው የቆየ ቢሆንም፣ አሁን በአዲሱ የሶማሊ መንግስት ውስጥ የተካከቱ አብዛኞቹ የደህንነት አባላት፣ የእርሱን የሶማሊያ ፖሊሲ ከሚቃወሙ ጎሳዎች መመልመላቸው ይበልጥ ስጋት ላይ እንደጣለው ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል።

የቀድሞ የአማራ ክልል የደህንነት ኃላፊ በርካታ ምስጢሮችን ዘረገፉ | ልደቱ አያሌውን ጨምሮ ማታ ማታ ስለሚታሰረውና ቀን ሰዎችን ስለሚያሳፍነው የግንቦት 7 ‘አባል’ የሚናገሩት አላቸው

ሁሉም ሊሰማው የሚገባው 

ሶስት የፖለቲካ ድርጅቶች ህዝባዊ ተቃውሞ እንዲባባስ አድርገዋል ተብለው ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑን ታወቀ

(ኢሳት) ሶስት የፖለቲካ ድርጅቶች ከአንድ አመት በፊት በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ እንዲባባስ አድርገዋል ተብለው ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑን ታወቀ።

ከቀናት በፊት በህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሲመረምር የቆየው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ሶስት የፖለቲካ ድርጅቶች ተቃውሞ እንዲቀሰቅስና እንዲባባስ የተለያዩ አስተዋጽዖ አድርገዋል ሲል ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል። የኮሚሽኑን ሪፖርት ያቀረበው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበኩሉ ህዝባዊ ተቃውሞን አባብሰዋል በተባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ክስ እንዲመሰረት ሃሙስ ውሳኔን ሰጥቷል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሰማያዊ ፓርቲ እና የጌዲዮ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ክስ እንዲመሰረትባቸው የተወሰነ መሆኑን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

ኦፌኮ እና ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ህዝባዊ ተቃውሞዎች እንዲባባስ አስተዋጽዖ አድርገዋል ተብለው ህጋዊ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው የተወሰነ ሲሆን የጌድዮ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች በበኩሉ በጌዲዮ ዞን የዘር ግጭት እንዲቀንስ አድርጓል ተብሏል።

በሶስቱ ክልሎች ከተካሄዱ ተቃውሞዎች ጋር በተገናኘ 669 ሰዎች መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለፓርላማ አቅርቦ በነበረው ሪፖርት አመልክቷል።

ይኸው ሪፖርት ሃሙስ ለፓርላማ አባላት ለውይይት ቀርቦ እንዲጸድቅ የተደረገ ሲሆን፣ የፓርላማ አባላቱ በአብዛኛው ድምፅ ሶስቱ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲከሰሱ ድምፅ ሰጥተዋል። የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ዕርምጃው የፖለቲካ ፓርቲዎችን ህልውና በፍ/ቤት በመሰረዝ ህጋዊነታቸውን ያሳጣቸዋል።

መንግስታዊው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የፖለቲካ ድርጅቶቹን ተጠያቂ ከማድረጉ በተጨማሪ የሃይል ዕርምጃን ወስደዋል የተባሉ የጸጥታ አባላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መወሰኑ ይታወሳል።

ይሁንና ምክር ቤቱ ተጠያቂ እንዲሆኑ በተወሰነው የጸጥታ አባላት ላይ የሰጠው ትዕዛዝ የለም።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የሶስት ወር ዕርምጃ 699 ሰዎች መሞታቸውን ቢገልፅም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ግን በሪፖርቱ አለመካተቱንና ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ከተገለጸው ቁጥር በላይ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋምት ይገልጻሉ።

ኮሚሽኑ ጥናቱ ከሃምሌ 2008 አም እስከ መስከረም 2009 አም መሸፈኑን አመልክቷል። ይሁንና ከሃምሌ ወር በፊት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች  ህዝባዊ ተቃውሞዎች ሲካሄዱ እንደነበርና ከ100 የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን መንግስት በወቅቱ ማረጋገጡ አይዘነጋም።

ህዝባዊ ተቃውሞን ለመቆጣጠር መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን፣ የአዋጁ መውጣትን ተከትሎ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንን ከ24 ሺ በላይ ሰዎችም ለእስር መገደላቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች ሲገልጽ ቆይቷል።

አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራቶች እንዲራዘም መደረጉን እስራትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲባባስ ማድረጉን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይገልጻሉ።

Ethiopia: New trial for bloggers accused of encrypting messages flies in the face of justice

Amnesty International UK
Press releases

The Ethiopian Supreme Court’s ruling today that two bloggers who were facing terrorism charges under the draconian Anti-Terrorism Proclamation (ATP) should face a new trial for offences against the Constitution, including encrypting messages, flies in the face of justice, said Amnesty International today.Ethiopia's Zone9 bloggers says "thank you"

The court ruled that, although the prosecution did not provide sufficient evidence to support terrorism charges against Nathnael Feleke and Atnaf Birhane (members of the Zone 9 Bloggers Collective), it had presented enough to support charges of “provocation and preparation to commit or support outrages against the Constitution or the Constitutional Order.”

Muthoni Wanyeki, Amnesty International’s Director for East Africa, the Horn and the Great Lakes, said:

“Learning how to encrypt messages is not a crime, but a freedom protected under the right to privacy and freedom of expression.

“The court’s reasoning that the bloggers confession as to having taken training on ‘security-in-a-box,’ as well as on campaigning, monitoring demonstrations and leadership, demonstrates their malicious intention against the government is not only ridiculous, but also inconsistent with their human rights as guaranteed under the Ethiopian Constitution, as well as regional and international standards.”

Security-in-a-Box is a guide to digital security widely used by activists and human rights defenders.

Amnesty International calls on the Ethiopian authorities to immediately drop the charges against Nathnael Feleke and Atnaf Birhane.

Ethiopia Supreme Court says two Zone 9 bloggers should face incitement charges

zoneeeeee

New York, April 6, 2017–Ethiopia’s Supreme Court today ruled that two bloggers from the Zone 9 collective, previously acquitted of terrorism charges, should be tried instead on charges of inciting violence through their writing. If convicted of the charge, Atnaf Berhane and Natnail Feleke would face a maximum prison sentence of 10 years, according to the Addis Standard newspaper.

The court upheld the lower court’s acquittal of two other Zone 9 bloggers, Soleyana S Gebremichael and Abel Wabella. Today’s actions by the Supreme Court were a response to prosecutors’ appeal of the October 2015 acquittal of all four.

“We urge Ethiopian authorities to do the right thing and drop any further prosecution of Atnaf Behane and Natnail Feleke on charges relating to their work,” said Africa Program Coordinator Angela Quintal. “Today’s acquittal of two Zone 9 bloggers is a positive step, but there can be no celebration until this exhibition of legal harassment ends once and for all.”

Ethiopia ranked fourth on CPJ’s 2015 list of the 10 Most Censored Countries and is the fifth worst jailer of journalists worldwide, according to CPJ’s 2016 prison census. CPJ awarded Zone 9 an International Press Freedom Award in 2015.

ትናንት April 1, 2017 በጀርመን ሃገር በፍራንክፈርት ከተማ የእግር ጉዞ ተካሄደ

Public walking rally against the TPLF government: April 1, 2017, Frankfurt, Germany!

Reported by : Alemayehu Kidanewold

 የኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበራት እና በፍራንክ ፈርት ግብረ ሃይል ባዘጋጁት የእግር ጉዞ ብዙ ህዝብ በተገኘበት በትናንትናው

እለት April 1/2017 በጀርመን ሃገር በፍራንክፈርት ከተማ  ተካሂዱዋል::

እግር ጉዞው ዋና አላማ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ዘርፈ ብዙ በደሎች የሰብአዊ የመበት ጥሰቶች በአስቸኩዋይ እንዲያቆምና ለህዝቦች ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለማስገደድ ፣የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ፣ የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁ  እንዲነሳና ብሎም በቆሼ ላለቁት ንጹሃን ዜጎች የተስማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለመግለጽ ነበር::

0-02-05-b962624a4ea4c82da4c80d8900ab475ff2ca448e98f15fe7df8da72c99c4a052_full0-02-05-62fe01ccd48a574d42c4488bf232dc6a3b672f4913578f991e7319ceb74e6596_full

በመላው ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያን የተሳተፉበት ይህ ትይንተ ህዝብ ንጹሁን የኢትዮጲያን ባንዲራ ከፍ አድርጎ በማውለብለብና በከፍተኛ ስሜት እልህና ቁጭት የታሰሩ የተገደሉ ጀግናና ሰማእት ኢትዮጵያንን ፎቶዋቸውን በመያዝ አብዛኛው ተሳታፊም ጥቁር  ልብስ በመልበስ ይሄ አረመኔ አገዛዝ እያደረሰ ያለውን ፋሺስታዊ ጭካኔ ለአለም ህዝብ አሳይተዋል::

በእግር ጉዞው ላይ ካነጋገርናቸው ተሳታፊዎች መሃል ‘’ብሶቱን ለተናገረ ህዝብ ምላሹ በአጋዚ ጦር በጥይት መጨረስ የተያያዘውን ይህን ደም መጣጭ አውሬ በአስቸኩዋይ በቃህ ልንለው እንደሚገባ” አስተያየታቸውን ሰተዋል::

0-02-05-5f26c5a1da3395decfc9c81f271bf63ae48d6717062eb97712976d0ea37bf4ec_full0-02-05-a80b3aa15aa7a68350335bd64118bd24a4160da5c3e3cc4fa16ac82e8c9e63b2_full