Public walking rally against the TPLF government: April 1, 2017, Frankfurt, Germany!
Reported by : Alemayehu Kidanewold
የኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበራት እና በፍራንክ ፈርት ግብረ ሃይል ባዘጋጁት የእግር ጉዞ ብዙ ህዝብ በተገኘበት በትናንትናው
እለት April 1/2017 በጀርመን ሃገር በፍራንክፈርት ከተማ ተካሂዱዋል::
የእግር ጉዞው ዋና አላማ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ዘርፈ ብዙ በደሎች የሰብአዊ የመበት ጥሰቶች በአስቸኩዋይ እንዲያቆምና ለህዝቦች ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለማስገደድ ፣የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ፣ የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳና ብሎም በቆሼ ላለቁት ንጹሃን ዜጎች የተስማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለመግለጽ ነበር::
በመላው ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያን የተሳተፉበት ይህ ትይንተ ህዝብ ንጹሁን የኢትዮጲያን ባንዲራ ከፍ አድርጎ በማውለብለብና በከፍተኛ ስሜት እልህና ቁጭት የታሰሩ የተገደሉ ጀግናና ሰማእት ኢትዮጵያንን ፎቶዋቸውን በመያዝ አብዛኛው ተሳታፊም ጥቁር ልብስ በመልበስ ይሄ አረመኔ አገዛዝ እያደረሰ ያለውን ፋሺስታዊ ጭካኔ ለአለም ህዝብ አሳይተዋል::
በእግር ጉዞው ላይ ካነጋገርናቸው ተሳታፊዎች መሃል ‘’ብሶቱን ለተናገረ ህዝብ ምላሹ በአጋዚ ጦር በጥይት መጨረስ የተያያዘውን ይህን ደም መጣጭ አውሬ በአስቸኩዋይ በቃህ ልንለው እንደሚገባ” አስተያየታቸውን ሰተዋል::