Archive | May 2017

‘በፌዝ ቡክ’ መቀነጣጠስ እና መጀናጀን ካቆምንበት ቀጥለናል …lol

 

እፎይ ትምህርት ዓለቀ ተገላገልን…. አሁን ደሞ ወደ ፌስ ቡክ ቻት እና ጅንጀና እስኪ እንመለስ
ግን ምን እንደተሸወድኩ ታውቃላችሁ ጥናት ሰዓት ላይ ስልኬን አለማጥፋቴ እንዴት ሰው አምስት ደቂቃ ሃሳቡን ሰብስቦ ማጥናት ያቅተዋል? ልማድ ሆኖብኝ መልክት ተላከ አልተላከ እያልኩ እጄ እንዴት ይላቀቅ ደሞ ከኔ ራቅ አድርጌ ባስቀምጠው ድምጹ ቂው….! ሲል አሁንም አላስችል ይለኝ እና እጄን ሰደድ አቤት አቤት ያየሁት መከራ እኮ….
የፈተናዬን ውጤት እስከማውቅ ብጉዋጉዋም… እድሜ ለፌዝ ቡክ ጉዋደኞቼ እንደጉድ… ይጀነጀናል….

አሁንማ በቃ ማን ከልካይ አለበኝ እንዴት ቻት ማረግ እንዳማረኝ…. 😂😂

ኤደን አንድዋ የፌስ ቡክ ጉዋደኛዬ ነች በጣም አሪፍ ልጅ ነበረች ቀልድም ቁምነገርም ትችልበት ነበር … ነገር ግን ዛሬ ጽፌላት በሶስተኛው ቀን ነው መልሱ የሚመለስልኝ:: እሱንም እግዜርን ከፈራች ነው እንጂ በአምስት ቀኑም ሊሆን ይችላል… በፖስታ ብትልከው እንኩዋን ይህን ያህል መች ይቆይና…. ?! ሊያውም በዚህ ዘመን …
ምን ያህል ጉዋደኞች ቢኖርዋት ነው እንዲህ ቢዚ የምትሆነው…? ብዬ ለማየት ብሞክር ፌስ ቡክ ጀግናው

”እሱ ሚስጥር ነው ላንተ አይፈቀድም” …ሰላለኝ ለመገመት ተገደድኩ
አንድ ፎቶ ብትለጥፍ በስድስት መቶ ሰው በአንድ ቀን ላይክ በመደረጉ በርግጠኝነት ከአንድ ሺህ በላይ ተከታዮች ሊኖርዋት ይችላሉ በዬ ስለገመትኩ ጣቶቼን ወደ ዳጊ (ዳግማዊት) አዙሪያለሁ …! ሁሌ ወረፋ መጠበቁ ሰለቸኝ እኮ….Lol

ዳጊ… አቤት… ድምጽዋ ውይ ውይ ውይ ….ገዳይ ነው…! አቤት ቁም ነገርዋ ሊያውም ከጠለቀ እውቀት ጋር… ቁንጅናዋ ያው “ፎቶ ሾፕ ይሁን ኦርጅናል” ብቻ የቴዲ አፍሮን ”ያምራል ያምራል ቁንጅናሽ ያምምራል” ዘፈን ሁላ ያስጋብዛታል::…kkk

የኔ የገጽ ፎቶዬ የቡና ሲኒ ቡናው ተቀድቶና ጤናዳም ከጎኑ በመሆኑ አንድ ቀን ስለቡና በሜሴንጀር ስልክ ወሬ ጀመርን
ወይ ጉድ አውርታው አትጠግብም እኔ እንደውም ረጅም ሰአት ዝም ብዬ ስሰማት ደስ ይለኛል

”ይኁውልህ”
አለችኝ በዛ በሚያምር ድምጽዋ

”ኢትዮጵያ ከ አስረኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ወይም ለ 1100 አመታት ያህል የቡና ባህል አላት በአለም የመጀመርያው ነን::….. 28% (ፐርሰንት) ኢኮኖሚያችን በቡና ላይ ነው…:: 15 ሚሊዮን ዜጋ በስራው ላይ ተሰማርቶ የእለት እንጀራውን ያገኛል:: ነገር ግን ቡናው ከገበሬው ለፍቶ ደክሞ በትንሽ ዋጋ ወደ ፈልፋይ እና አጣቢ ይሸጣል:: ከዛ ወደ ውጭ የሚልኩ ነጋዴዎች እጅ ይደርሳል:: በመሃል ብዙ ሰው እጁን ሰለሚያስገባ ዋጋው ይወደዳል:: ይህ ደሞ የቡናው ውድ መሆን የሚገዛውን ሰው ውስን ሰለሚያደርገው ያደጉት ሃገሮች አይኖቻቸውን በጥራት እና በብዛት አምርተው በቅናሽ ወደሚሸጡ እንደ ዩጋንዳ ህንድ ኤንዶኔዥያና ብራዚል በማድረግ ላይ ናቸው:: ይህ ደሞ ለሃገራችን የወደፊት ኢኮኖሚ ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል አስበው…!!” አለችኝ ዳጊ

እውነትዋን ነው እኮ አልኩ በሃሳቤ ለምሳሌ አሜሪካ የጦር መሳርያ በ አመት ለሳውድ አረብያ 82 ቢሊዮን ዶላር እንደሸጠች ሌላውን ሳንቆጥር…. እንዲሁም ጀርመን ማሽኖችን መኪናዎች ኬሚካሎች የኤሌትሪክ ሃይል የህክምና መሳሪያዎችና መድሃኒቶች ባቡር በ አመት 1.5 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚያስገቡ መረጃዎቻቸው ያሳያል:: ሆ …….ታድያ እንዴት አያድጉ?

ዳጊ ቀጠለች ”የተማረው የሰው ሃይል ክፍል ስደትን ወዶም ሆነ ተገዶ በመምረጡ ሃገራችን በተወሰነ ነገር ላይ መፍጨርጨሩ በዙም ለውጥ ሊያመጣ አላስቻለውም ዘመናዊነት እና ከጊዜው ጋር አለመራመድ በዙ ወደሁዋል እንድንወርድ አደርጎናል”
እያለች ረጅሙን ነገር በአጭሩ ቁልጭ አርጋ አስቀመጠችው
ወይ ዳጊ….
እና አንቺ በግል ምን ታስቢያለሽ ታድያ?… ብዬ ጠየኩዋት
”ለትምህርት ነበር ውደ ውጭ የወጣሁት አሁን ጨርሻለሁ እዚህ መስራትና መኖር እችላለሁ እነሱም የተማረ ሰው ማማለል እና መሰብሰብ ከዛም አፍሪካን ወደሁዋላ አስቀርተው እራሳቸውን ማሳደግ ይችሉበታል እኔ ግን ለሃገሬ አስፈልጋታለሁ እኔም ሃገሬን እፈልጋታለሁ!!”
በመሃል ረጂም ሰከንድ ዝም አለች እና
”በሰው ሃገር እድሜ ልክ ድመት ሆኖ ከመኖር በሃገሬ አንድ ቀን አንበሳ ሆኖ መሞት እመኛለሁ” አለችኝ

ዳጊ አንድ ሳትሆን ሺህ ቢሆኑ ምን ነበረበት… ብዬ ተመኘሁ ይህን ባወራን በወሩ ከኢትዮጲያ ሆና ጻአፈችልኝ እንዲህ ይላል
”ኢትዮጵያን ደምና ጦርነት አይቀይራትም በደም ብትቀየር ኖሮ እነ አጼ ቴዎድሮስ ያፈሰሱላት ደም እስካሁን በቀየራት ነበር በአሁኑ ዘመን ኢትዬጵያን የሚቀይራት አንድነት ሰላም ፍቅር እና ዋናው ደግሞ ታሪክን ማውራት ብቻ ሳይሆን ደም እስክንተፋ መስራት ነው:: ያኔ ሃገር ትቀየራለች”
እኔም በውስጤ የፈተና ውጤት እንግዲህ ይምጣና ዳጊ ጋር አንዱ የኢትዮጵያ ክፍል እንገናኝ ይሆናል::

እስከዛው ግን የፌስ ቡክ ጅንጀናው ይቀጥላል….😂😂😂

facebook

Ethiopia Court Found Former Senior Opposition Figure Yonatan Tesfaye Guilty of Terrorism Charges

Addis Standard

Yonatan Tesfaye charged after anti-govt Facebook posts

Addis Abeba, May 16, 2017 – The Federal High court fourth criminal bench has today passed a guilty verdict against Yonatan Tesfaye, former opposition Blue Party public relations head.

Yonatan was first arrested in December 2015, barely a month after the first wave of a year-long #Oromoprotests erupted.  He was held incommunicado during the pre-trial weeks and was subsequently charged in May 2016 under Ethiopia’s infamous anti-terrorism proclamation (ATP).

Yonatan has been defending the charges against him since then. The charges of ‘encouragement of terrorism’, stipulated under article six of the ATP, were largely drawn from his Facebook activism during the protests. According to article six of the ATP, “Whosoever publishes or causes the publication of a statement that is likely to be understood by some or all of the members of the public to whom it is published as a direct or indirect encouragement or other inducements to them to the commission or preparation or instigation of an act of terrorism…” is subject to terrorism charges.

He had presented several defense witnesses, including prominent opposition party leaders from the Oromo Federalist Congress (OFC), Bekele Gerba and Dr. Merera Gudina, who are in jail at the time of their testimony fighting charges of terrorism and multiple criminal charges respectively, and journalist Eskendir Nega, who is serving 18 years in prison for terrorism-related charges.In addition, Yonatan’s close friend Ephrem Tayachew, his father Tesfaye Regassa, and his sister Gedamnesh Tesfaye as well as academicians from the Addis Abeba University (AAU), including the outspoken philosopher Dr. Dagnachew Assefa and Dr. Yaqob Hailemariam have all appeared in court to testify in defense of Yonatan’s innocence.

However, this morning the court in its verdict overruled all defense testimonials by upholding prosecutors’ accusations. Yonatan’s sentencing is adjourned to May 25.

Yonatan could face from ten to 20 years rigorous prison term in a federal prison; however, the court ruled that he can appeal for a minimum sentence.

***According to new information Addis Standard received, after the sentencing is handed over, Yonatan’s defense team, led by his lawyer Shibiru Belete, is planning to object to the verdict and appeal for the charges to be reduced to criminal charges. 

የቴዲ አፍሮ ሳምባሬ……

የቴዲ አፍሮ ሳምባሬ……

መጻፍ ባልፈልግም ያጽፋል:: አስተያየት ሰጥቼ ባልውቅም ዛሬ ግን ግድ ሆ…..

አቤት ያገሬ ልጅ ትንሽ ጋደድ ብትል ገዝግዘው ጣሉህ? እረ ስንቱን ገዘገዝን? እረ ስንቱን ጥለን ቀበርን?

ወትሮውንስ ማመዛዘን ማድነቅና ማክበር የት ለምዶብን? እስቲ እዩዋቸው ትናንት የት ይደርሳሉ የተባሉትን በደካማ ጎናቸው እየገባን በቀንና በለሊት ሚስጢራቸውን ስንፈለፍል ከርመን በመጨረሻም ዳሽንን ከሚያክል ተራራ ላይ ወርውረን እጃችንን ረገፍ ረገፍ አድርገን ደሞ ሌላ ይሚጣል ፍለጋ የምንቃርም….

እንደውም የሚመስለኝ የምናደንቀውም በራሱ ጥረት እላይ ስለወጣና ከመሬት ለማፍረጥ ፈልገን እጃችን ስላልደረሰበት ነው እንጂ ከኛ በላይ የወደቀ ሰው እንደማየት የሚያስደስተው ማን አለ….?

ወይ አንሰራ ወይ አናሰራ ወይ አንማር ወይ ሰው እንዲማር እድል አንሰጥ አለሁ ማለት ብቻ ጉራ ብቻ ቲኒሽ ብጣቂ እውቀት…. በሰው ስቃይ መደሰት….ቲሽ…..!!

ለምን እንደወደድነው እና እንደምናደንቀው የማናቅ ፥ ለመጥላትም ደሞ የሚያመዛዝን ጭንቅላት የሌለን ፥ ስህተት ሰራ ከተባለ ስህተቱን እንጂ ምክንያቱን መስማት መመርመር የማንፈልግ እረረረረረረረረ….. ”እረ እዚህ ሰፈር ወሬ አለ ኑ…….” ስንባል ግርርርርርር…… ብለን የምንግተለተል …ቀሽም…. ቀልቀሎ ስልቻ….

ቆይ ባይዘፍኑ ቢቀርባቸውስ ፣ ባይጽፉስ ቅኔን ባይቀኙ ፣ ጥበብ የት አባትው ባይጠበቡላትስ ፣ ሃገርን ለማሳደግ ደፋ ቀና ባይባልስ ፣ የምን ፖለቲካ እኛን ብሎ ፖለቲከኛ ፣ እረ ባይሮጡና በኦሎምፒክ አደባባይ ሰማችንን ባያስጠሩስ አርፈው ከጉዋዳቸው ቢወተፉስ ፣ ይሄ ሁሉ ውርጅብኝም ባልደረሰባቸው እረረረረረረ…….

ወይኔ ቴዲ አፍሮዬ ይሄ ሁሉ የሚያደንቅክ ሰው አሁን ካልሞትልነት የሚልህ ሰው እንዳይወርድ ሆኖ የተሰቀለ”…. የሚልህ ሰው ክቦክቦክቦእላይ ያደረሰህ ሰው…… ብቻ……… አንዲት ጉድፍ ትገኝብህ፥ ያኔ ነው እንግዲህ ማየት…..!

ጋሽ ስብሃት እንዳለው ብቅ ብትል ይመቱሃልእውነቱን ነው ምሽግ ውስጥ ብንሸሸግማ ማን አባቱ ይነካንና?

የሚሰራ እጅ እንደሚቆሽሽ ፣ የሚሮጥ ጉልበት እንደሚዝል ፣ ቀንስ አንስቶ ቀንስ እንደሚጥል መቼ ተረዳንና??

የቴዲ አፍሮ ሳምባሬ ሙዚቃ ቀጥሎዋል…….

ክብር ለሚሰራ ለሚፈጥር እና ሃገርን ለመቀየር ለሚደክምና ለሚሳሳት!!!

አሌክስ ኢትዮጵያ

teddy afro

አናኛቱ

አናኛቱ

(በእውነተኛ ታሪክ ላይ እና ከቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም በአንደኛው ዘፈን ላይ የተመሰረተ ልብ ወለድ)

የልቦለዱ ገጸባህሪያት፡ አኖሌ….(ወንድ…..ቦይ ፍሬንድ)….ጊፍቲ..(የአኖሌ እጮኛ…ገርል ፍሬንድ)…ኢጆሌ(አኖሌ መኖሪያ ቤት አካባቢ የማይጠፋ አራዳ የለገጣፎ ልጅ …አንዳንዴ ለአኖሌ የሚላላክ ሲሆን ዋና ስሙ ናፍያድ ይባላል)…አለማየሁ (የአጋዚ ወታደር…..ልቦለዱ መሃል ላይ ክፉ ስራ የሚሰራ)… ..……ወ/ሮ ሃፍቷ(ልቦለዱ መሃል አሳዛኝ ነገር ሲከሰት ጉድ ጉድ የሚሉ ሴትዮ)….ቴዲአፍሮ…..(ዘፈኑ በአሁኑ ሰአት የአለም የሙዚቃ ቢልቦርድን በአንደኝነት እየመራ ያለ ሙዚቀኛ….በገሃዱ አለም የሚገኝ)…….አንዲማኛ (የእውነት ስሙ አንዱአለም በውቀቱ ገዳ ….የልቦለዱ ደራሲ….በገሃዱ አለም የሚገኝ እና በስነጽሁፍ ታሪክ ከዘፈን ተነስቶ ልቦለድ የጻፈ የመጀመሪያው አትዮጲያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን፣ጉራ ብቻ )….የኦሮሞ መብት(በልቦለዱ መሃል የሚነሳ ጥያቄ …በገሃዱ አለም የማይገኝ)
እሺ ወደ ልቦለዱ እንግባ
የልቦለዱ መግቢያ፡…….ቀኑ ጸሃያማ ነው፡፡(እንደማንኛውም የኢትዮጲያ ልብወለድ ቀኖች ማለት ነው)፡፡
ዛሬ የአኖሌ እና የጊፊቲ የፍቅር ጥንስስ የተጀመረበት የመጀመሪያ አመት አኒቨርሰሪያቸውን የሚያከብሩበት ቀን ነው፡፡ልክ የዛሬ አመት በወርሃ መስከረም ቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ በኢሬቻ በአል ነበር አኖሌ ጊፍቲን ያያት፡፡በበአሉ ላይ እንደተገኙት እንደአብዛኛው የኦሮሞ ጉብላሊቶች የሚያምር የባህል ልብስ ለብሳ ደምቃለች፡፡ ……”አከሚቲ በሬዲ !ወይኔ እንዴት አባቷ ታምራለች?!” አለ አኖሌ ..ገና እንዳያት…….
ረጅም ጥቁር ለስላሳ ጸጉሯ ከትከሻዋ ላይ ፍስስ ብሏል፡፡ግምባሯ ላይ በጨሌ የተሰራ የባህል ጌጥ አድርጋለች፡፡አንገቷ እና የእጅ አምባሯ ላይ ያደረገችው ጌጥ የሆነ እዚህ ጋር ስሙ የማይጠቀስ የፖለቲካ ፓርቲ አርማ ይመስላል፡፡ከአንዲት ጓደኛዋ ጋር እየተላፋች ትሳሳቃለች…..ስትስቅ ደግሞ የበለጠ ታምራለች….ልክ ስሟ የተጠራ ይመስል ድንገት ወደ አኖሌ ዞር አለች….አይናቸው ሲገጣጠም ድንግጥ ብላ አይኗን ስብር አደረገች…..አኖሌ በመዶሻ አናቱን የተመታ መሰለው….
አንባቢ ሆይ የአንተንም የእኔንም ጊዜ ላለመሻማት አኖሌ ፍቅር ሲይዘው የሆነውን እና የተሰማውን ነገር ሌላ ግዜ ካነበብካቸው የፍቅር ድርሰቶች ወስደህ ታሪኩን አሟላ..…..እኔን ብቻ አታድክመኝ…….
እሷስ!?
የዛን ቀን በአሉን አብረው አከበሩ፡፡ ዱከም ድረስ ምንም ድካም ሳይሰማቸው ድሮ እንደሚተዋወቁ ፍቅረኞች እጅ ለእጅ ተያይዘው ወክ አደረጉ …ስለ ኦሮሞ ባህል፡ መብት ፡ትግል፡ ወዘተ ብቻ ስለ ብዙ ጉዳዮች ተወያዩ….ያው አንባቢ እንደጠረጠርከው …እሷም እራስምታት የሚያስይዝ ፍቅር ያዛት….እዚህ ጋር አንዳንድ ጨቅጫቃ አንባቢ” የልጅቷ ጓደኛስ የት ሄደች?!” ብሎ እንደሚጠይቅ ይገባኛል….ጭቅጭቅ ነው ንባብ ነው የያዝከው የኔ ወንድም?!…..ጓደኛዋ ቅድም በድርሰቱ ውስጥ የተጠቀሰችው “ጊፍቲ ከጓደኛዋ ጋር እየተላፋች ትሳሳቃለች” ለሚለው ዓ/ነገር ማሟያ እንጂ እኔ እያንዳንዱን ገጸባህሪ አንዴ ጠቅሼዋለሁ ብዬ ወደ ቤቱ የማስገባት ግዴታ ያለብኝ አይመስለኝም፡፡
የልቦለዱ መሃል፡
ጊፍቲና አኖሌ አመቱን ሙሉ በፍቅር እብድ አሉ፡፡እንደውም በተገናኙ በዘጠነኛው ወር ጊፍቲ ጓዟን ጠቅልላ ለገጣፎ ከሚገኘው የአኖሌ የሚያምር ቪላ ገባች፡፡በየስራ ቦታቸው ተለያይተው ሲውሉ ቢያንስ አስር ግዜ ይደዋወላሉ….ከስራ እንደወጡ ያለምንም ወለም ዘለም ይገናኛሉ…ወክ ያደርጋሉ ……ፊልም ያያሉ……አኖሌ መጽሃፍ የሚያነብ ከሆነ ጊፍቲ ሆዱ ላይ ትተኛና የምትወዳቸውን ፊልሞች ቻናል እያቀያየረች ታያለች……ሁለት ሰአት ሲሆን እና እለቱ የእሱ እራት የማቅረብ ቀን ሲሆን አኖሌ መጽሃፉን ይዘጋና …ወደኪችን ይገባል….”ንግስት ሆይ ሺ አመት ይንገሱ” ይልና ልክ እንደ ቤተመንግስት አገልጋይ ወገቡን እያጠፈ ጠረጴዛው ላይ ሰሃኖቹን ይደረድራል…ጊፍቲ ትፍነከነካለች…… የሷ ተራ ከሆነም ተመሳሳይ መስተንግዶ ከልዩ አክብሮትና ፍቅር ጋር ይቀጥላል……አንዳንዴ ደግሞ በረንዳቸው ላይ ቁጭ ይሉና ከአርቲስት ጎረቤታቸው ቤት አልፎ አልፎ የሚሰማውን ማራኪ የፒያኖ ድምጽ ያጣጥማሉ…..ጎረቤታቸው 365 ቀናት ሙዚቃ መስራት የማይሰለቸው…..ቴድሮስ ካሳሁን የተባለ ተወዳጅ የሙዚቃ ሰው ነው፡፡ከእነሱ በኋላ ነው ከእነሱ አጠገብ ያለውን ቤት ገዝቶ ለገጣፎ የገባው፡፡ትሁት ጻባዩ እና እራሱን አለማካበዱ ግርም ይላቸዋል…..ካለ ኦሮምኛ ዘፈን የማታዳምጠው ጊፍቲ “ይሄ ልጅ በዚሁ ከቀጠለ አንድ ቀን አሊቢራን ይተካል!” ትላለች…አኖሌ በዚህ አባባሏ ሁሌ ፈገግ ይላል፡፡
የልቦለዱ መገባደጃ
የ2009 ኢሬቻ በአል ለሁለቱ ፍቅረኞች የመጀመሪያ አኒቨርሰሪያቸውን የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ ከሌሎች ኢሬቻዎች በተለየ ጉጉት እየጠበቁት ቆይተው እነሆ ዛሬ ደረሰላቸው….
በሀገሪቱ ውስጥ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሰሞኑን በተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት መነሻ በበአሉ ላይ ችግር ይከሰታል በሚል መንግስት መትረየስ፡ታንክ ፡መድፍ እና ሄሊኮፕተርን ጨምሮ አንድ ከጅቡቲ ከፍ ከሩዋንዳ ዝቅ ያለችን አነስተኛ ሀገር ለመውረር የሚያስችል የተሟላ ጦር በስፍራው አስፍሯል……..
ከሁሉ የሚያሳዝነው ግን ከበአሉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ አኖሌ ጂም ውስጥ ስፖርት ሲሰራ አደገኛ የስር መዞር እግሩ ላይ ስላጋጠመው…እንኳንስ ሆራ አርሰዲ ለመሄድ ከቤት ወደ ደጅ ለመውጣት እንኳ የሰው ድጋፍ የሚሻ ሆኖ ቁጭ ማለቱ ነበር….….ጊፍቲ የፈለገ ቢሆን ከሆራ አርሰዲማ አልቀርም ብላ ከዛች የድሮ ጓደኛዋ ጋር በጥዋት ከአምናው እጥፍ አምሮባት ወደ ደብረዘይት አቀናች…….
“ስልክሽን ደግሞ እንዳታጠፊ ፍቅር! “አላት ከቤት ስትወጣ…ግምባሯን ሳም አደረጋትና “ኦፍ ኤጊ “አላት በድጋሚ………
ከቀኑ 9 ሰአት ሆኗል……
አኖሌ በአንድ እጁ ምርኩዝ ተደግፎ ጊቢ ውስጥ ይንጎራደዳል….ከቢሾፍቱ አካባቢ የሚሰማው ዜና መልካም አይደለም……የጊፍቲ ስልክ ይጠራል የሚያነሳው የለም………ሆዱ ተሸበረ…….
ጎረቤቱ ቴዲ አፍሮ ቱታ ለብሶ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ ሁል ግዜ የዘፈን ግጥም የሚጽፍበትን ቡኒ ክርታስ ይዞ ቡዝዝ ብሎ ደጅ ደጁን ይመለከታል……የእሱንና የአኖሌን ቪላ የሚለየው አጭር የሚያምር የእንጨት አጥር ነው፡፡
“አኖሌ ማልታቴ!?”….አለ ቴዲ ….አኖሌ ቴዲን ኦሮምኛ እያለማመደው ሲሆን ለዚህ ውለታው ቴዲ አኖሌን አልፎ አልፎ ፒያኖ ያስተምረዋል፡፡
“ጊፍቲ ቢሾፍቱ ጥዋት ሄዳ እስከአሁን አልተመለሰችም ….. ስለአካባቢው የሰማኸው ነገር አለንዴ ?ስልኳ አይሰራም! ምክንያቱን ለማወቅ በጣም ተጨንቂያለሁ….ደግሞ ስተዘገይ ሁሌ እሰጋለሁ….”አለ አኖሌ …..
“አይዞህ ምን አትሆንም ወይ መታም ይሆናል! ” አለ ቴዲ ፡፡በቢሾፍቱ ግርግር ተነስቶ ቀላል የማይባሉ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ጭምጭምታው የደረሰው ቢሆንም ጭንቀቱን አኖሌ እንዲያውቅበት አልፈለገም…..
“አረ ቴዲዬ ልቤን ግራ ገባው……ላያት ከቤት እደጅ ስንቴ ገባሁ ስንቴ ወጣሁ…”አለ…..አኖሌ በጭንቀት…
“ወይ አንዱን ልጅ ልኬ ባረፍኩኝ ከስጋት …..ቀርታስ ቢሆን ሄዶ ከመንገድ ማን አያት……”አለ አኖሌ በድጋሚ…..አሁን የተናገረው ለቴዲ ይሁን ለራሱ ግልጽ አይደለም……
“ያንን ልጅ ላከው……”አለ ቴዲ ከአጥር ውጭ ወደ ቆመው ጩጬ እየጠቆመ….
“…..ኢጆሌ እስቲ መንገዱን እይና ተመለስ” አለ አኖሌ ጮክ ብሎ…… ከድጅ የቆመው ልጅ “ማንን?” ብሎ መጠየቅ አላስፈለገውም…….እየበረረ ሄደ…..
ሰአታት አለፉ ……ቴዲ አኖሌን ማጽናናት ከሚችለው በላይ ሲሆንበት እቤቱ ገባና መተከዣው ፒያኖ ላይ ቁጭ አለ….ውስጡ ተረብሿል…..ስልኩን አነሳና የፌስቡክ አካውንቱን ከፈተ…..የሚያያቸው ገጾች በሙሉ በቢሾፍቱ የተፈጀውን ህዝብ ፎቶ ይዘዋል….ብላቴናው ልቡ በሀዘን ስብር እንዳለ…አለፍ አለፍ እያለ….የሚዘገንኑትን ፎቶዎች ማየት ቀጠለ….ድንገት አንድ ፎቶ ላይ አይኑ አረፈ…..ሰውነቱ ሽምቅቅ አለ…በአንድ የገደል ጫፍ ላይ በዛ ያለ የወጣቶች እሬሳ ይታያል….በጉልህ ከሚታዩትና እንደዋዛ በአቧራው ላይ ክልትው ካሉት ወጣቶች ውስጥ የአንደኛዋን ውብ ወጣት ፊት …….ቴዲ በደንብ ይለየዋል……ጣቶቹ በደመነብስ የፒያኖውን ቁልፎች እየነካኩ ከእያንዳንዱ ምት ጋር የእምባ ዘለላዎች አኩል መንጠባጠብ ቀጠሉ…….

መታስ ቢሆን ማን አያት
ቀርታስ ቢሆን ማን አያት
ጠፍታስ ቢሆን አናኛቱ…………….
.
.
የዚህ ጽሁፍ መታሰቢያነቱ በእለቱ እንደዋዛ ለተጨፈጨፉት የኦሮሞ ወጣቶች ይሁንልኝ፡፡
ምንም ቢሆን ምንም
ይመቻችሁ፡፡

teddy

የወያኔ የዝርፊያ ድርጊት – በኤርምያስ ለገሰ የመለስ ልቃቂት

ይገረም አለሙ

አዩትና ልቡ እንደሞተበት
አባቱ ቀየ ላይ ወርደው ጠመዱበት

የኤርምያስ ለገሰን የመለስ ልቃቂት መጽኃፍ እያነበብኩ ነው፡፡ የወያኔ የዝርፊያ ድርጅቶችን አይነትና ብዘት በተለያየ ግዜ በተለያየ መንገድ እየተነገረም እየተጻፈም ያውቃናቸው ቢሆንም ይህን ያህል ዝርፊያ መፈጸማቸውን የሚያውቅ ብዙ  ሰው የነበረ አይመስለኝም፡፡ ኤርምያስ የካድሬነት ቆይታውም ሆነ የኮሙኒኬሽን ምኒስቴር ዲኤታነቱ  ዘራፊዎቹን ድርጅቶች በቅርብ ለማወቅ ያስቻለው በመሆኑ የሚያስነብበን በመረጃ እና ማስረጃ የተረጋገጠ እውነት ልብ ያቆስላል፡፡ ከወያኔዎቹ ድፍረት የእኛ ዝም ብሎ ሀገር ማዘረፍ ጥያቄ ያጭራል ቁጭት ይፈጥራል፡፡ ግና እኛ ከህውሀት በተቃራኒ የቆምን ነን የምንል ወገኖች ከአንድ ሳምንት የሚያልፍ ቁጭት፣ ንዴት፣ ምሬት፣ ወዘተ አያውቀንም እንጂ፡፡Yemeles Likakit book cover

አቶ ኤርምያስ የገለጸውን የወያኔ ዘረፋ ሳነብ “አረሱት መተማን የእኛን የእኛን እጣ፣ አረሱት እራያን የእኛን የእኛን ዕጣ፣ እነርሱ ምን ያርጉ ከእኛ ወንድ ሲታጣ” የሚለው ቀረርቶ ታወሰኝ፡፡ በትንሽ በትንሹ አንድ ሁለት እያሉ ሞከሩ፣ አዩን፣ ገመቱን፣ ምንም የተቃውሞ ምላሽ ስላልገጠማቸው የዘረፋውን አይነቱንም ስልቱንም አሳድገው ቀጠሉ፤ ዝርፊያው ጎልቶም ጎልብቶም ሲታይም ከአንድ ሰሞን ጫጫታ ያለፈ ነገር አልገጠማቸውምና  “አዩትና ለዩትና ልቡ እንደሞተበት፣ አባቱ ቀየ ላይ ወርደው ጠመዱበት” እንደሚባለው የሀገሪቱን ሀብት በሙሉ በማግበስበስ እንድም ወደ ትግራይ ሁለትም ወደየኪሳቸው ማድረጉን ተያያዙት፡፡ ሰውየው “ሚስትህ አረገዘች ወይ ቢሉት፣ ማን ወንድ ብላ አለ እንደሚባለው ማንን ፈርተው ምንስ አስፈርቷቸው ዝርፊያውን ያቁሙ!

የአቶ ኤርሚያስ የመለስ ልቃቂት መጽኃፈ እንደሚነግረን ከዘራፊው ህውሀት በላይ አዘራፊዎቹ ለጌታ አደሮች ትልቁን ድርሻ ተጫውተዋል እየተጫወቱም ነው፡፡ እነርሱ መቼም አንዴ ህሊናና ሆዳቸው ቦታ ተለዋውጧልና ምን ተባለ ምን ላይሰማቸው ይችላል፡፡ እነዚህ በስም ተጠቅሰው፣ ጸያፍ ምግባራቸው በማስረጃ ተደግፎ የተገለጸ ሰዎች ሚስቶችና ልጆች ይህን መጽኃፍ ሲያነቡ ምን ይሰማቸው ይሆን? የልጅና የሚሰት ማፈሪያ ከመሆን ፈጣሪ ይጠብቀን፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሀገራችን እውን ሆኖ የህግ የበላይነት ሊሰፍን ከቻለ የአቶ ኤርምያስ መጽኃፍ ወንጀለኞችን ለመለየትና ለወንጀላቸውም መረጃና ማስረጃ ለማሰባሰብ መንገድ መሪ ነው ፡፡

ይህን የሚያህል ህውኃቶች ኢትዮጵያን እየጋጡ ሳያላምጡ የሚውጡበትን ወንጀል የፖለቲካ ድርጅቶች በዝምታ መመልከታቸው ከተናገሩም ብለን ነበር ለማለት ያህል መሆኑ ያስገረመው ኤርምያስ በገጽ 425 ላይ “ታዲያ ኩባንያዎችን በተመለከተ በተቀዋሚ ፓርቲዎችም ሆነ አመራሮቻቸው ዘንድ “ተከድኖ እየበሰለ” ያለው ጥያቄ ምንድን ነው? ይህ በግልጽ መመለስ ያለበት ግን ደግሞ በከፍተኛ ፍራቻ የማይገለጠው ቁም ነገር በእነዚህ ፋብሪካዎችን የንግድ ተቋማት የትግራይ ህዝብ ተጠቅሟል ወይ? የትግራይ ህዘዝብ ጥቅም እያገኘ እንዳልሆነ ለምን ራሱ ምስክርነት አይሰጥም የሚለው ሆኗል፡፡ ርግጥም መጠቀም ማለት ምን ማለት ነው? እውነት ትግራይ ለምታች ወይ? ተጠቅማለች ወይ? የሚሉት ጥያቄዎች ግልጽ ምላሽ የሚያሻቸው ናቸው፡፡ እየተነገረ ያለው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በሁሉም ዘርፍ በሞኖፖል የየዘ ድርጅት ስለሆነ በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጠ ድርጅትም ሆነ በህዝቡ እይታ አቋማቸው መታወቅ ይኖርበታል፣”  ይላል፡፡

የፖለቲከኞቹ ዝምታ አጠያያቂ፣ አቋማቸው መታወቁም አሰፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታ ነው፡፡ ነገረ ግን ኤርምያስ በስፋትና በግዝፈት ያነሳውን ዘረፋ ከትግራይ መጠቀም አለመጠቀም ጋር አያይዞ ጥያቄ ማንሳቱ ጉዳዩ የሚያሳንሰውም ዋናውን አቅጣጫ የሚያስተውም ሆኖ ታየኝ፡፡ ይህን ለማሳየት በ1992 ምርጫ ክርክር ወቅት ስለ እነዚህ ድርጅቶች የተባለውን ማስታወሱ የሚጠቅም ይሆናል፡፡በወቅቱ የእነዚህ ድርጅቶች ጉዳይ በፖለቲካ ፓርቲዎቸ ዘንድ በስፋት ይነሳ ነበር፡፡ በተለይም በወቅቱ አዲስ የተመሰረተው ኢዴፓ ዋንኛ የመከራከሪያ አጀንዳ አድርጎ ይዞት ነበር፡፡ ታዲያ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ በነበረ የክርክር መድረክ ጉዳዩ ሲነሳ በኢህአዴግ በኩል በትጥቅ ትግል ወቅት ያፈራነው ሀብት ነው መነሻው፤ ሥልጣን ስንይዝ ምን እንዳረገው እንበትነው፣ እንከፋፈለው ወዘተ የሚል የብስጭት ምላሽ ሲሰጥ፤ ከተቀዋሚው ወገን እኛ ህውሀትን የምናውቀው ጠመንጃ ይዞ ዱር ቤቴ ብሎ መዋጋቱን እንጂ በንግድ ስራ መሰማራቱን አይደለም፣ድርጅቶቹ የተመሰረቱት ጫካም እያላችሁ ወደ አዲስ አበባማ ስትጓዙ መንግስትም ከሆናችሁ በኋላ ከህዝብ በዘረፋችሁት ንብረት ነው፡፡የሚል ምላሽ ተሰጠ፡፡

በቀጣዩ ቀን ኢህአዴጎች ትንሽ የቅርጽ ለውጥ አድርገው፡ ድርጅቶቹ የህዝብ ሀብት ናቸው፣ የትግራይ ህዝብ፣ የአማራ ህዝብ የኦሮሞ ህዝብ፣ የደቡብ ህዝብ ንብረት ናቸው የሚል መከራከሪያ ይዘው ቀረቡ፤ ከተቀዋሚው ወገን ለዚህ የተሰጠው ምላሽ በመዝጋቢው መስሪያ ቤት ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በተጠቀሱት ስሞች የህዝብ ንብረት ተብሎ የተመዘገበ ድርጅት የለም የሚል ነበር፡፡ በዚህ ግዜ አንድ  ከነገረ ሥራው ጉዳዩ ያልገባው መሆኑ የሚያስታውቅ የኦህዴድ ካድሬ በንዴት ስሜት በድንገት ከመቀመጫው በመነሳት የኦሮሞ ህዝብ ንብረት የሚባል የለም ብሎ ሲናገር አዳራሹ በሳቅ ተሞላ፡፡

በሶስተኛው መድረክ  አቶ በረከት ተገኘና ድርጅቶቹ ለትርፍ የማይሰሩ፣ መንግስትና የግል ባለሀብቶች ሊሸፍኑት የማይችሉትን የልማት መስክ የሚሸፍኑ ኢንዶውመንቶች ናቸው፡፡  የማን ናቸው ምንድን ናቸው የሚለው ላይ ማተኮሩ ምን ይጠቅማል፤ ምን እየሰሩ ነው የሚለውን ማየቱ ነው የሚሻለው ወዘተ በማለት ድርጅቶቹ ሰሩት እና እየሰሩ ነው ያለውን በመዘርዘር አዲስ መከራከሪያ አቀረበ፡፡ተቀዋሚዎችም ከህውሀት ድርጅቶች አንዳቸውም በኢንዶውምነት ስም እንዳልተመዘገቡ፤ተግባራቸውም ከዚህ የራቀ መሆኑን፣ ሁሉም አትራፊ ብቻ ሳይሆኑ የግል ባለሀብቱን እየተጋፉ ከገበያ የሚያስወጡ እንደሆኑ ወዘተ በመጥቀስ ተከራከሩ፡፡

የማን ናቸው እንዴት ተመሰረቱ፣ የሚለውን ትታችሁ ምን እየሰሩ ነው ብሎ መጠየቁ ነው የሚበጀው የሚለው የበረከት አቀራረብ የህውኃትን አቅጣጫ የማስቀየሪያ የተለመደና እስካሁንም የቀጠለ አካሄድ ያሳየ ነበር፡፡ ትኩረት ማስቀየር፣ አቅጣጫ ማስለውጥ አንዱን ለማድበስበስ ሌላ አጀንዳ መስጠት የተለመደ የወያኔ ተግባር ሲሆን አብዛኛው ተቀዋሚም ይህን ለምዶ ወያኔን ተከትሎ ይነጉዳል  በሚያቀብለው ኳስ ይጫወታል  እንጂ ነገሮችን አዋጭና ወያኔን መፈናፈኛ ማሳጣት በሚያስችል መልክና መንገድ ማስኬድ አይችልም፡፡ ለዚህም ነው ከዛ በኋላ የፖለቲካ ድርጅቶች በወያኔ የዘረፋ ድርጅቶች ጉዳይ አቋም ይዘው ሲናገሩም ሆነ ሲጠይቁ ያልተሰሙት፡፡

በእነዚህ ድርጅቶች የትግራይ ህዝብ ተጠቅሟል አልተጠቀመም የሚል ጥያቄ በአብይነት ሲነሳ ከ15 ዓመታት በፊት  በረከት አትንኩት ያለውን ዋናውን የድርጅቶቹን ማንነት፣ ምንነትና እንዴትነት ጥያቄ ወደ ጎን ማድረግና ወያኔ በሚፈልገው ስልት መጫወት ይሆናል፡፡እውነታው ይህን አያሳይም እንጂ በእነዚህ ድርጅቶች የትግራይ ህዝብ ተጠቅሟል አልተጠቀመም ለሚለው ጥያቄ ምላሹ አዎ ተጠቃሚ ነው የሚል ቢሆን ድርጅቶቹ ተቀባይነት ሊኖራቸው ነው ማለት ነው? አይመስለኝም፡

መነሳት ያለበት ጥያቄ ሆኖ የሚታየኝ፣

1–እንዴት ተመሰረቱ፤ ከዚህ ጥያቄ የሚገኘው ምላሽ እነርሱ እንደሚሉት በትጥቅ ትግል በተገኘ ገንዘብ፣ ወይንስ ሌሎች እንደምንለው ከሀገር  በተዘረፈ ሀብት የሚለውን ያሳያል፡፡ ያለጥርጥር የሚገኘው ምላሽ በማስረጃ የሚረጋገጠውም ድርጊት ሁለተኛው ነው የሚሆነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ በተዘረፈ ሀብት የተቋቋመ ድርጅት ማንም ይሁን ምን፣ እንዲሁም ምንም ያድርግ ምን ከተጠያቂነት ነጻ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለሆነም የህውሀት የዘረፋ ድርጅቶች ( የንግድ የሚለው መጣኝ ስም አይመስለኝም) ለአብዛኛው የትግራይ ነዋሪ ምንም ባልጠቀሙበት ሁኔታ ቀርቶ ለእግሩ መራመጃ ወርቅ ቢያነጥፉለት፣ በየ ቤቱ ወተት በቧንቧ ቢያስገቡለት እንኳን ከተጠያቂነት  ነጻ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

2-እንዴትና ምን ሰርተው አደጉ፣ ተመነደጉ፤ በወሬ ደረጃ እናውቀው እንደነበረውና አቶ ኤርምያስ በማስረጃ እንዳረጋገጠልን እነዚህ ድርጅቶች ያደጉ የተመነደጉት በንጹህ ሰርተው በነጻነት ተወዳደረው አይደለም፡፡ የድርጅቶቹ ባለቤቶች መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው እቃዎችን ከቀረጥ ነጻ ከማስገባታቸው በላይ ከባንክ ተበድረው አለመክፈላቸው፣ ሲበዛም እዳ ማሰረዛቸው፣ የመንግስት ድርጅቶችን ንብረት ወስደው የራሳቸው ከማድረጋቸው በላይ ለባለንብረቶቹ መልሰው በማከራየት ተጠቃሚ መሆናቸው፣ ድርጅቶችን ወደ ግል ማዞር በሚል ሰበብ በአነስተኛ ዋጋ ድርጅቶችን ከመሰብሰባቸው ባሻገር እነርሱ ከሚያመርቱት ምርት ጋር ተመሳሳይና በገበያ ተፈላጊ የሆነ ምርት የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን መንግስታዊ ሥልጣንን በመጠቀም ከገበያ በማስወጣት ወይንም ተፎካካሪ እንዳይሆኑ በማዳከም፡ ገበያውን ለብቻቸው መያዛቸው ( የጨርቃ ጨርቅና የስሚንቶ ፋብሪካዎች ይጠቀሳሉ) ወዘተ የከፋ ወንጀል ነው፡፡ ሌላም ሌላም ይጠቀሳል፤

ስለሆነም እነዚህን ድርጅቶች ማንነታቸው፣ ምንነታቸውና እንዴትነታቸው ላይ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ በመጥቀም አለመጥቀማቸው ላይ ማተኮርና በዚሁ ለመመዘን መሞከር ፖለቲካዊም ህጋዊም አካሄድ አይመስለኝም፡፡

ግን ግን  ይህ ሁሉ በአቶ ኤርምያስ የመለስ ልቃቂት መጽኃፍ የተገለጸው ዝርፊያ ሲካሄድ እኛ የት ነበርን? ብለን በየግል ራሳችንን መጠየቅ ያለብን ይመስለኛል፡፡ ውሻ ልጆቿን ሰብስባ ምን ቢርባችሁ እሰው ቤት ገብታች እቃ እንዳትደፉ የውሻ  ልጅ ተብላችሁ ታሰድቡኛላችሁ በማለት ትመክራቸዋለች፡፡ በዚህ ግዜ ከመሀል አንዷ ተከፍቶ ካገኘንስ በማለት ስትጠይቃት   አፍሽ እስኪከቱልሽ ልትጠብቂ ነው በማለት መለሰች እንደሚባለው ወያኔ ኢትዮጵያን ክፍቷን አገኛትና ጫካ ሆኖ ሲጎመዥበት የነበረውን ነገር ሁሉ እየዘረፈ ሳያላምጥ ዋጠ እየዋጠም ነው፡፡ ራሳችንን እንጠይቅ!

“ቴዎድሮስ ካሳሁንን እና ሙዚቃውን ለምን ህዝብ ይወዳቸዋል?” (ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ)

teddy afro

ኢትዮጵያዊነት በአንጻረ ጎሰኝነት

ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ

“ቴዎድሮስ ካሳሁንን እና ሙዚቃውን ለምን ህዝብ ይወዳቸዋል?” ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ “እሱ እና ሙዚቃው ኢትዮጵያዊነትን ስለሚዘምሩ ነው፤” የሚል ነው። በሌላ አነጋገር፥ ጎሰኝነትን ስለማያራምዱ ነው።

ባለፉት 48 ዐመታት በተማሪዎች ቆስቋሽነት የተጀመረው ጎሰኝነት ባለፉት 25 ዐመታት እንደ ሰደድ እሳት ተዛምቶ፥ በኢትዮጵያዊነት ላይ የማያቋርጥ ዘመቻ አካሂዶ፥ ኢትዮጵያዊነት ጨርሶ አለማክተሙ እና ማንሰራራቱ የሚያስገርም ነው። ኢትዮጵያዊነትን ለሚጠሉ ደግሞ አስደንጋጭ መርዶ ነው። እውነት ይህን ያህል ህዝብ ጎሰኝነት አንገፈገፈኝ ብሎ ኢትዮጵያዊነትን ናፍቋልን? መልሱ አዎንታዊ ይመስላል።

በእርግጥም ኢትዮጵያን ሊያድናት የሚችለው ኢዮዬጵያዊነት ነው። ለመሆኑ “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ምንድነው? ኢትዮጽያስ ለምን ኢትዮጵያ ተባለች? ኢትዮጵያ ማለት በሱባ (ከግእዝ በፊት የነበረ የጥንት ወገኖቻችን ቋንቋ) ብጫ ወርቅ ስጦታ (ለእግዚአብሄር) ማለት ነው። የዛሬ 4000 ዐመት የኖረው የንጉሥ ንጉሥ የካህን ካህን በመሆን ዐለማዊና መለኮታዊ ማእረግ የነበረው አባታችን ኢትዮጵ በዚህ ስም ይጠራ ስለ ነበር ሀገሪቱን ኢትዮጵያ አሰኛት። የኢትዮጵያን ስልጣኔ ልጆቹ በመላው አፍሪካ በማዳረሳቸው እስከዛሬ 600 ዐመት ድረስ መላው አፍሪካ ኢትዮጵያ ይባል ነበር። አሁንም በኢትዮጵያውያን አፋሮቻችን ምክንያት አፍሪካ ይባላል። ዞሮ ዞሮ ከእኛ ስም አልወጣም።

ኢትዮጵ 10 ወንዶች ልጆች ወልዶ 10ስሩ ተባዝተው ዛሬ ሁላችንም ከነሱ ተገኘን። ስለዚህ በእያንዳንዳችን ደም ስር ውስጥ የኢትዮጵ ደም እየፈሰሰ ሁላችንንም እዛምዶናል ማለት ነው። ትውልደ ኢትዮጵያ የሆንን ሰዎች ሁሉ ወደድንም ጠላንም አመንን አላመንም፣ እውስጣችን የእዚህ ትልቅ ሰው እና የክብርት ሚስቱ የንግሥት እንቁዮያጳግዮን ደም ይፈስሳል። ይህም እጅግ የሚያኮራ እንጂ የሚያሳፍር አይደለም። ይህን የማይቀበል ክቡር እና ግዙፍ የሆነውን ማንነቱን የማያውቅ ብቻ ነው። ወይም በፓለቲካ ልቦናውን የታወረ ነው።

ጎሳስ ምንድነው? ጎሳ አንድ ቋንቋ የሚየናገሩ ሰዎች ማለት ነው። ዘርፉ ከቋንቋ እንጂ ከዘር አይደለም። የአማራ ወይም የኦሮሞ ጎሳ ማለት አማርኛ ወይም ኦሮምኛ የሚናገር ሰው ማለት እንጂ ዘሩን አይጠቁምም። ቋንቋ የመግባቢያ መሣሪያ ብቻ ነው እንጂ በደም የሚያገናኝ አይደለም። በደም፥ ያው ከፍ ብዬ እንዳልኩት የኢትዮጵ ልጆች ነን። ኢትዮጵያ ውስጥ 82 ቋንቋዎች ተናጋሪዎች አሉ። በዘራቸው ግን አንድ ናቸው። የመነጩት ከኢትዮጵ ደም ነውና። ስለዚህ ሁሉንም ትውልደ ኢዮያጵያውያንን በስጋ የሚመያዛምዳቸው ኢዮዮጵ ነው እንጂ ቋንቋው አይደለም። የዚህን ዝርዝር ለማየት “የኦሮሞ እና አማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” የተሰኘውን መጽሀፌን መመልከት ይጠቅማል።

እንግዲህ ኢትዮጵያዊነትን በአሁኑ ሰዐት ሰው ሁሉ የፈለገው ውስጡ ያለው ደመነፍስ ኢዮጵያዊነቱን ስለ አረጋገጠለትና ጎሰኝነት ዋጋቢስ መሆኑን ስለተገነዘበ ነው። ከአሁን በኋላ ኢዮጵያዊነት ለምልሞ ያብባል እንጂ ጠውልጎ አይደርቅም።