Archive | May 24, 2017

‘በፌዝ ቡክ’ መቀነጣጠስ እና መጀናጀን ካቆምንበት ቀጥለናል …lol

 

እፎይ ትምህርት ዓለቀ ተገላገልን…. አሁን ደሞ ወደ ፌስ ቡክ ቻት እና ጅንጀና እስኪ እንመለስ
ግን ምን እንደተሸወድኩ ታውቃላችሁ ጥናት ሰዓት ላይ ስልኬን አለማጥፋቴ እንዴት ሰው አምስት ደቂቃ ሃሳቡን ሰብስቦ ማጥናት ያቅተዋል? ልማድ ሆኖብኝ መልክት ተላከ አልተላከ እያልኩ እጄ እንዴት ይላቀቅ ደሞ ከኔ ራቅ አድርጌ ባስቀምጠው ድምጹ ቂው….! ሲል አሁንም አላስችል ይለኝ እና እጄን ሰደድ አቤት አቤት ያየሁት መከራ እኮ….
የፈተናዬን ውጤት እስከማውቅ ብጉዋጉዋም… እድሜ ለፌዝ ቡክ ጉዋደኞቼ እንደጉድ… ይጀነጀናል….

አሁንማ በቃ ማን ከልካይ አለበኝ እንዴት ቻት ማረግ እንዳማረኝ…. 😂😂

ኤደን አንድዋ የፌስ ቡክ ጉዋደኛዬ ነች በጣም አሪፍ ልጅ ነበረች ቀልድም ቁምነገርም ትችልበት ነበር … ነገር ግን ዛሬ ጽፌላት በሶስተኛው ቀን ነው መልሱ የሚመለስልኝ:: እሱንም እግዜርን ከፈራች ነው እንጂ በአምስት ቀኑም ሊሆን ይችላል… በፖስታ ብትልከው እንኩዋን ይህን ያህል መች ይቆይና…. ?! ሊያውም በዚህ ዘመን …
ምን ያህል ጉዋደኞች ቢኖርዋት ነው እንዲህ ቢዚ የምትሆነው…? ብዬ ለማየት ብሞክር ፌስ ቡክ ጀግናው

”እሱ ሚስጥር ነው ላንተ አይፈቀድም” …ሰላለኝ ለመገመት ተገደድኩ
አንድ ፎቶ ብትለጥፍ በስድስት መቶ ሰው በአንድ ቀን ላይክ በመደረጉ በርግጠኝነት ከአንድ ሺህ በላይ ተከታዮች ሊኖርዋት ይችላሉ በዬ ስለገመትኩ ጣቶቼን ወደ ዳጊ (ዳግማዊት) አዙሪያለሁ …! ሁሌ ወረፋ መጠበቁ ሰለቸኝ እኮ….Lol

ዳጊ… አቤት… ድምጽዋ ውይ ውይ ውይ ….ገዳይ ነው…! አቤት ቁም ነገርዋ ሊያውም ከጠለቀ እውቀት ጋር… ቁንጅናዋ ያው “ፎቶ ሾፕ ይሁን ኦርጅናል” ብቻ የቴዲ አፍሮን ”ያምራል ያምራል ቁንጅናሽ ያምምራል” ዘፈን ሁላ ያስጋብዛታል::…kkk

የኔ የገጽ ፎቶዬ የቡና ሲኒ ቡናው ተቀድቶና ጤናዳም ከጎኑ በመሆኑ አንድ ቀን ስለቡና በሜሴንጀር ስልክ ወሬ ጀመርን
ወይ ጉድ አውርታው አትጠግብም እኔ እንደውም ረጅም ሰአት ዝም ብዬ ስሰማት ደስ ይለኛል

”ይኁውልህ”
አለችኝ በዛ በሚያምር ድምጽዋ

”ኢትዮጵያ ከ አስረኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ወይም ለ 1100 አመታት ያህል የቡና ባህል አላት በአለም የመጀመርያው ነን::….. 28% (ፐርሰንት) ኢኮኖሚያችን በቡና ላይ ነው…:: 15 ሚሊዮን ዜጋ በስራው ላይ ተሰማርቶ የእለት እንጀራውን ያገኛል:: ነገር ግን ቡናው ከገበሬው ለፍቶ ደክሞ በትንሽ ዋጋ ወደ ፈልፋይ እና አጣቢ ይሸጣል:: ከዛ ወደ ውጭ የሚልኩ ነጋዴዎች እጅ ይደርሳል:: በመሃል ብዙ ሰው እጁን ሰለሚያስገባ ዋጋው ይወደዳል:: ይህ ደሞ የቡናው ውድ መሆን የሚገዛውን ሰው ውስን ሰለሚያደርገው ያደጉት ሃገሮች አይኖቻቸውን በጥራት እና በብዛት አምርተው በቅናሽ ወደሚሸጡ እንደ ዩጋንዳ ህንድ ኤንዶኔዥያና ብራዚል በማድረግ ላይ ናቸው:: ይህ ደሞ ለሃገራችን የወደፊት ኢኮኖሚ ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል አስበው…!!” አለችኝ ዳጊ

እውነትዋን ነው እኮ አልኩ በሃሳቤ ለምሳሌ አሜሪካ የጦር መሳርያ በ አመት ለሳውድ አረብያ 82 ቢሊዮን ዶላር እንደሸጠች ሌላውን ሳንቆጥር…. እንዲሁም ጀርመን ማሽኖችን መኪናዎች ኬሚካሎች የኤሌትሪክ ሃይል የህክምና መሳሪያዎችና መድሃኒቶች ባቡር በ አመት 1.5 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚያስገቡ መረጃዎቻቸው ያሳያል:: ሆ …….ታድያ እንዴት አያድጉ?

ዳጊ ቀጠለች ”የተማረው የሰው ሃይል ክፍል ስደትን ወዶም ሆነ ተገዶ በመምረጡ ሃገራችን በተወሰነ ነገር ላይ መፍጨርጨሩ በዙም ለውጥ ሊያመጣ አላስቻለውም ዘመናዊነት እና ከጊዜው ጋር አለመራመድ በዙ ወደሁዋል እንድንወርድ አደርጎናል”
እያለች ረጅሙን ነገር በአጭሩ ቁልጭ አርጋ አስቀመጠችው
ወይ ዳጊ….
እና አንቺ በግል ምን ታስቢያለሽ ታድያ?… ብዬ ጠየኩዋት
”ለትምህርት ነበር ውደ ውጭ የወጣሁት አሁን ጨርሻለሁ እዚህ መስራትና መኖር እችላለሁ እነሱም የተማረ ሰው ማማለል እና መሰብሰብ ከዛም አፍሪካን ወደሁዋላ አስቀርተው እራሳቸውን ማሳደግ ይችሉበታል እኔ ግን ለሃገሬ አስፈልጋታለሁ እኔም ሃገሬን እፈልጋታለሁ!!”
በመሃል ረጂም ሰከንድ ዝም አለች እና
”በሰው ሃገር እድሜ ልክ ድመት ሆኖ ከመኖር በሃገሬ አንድ ቀን አንበሳ ሆኖ መሞት እመኛለሁ” አለችኝ

ዳጊ አንድ ሳትሆን ሺህ ቢሆኑ ምን ነበረበት… ብዬ ተመኘሁ ይህን ባወራን በወሩ ከኢትዮጲያ ሆና ጻአፈችልኝ እንዲህ ይላል
”ኢትዮጵያን ደምና ጦርነት አይቀይራትም በደም ብትቀየር ኖሮ እነ አጼ ቴዎድሮስ ያፈሰሱላት ደም እስካሁን በቀየራት ነበር በአሁኑ ዘመን ኢትዬጵያን የሚቀይራት አንድነት ሰላም ፍቅር እና ዋናው ደግሞ ታሪክን ማውራት ብቻ ሳይሆን ደም እስክንተፋ መስራት ነው:: ያኔ ሃገር ትቀየራለች”
እኔም በውስጤ የፈተና ውጤት እንግዲህ ይምጣና ዳጊ ጋር አንዱ የኢትዮጵያ ክፍል እንገናኝ ይሆናል::

እስከዛው ግን የፌስ ቡክ ጅንጀናው ይቀጥላል….😂😂😂

facebook