Archive | June 2017

ከስደት ምክንያቶች አንዱ….

 

ከእሙ ጋር አልፎ አልፎ ቅዳሜ ማታ እኔ ቤት ወይም እስዋ ጋር እየተገናኘን አንድ ሁለት እንላለን ፣ ካርታ እየተጫወታለን ፣ አልያም የሃገረኛ ፊልሞች እያየን እናመሻለን ::

እሙ ጨዋታ ትችልበታለች ቁም ነገርዋም ቀልድዋም አይጠገቡም:: ጠይም መልኩዋን እና ቁንጅናዋን ስለምወደላት እና ሁሌም ሰለማደንቅላት ደስ ይላታል

አንዳንዴ እንደውም…. ታውቂያለሽ አይደል ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ቢኬድ አንችን የመሰለ ቆንጆ እንደማይገኝ እላታለሁ….

ሂድ ወገኛአሁን ዞረህ ያየህ አትመስልም?”… ትላለች እየሳቀች እና እየተሽኮረመመች

አንድ ምሽት ግን ከሃገር ለምን እና እንዴት እንደወጣች ጠየኩዋት::…

ትንሽ ወደ ሁዋላ መለስ ብላ እንደማሰብ ካለች በሁዋላ ……የመጀመርያ ባለቤቴን ሽሽት ነው…” አለችኝ

ማለት…. ….እንዴት? ብዬ ጥያቄዬን አከታተልኩት:: ያው በዝርዝር እንደታወራኝ ሰለፈለኩ

ይኁውልህ ሰውየው በእድሜ በጣም ትልቅ…. ያለተማረ….. ግን በጣም ሃብታም እና የጊዜው ሰው እንደሚባሉት ነበር:: አባታችን በልጅነታችን ስለሞተ እናታችን በጣም ተቸግራ ነበር ያሳደገችን:: የዚህ ሰውየ እኔን የማግባት ሃሳብ ሲመጣ ቤተሰባችን የታየው በሰውየው ሃብት እነሱ ሃብታም መሆን እንጂ የእኔ በእድሜ ማነስም ሆን ጉዳቴ የታየው ማንም አልነበረም::

ተጋብተን ሁለት ቀን እንኩዋን ከእኔጋ አላሳለፈም:: አምሽቶ ይመጣል ፥ ከፈለገ ያደራል ፥ ሲያሻውም ሳምንት ለስራ ነው በሎ ቆይቶ ይመጣል ማንም እሱን የመጠየቅ መብት የለውም ::

ለኔም ትንሽዬ ቡቲክ ቦሌ አካባቢ ከፍቶልኝ ስለነበር ያው እቃ ለማምጣት ወደ ዱባይም ወደ አውሮፓም መውጣት እንደምፈልግ በግድ ሰለጨቀጨኩት ይዞኝ ይሄዳል ቀን አብረን እቃ ማየት ካለብን አብረን እናያለን ማታ ግን የትም ከማንም ጋር እኔን ሆቴል አስቀምጦ ሲማግጥ ያድራል::

በዙ ጌዜ ቻልኩት በሰው አስመከርኩት በሽማግሌ አስለመንኩት እሱ ግን ገንዘብ ስላለው ማንንም አይፈራምም እኔንም ማስፈራራቱን ቀጠለ:: ሞቅ ሲለው እንደውም መሳሪያውን ያወጣና….. ”አርፈሽ ካልተቀመጥሽ በእዚህ እግርሽን ላሳጥረው እንደምችል እና ማንም እንደማይጠይቀኝ ታውቂያለሽ አይደል? ይለኝ ነበር….. አንጀቴ ቢያርም የግድ ለቤተሰቦቼ ስል መታገስ እንዳለብኝ እራሴን ለማሳመን ሞከርኩ::

የመጨረሻ ቀን ግን በስልክ ደውሎ ሻራተን ሆቴል ጋዝ ላይት ነኝነይ”… በሎኝ ስደርስ ሞቅ ብሎታል ከሰዎች ጋር ያሽካካል :: ለኔም አዘዘልኝ እኔ የማላውቅቸውንም ሰዎች ካልጠጣችሁ እያለ ይጋበዛል:: ለኔ ከእቤት መውጣቴን ብወደውም እሱን በእንዲህ አይነት ሁኔታ ማየት ግን ደስታየን አቀዝቅዞት ነበር::

ብዙም ሳይቆይ በጆሮዬ ጠጋ አለና ሚኬሌ እኮ ሞተ”… አለኝ:: ሰምቼዋለሁ ግን ስለሰከረ ስም ተሳስቶም መሰለኝ

ምን?… ብየ በድንጋጤ ጠየኩት ሚኬሌ ማለት የእሱ የቅርብ ጉዋደኛው ፣ በማንኛውም ችግር ጊዜ ከጎኑ የሚቆምለት ፣ ብዙ ውለታን የዋለለት ፣ የእኛ ትዳር እንዳይፈርስ ሁሌ የሚጥር ፣ መካሪው ፣ የልቤ ጉዋደኛ የሚለው….. ሞቶ እሱ ምንም ሳይመስለው እኔንም ጨምሮ መሸታ ቤት….. ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ ነው

መኪናዬን ጠዋት ተበድሮኝ ወደ ክፍለ ሃገር ሲሄድ ተገልብጦ ሞተእስኪ ይታይሽ አዲስ መኪናየን እኮ ነው ድምጥማጡዋን ያጠፋት”… እያለ በመኪናው መገልበጥ ይበሳጫልይሳደባል … እራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም

የልብ ጉዋደኛህ ሞት ነው የሚያሳዝንህ…? ወይስያንተ ቆርቆሮ መጎዳት ነው የሚያሳዝንህ? ሳላስበው ጮኩ

እንደ እብድ እየበረርኩ ወደ ውጭ ወጣሁ እግሬ ግን መራመድ አልቻለም:: የሰው ልጅ ህይውት እንደ ድንገት ወጥቶ መቅረት ፣ ደግ የማይበረክተበት ምድር ፣ ለተቸገረ ልቡ ሁሌ የሚራራው ፣የቤተሰብ ሃላፊነቱ ፣ የአምስት ወር ነፍሰ ጡርና በቅርቡ ያጫት ፍቅረኛ ያለችው ሚኬሌ….. መሬት ላይ ወድቄ ሆዴን በእጄ ጭብጥ አርጌ ይዤ ማልቀስ ጀመርኩ::

እየትንገዳገደ አጠገቤ ደረሰ

ምነውሌላ ግንኙነት ነበረሽ እንዴ?… እንዴህ የሚያደርግሽ…” እየተንተባተበ መርዛማ ንግግሩን ተፋው….

ይህን ስሰማ እራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም ያን ያህል ጉልበት ሁላ ከየት እንዳገኘሁ አላውቅም ብቻ በጥፍሬ ፣ በጥርሴም ቦጫጨኩት…. ሰዎች ቢይዙኝም ማቆም ግን አልቻልኩም::

አንተ ውሻ….. አተት ልክስክስ…. እኔን…? እንደወንድም በሚሳሳልህ ጉዋደኛህ እ….. እንባየ ይረግፋል…. በግድ በሰው ግልግል በታክሲ ጭነው እናቴ ቤት አደረሱኝ:: ሌሊቱን ሙሉ ሳለቅስ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነጋ:: በንጋታው የሚኬሌን ቀብር እንኩዋን መሄድ አልቻልኩም ምክንያቱም ይሄን ሰውየ ለአንድ ሰከንድ የማይበት አቅም አልነበረኝም::ምን ማድረግ እንዳለብኝ ብዙ አሰብኩ በዙ አወጣሁ አወረድኩ…. በመጨረሻም ስደት!!…. በአልተቃጠለው የጣልያን ቪዛ የእሱን አምስት ሳንቲም ሳልነካ እናቴንም እንኩዋን የት እንደሄድኩ ሳልነግር እና ሳልሰናበት ከሃገር ወጣሁ…..

እሙ ይሄን ስትነግረኝ በተመስጦ እየሰማሁዋት ሳላሰበው የእኔም እንባ እየወረደ ነበር

አሳ ጎርጓሪ…

 <<ትግራይ በልማት ወደሁዋላ ቀርታለች!>> የሚለው የሰሞኑ ለቅሶ አንዳንዶች የተዘጋ ፋይል በግድ እንዲከፈት እየጎተጎቱ ይመስላል።ስርዓቱ ፍትሐዊ አይደለም ሲባል የአማራው እንግዳ ቡድንን ባህርዳር ከነማን <ካልገደልን> ብለው በአስለቃሽ ጭስ የተበተኑት የትግራይ ልጆችና በሰላማዊ የእሬቻ ሀይማኖታዊ በዓል ላይ እጃቸውን ወደ ላይ ለሰላማዊ ተቃውሞ ባመሳቀሉ ላይ ጥይት ማርከፍከፍንም ይጨምራል።ዜጎች እኩል ሊታዩ ይገባል ለማለት ነው። አንዱ አላግባብ የሚገደል መሆን የለበትም።

የሰሞኑ የትግራይ በልማት ወደ ሁዋላ ቀርታለች፣ በፌዴራሉ መንግሰት ተበድላለች አይነት ለቅሶ በበጀት ዋዜማ መሆኑ ብዙ የተዘጉ ፋይሎች እንዲከፈቱ ያበረታታ ይመስላል። ለመሆኑ ትግራይ ከማን ጋር ተወዳድራ ነው ወደ ሁዋላ የቀረችው? ከአሜሪካ ወይስ ከስዊዘርላንድ? መቼም ከአማራ፣ከኦሮሚያ፣ከሱማሌ፣ከደቡብ ወዘተ እያላችሁ በማስረጃ እንደማትሞግቱን ተስፋ አደርጋለሁ። ትግራይን ጨምሮ ሁሉም የአገሬ ሕዝቦች የሚኖሩበት ቦታ በልማት ቢያድግ እመኛለሁ። ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ትግራይ እንደ እናት ልጅ ሌላውን አንዳንዱን እንደጠላት የቀረውን እንደ እንጀራ ልጅ የሚያይ ስርዓት <<የፌደራል>> የሚል ታርጋ ስለተለጠፈለት እንውቀሰው ካላችሁ ለምን ለትግራይ ክልል አደላ በሚል ካልሆነ << ጩኸቴን ቀሙኝ>> አይነት የሰሞኑ ለቅሶ ውሃ አይቋጥርም።
የአንድ አገር ብሄራዊ ዳቦ (በጀት) ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት እንዴት ሲከፋፈል እንደነበር፣ተሰርቆም፣ተለምኖም የመጣው ሁሉ በአድልዎ አንዴት ለትግራይ ክልል ቅድሚያ በሚል ይሄድ እንደነበር ብዙ ማስረጃ መዘርዘር ይቻላል።<<ይሄ ሁሉ ተግዞ የትግራይ ክልል ከሌላውም አፍ እየተቀማ ተወስዶ ያን ያህል አልተጠቀመም!>> የሚል ቅሬታ የሚያቀርብ ቢኖር ፍትሐዊ ያልሆነውን ስርዓትና አመራር መደገፉ አንድ ነገር ሆኖ ጆሮ ገብ ስሞታ ሊሆን ይችል ይሆናል።
በየዓመቱ የአገሪ በጀት ይደለደላል። የበጀት ስሌቱን ዛሬ <<ትግራይ ተደብላለች>> የሚሉት እንዴት እንደተሰራ መለስ ብለው ቢያዩት እንመክራለን።በአጭሩ ሕወሃት በሚቆጣጠረው የፌዴሬሽን ም/ቤት ከየክልሉ ለም/ቤቱ በተወከሉ ፖለቲከኞች የበጀት ድልድሉ ቀመር ይጸድቃል። ባለፉት ሃአ ስድስት ዓመታት፡ኢሄ ድራማ እንደቀጠለ ነው። መጀመሪያ በጦርነት የተጎዱ ክልሎች ልዩ ድጎማ ይሰጣቸዋል ተባለ።በዚህ ሒሳብ ከአቅሟ በላይ( በጀት ስሌቱን ይሄን ታሳቢ ያደረገ በማድረግ) ተቀም ያለ በጀት ለትግራይ ተደጋግሞ ተሰጥቷል።
ከዛሬ 13 ዓመት በፊት አንድ ቀን ለዘገባ ወደ ፓርላማ ስሄድ በአጋጣሚ በሌላ አዳራሽ የጦፈ ክረክር መኖሩን አንዱ አባል ሹክ ይለኛል። ጉዳዩን ለመስማት <<የሕዘብ ተወካዮች>>(እነሱ የሚጠሩበት ስም ስለሆነ ይቅርታ) የፓርላማ አባላት ተብዬዎቹን ስብሰባ ተውኩና በዚያው በፓርላማ ጊቢ አጠገቡ ወደሚገኘው የፌዴሬሽን ም/ቤት ገባሁ።እነዚህ ፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት በቀጥታ ከክልሉ ተወክለው የሚመጡ በመሆኑ ብዙዎቹ የየክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ናቸው። የዕለቱ ውይይት የበጀት ቀመር ስሌቱ ላይ ለመወሰን ነበር። ይሄ ደፋር ም/ቤት በአገሪቱ በጀት ስሌት ላይ ብቻ ሳይሆን በሕገ መንግስቱም ላይ ፈራጅ ነው። ዳኞች በግልጽ ለሚያዩት ሕገ መንግስቱን የጣሰ ክስም ሆነ አቤቱታ <<ይሄ ሕገመንግስታዊ አይደለም >>የሚል ቅሬታ ሲቀርብ ወዲያው ወደዚህ ም/ቤት ይልካሉ፤ይሄ ም/ቤት ከአልሆነ ሌላ ሕገ መንግስቱን የመተርጎም ስልጣን የለውም። ለበጀት ድልደላው መሰረት የሆነውም ቀመር የሚወሰነው በዚህ ም/ቤት ነው:፡ ታዲያ በዚያ ዕለቱ ስብሰባ የበጀት ቀመሩን ለመወሰን የትግራይ ክልልን ወክለው ከሚገኙት፡ፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት መካከል አቶ ሐሰን ሺፋ በጊዜው የፌዴራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ፣ዶ/ር ሰለሞን ዕንቋይ የክልሉ ሌላ ባለስልጣን መገኘታቸው ትዝይለኛል።የአፋር እና የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንቶችም ነበሩ። የሆነው ሆኖ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የነበረው ከበጀቱ በህዝበ ብዛት ስሌት ለመቶኛ ሲካፈል በዚያም በዚህም እየተባለ ዛሬ ተጎዳች የተባለችው ከአገሪቱ ህዝብ 6 በመቶውን ምትኢዘው ትግራይ ያለ ማጋነን በአካፋ ይዛቅላታል። የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል ሆኖባቸው ነው መሰል አንዳንድ ክልሎች የበጀት ስሌቱ ቀመር አግባብ አይደለም የሚል ስሞታ በዜያ ስብሰባ ላይ ያነሳሉ።ሕወሓት ይህ መሰሉ ጥአቄ አንዳንዴ በተለያዩ ክልሎች ሲነሳ <<የትግራይ ሕዝብ ደመኞች>> እያለ በማሸማቀቅ ጥአቄውን ሲያዳፍን ቆይቷል። በዕለቱ የቤንሻንጉሉ የጊዜው ፕሬዝዳንት ያረጋል አይሸሹም እየደጋገመ በተለይ ትግራይና ቤንሻንጉልን ጨምሮ አነስተኛ ሕዝብ ያላቸው ክልሎች ለቀመሩ የሕዝብ ብዛት በመቶኛ ከፍ ብሎ ከተሰጠ እንደሚጎዱ በማስታወስ ሰፋ ያለ ዲስኩር እንዲያደርግ ተደረገ:፡ በተናገረ ቁጥር እነ ሐሰን ሺፋን እየደጋገመ ዞሮ ማየቱ ሰውዬው ከሁዋላ በሱ በኩል ሆን ተብሎ እንዲነሳ የተፈለገ አጀንዳ ለመኖሩ ግልጽ ነው። ሕወሓት እንደልቡ ከሚጨፍርባቸው ሰዎች አንዱ ያረጋል ነው። እንደልቡ ከሚጋልብበባው ክልሎች ቤንሻንጉል ክልል አንዱ ነው:፡ ቁጥር የገባቸው በመጠኑ ለማስረዳት ሞከሩ። አንዳንዶች ፈራ ተባ እያሉ የሕዝብ ብዛት በቀመር ስሌቱ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ፣መሰረተ ልማት ወደሁዋላ መቅረቱን ቁጥር እያስደገፉ ለማስረዳት ሞከሩ። አጠር አጠር ያለ አስተያየት ሲሰጥ የቆየው ሐሰን ሺፋ ቆጣም ከረርም እያለ በምክር ቤቱ ያሉትን ለማሸማቀቅ እሱ የትግራይ ሕዝብ ደመኞች ያላቸውን እየጠቀሰ የቀረበውን ለሕዝብ ብዛት የበለጠ ይሰጥ የሚለውን አጣጣለ። ሕዝብ ብዛት እየተባለ ቅድሚያ የበጀት ቀመሩ ከፍተኛ ድርሻ ከያዘ በጦርነት ተጎዳችው ትግራይ ተጠቃሚ እነደማትሆን ዘረዘረ። ለይስሙላ የተደረገው ውይይት ሐሰን ሺፋ ያስረገጠበትን ሀሳብ መሰረት ያደረገ ውሳኔ ተላለፈና ተዘጋ።በዚህ ቀመር ስሌት በጀት ይመደብና <<ፓርላማው>> ሰኔ 30 ለእረፍት ከመዘጋቱ በፊት አጸደቀው ይባላል፡:
የበጀቱን ጉዳይ ያነሳሁት በአገሪቱ ሕዝብ ስም የተገኘ ገቢ፣ከብድርና ከዕርዳታ ከሚመጣው ማን የአንበሳውን ድርሻ ሲቀረጥፍ እንደኖረ በግልጽ ያሳያል ብዬ ነው። ከዚህ በተረፈ በእነ ኢፈርት ስም ከዚህ በጀት ጨምሮ ከየባንኩ የተዘረፈው፣ የመሰረተ ልማት፣የፋብሪካዎች አይነትና ቁጥር ፣በሰበዓዊነት ተግባር የመጡ መንግስታዊ ድርጅቶች ሳይቀር በአማራ፣በኦሮሞ፣በሶማሌ ሆነ በሌላ ክልል ለመስራት ያመጡትን ፕሮጀክት አጥፈው ዛሬ ተበደለች ወደተባለው ትግራይ ካላዞሩ ፈቃድ እንደማይሰጣቸው እየተነገራቸው አንዳንዶች ያንን ሲፈጽሙ ጥቂቶች እየጣሉ ወጥተዋል፡፡በዚህ አድሎዋዊ ሆን ተብሎ በተሰራበት ፖሊሲ ሳቢያ ህብረተሰቡን በልማት ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ፕሮጀክቶች ወደ አንድ አካባቢ(ትግራይ) በብዛት እንደሚገፉ ተደጋግሞ የተዘገበ ነው:፡ በእርግጥ በአማራ ክልል ዕድሜያቸው ያልደረሱ ህጻናትን ለማምከን ዘመቻ ጭምር እተደረገ የ10 ዓመት ህጻናት ሳይቀር ወሊድ መከላከያ ከለፍላጎታቸው በክንዳቸው እየተቀበረ መካን እነዲሆኑ ተፈርዶባቸዋል። ህጻናት በጊዜ ክትባት አጥተው ከተወለዱት በስንት መቶኛ አንደሚሞቱ ይህም ቁጥር ከትግራይ በስተቀር በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ክልል ብዙ መሆኑን ባለፈው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ለመቃወም የራሱ ስርዓቱ ያሰራጨወን ማስረጃ ይፋ ያደረገው የአማራ ባለሙያዎች ጥናት ያሳያል።

የትግራይ ተሟጋቾች ይሄ ማለት እያንዳንዱ የትግራይ ሕዝብ ተጠቀመ ማለት ነው ተብሏል ብለው አጀንዳ ለማስቀየር ወይ ለማደናቆር ሲሞክሩ ይገርመኛል።ዛሬም ድንጋይ ላይ ተቀምጠው የሚማሩ ህጻናት ኢትዮጵያውያንን እያየን፤ በበጀቱ ዋዜማ <<በተቃዋሚ ታጋዮቹ>> አንደበት የሚደለቀው የባቡሩና በልማት ወደ ሁዋላ መቅረት ዜማ ሌላው ቀርቶ የድሬዳዋን ከተማ ሕዝብ መከራና ድህነት ያየ አይታዘባችሁም? ዛሬም በሰው ጫንቃ በምጥ የተያዘች እናት ብዙ ኪሎ ሜትሮች እየተጓዘቸ መንገድ ላይ ሕይወቱዋ በሚያልፍበት አገር፣ዜጎች በገፍ ስራ አጥ ሆነው የብሔራዊ ዳቦ ድርሻቸው በአድልዎ እየተቀማ፤ ከቆሻሻ ላይ እስከመብላት ሲደርሱ፣ቆሻሻ ላይ ኖረው በቆሻሻ ተቀብረው ሲሞቱ ይሄን ስርዓት ያቆመ ሕወሓት በበላይነት እያስተዳደረ <<ባቡር…በልማት ቀረን ተበደልን….>> ስትሉ አታፍሩም? ባይሆን ሲታደግም ፍትሀዊ በሆነ መንገድ በአገሪቱ ሀብትና በእዳ ከመጣ ሀብት እኩል ካልሆነ ሌላው የበይ ተመልካች የሚሆንበት ስርዓት ለአገር አደገኛ መሆኑ እንዴት አይገለጥላችሁም? ዘንድሮ እናቱ የሞተችበትም ውሃ የወረደችበትም እኩል ያለቅሳል ሆኖ እንጂ በእውኑ በልማት የተጎዳችው ትግራይ ከየትኛው ክልል ጋር ተወዳድራ ነው? መቼም እዛ ሰፈር ማፈር ከቀረ 26 ዓመቱን አክብሯልና ዓለም አቀፉ የሒሳብ ስሌት እኛ ሳናውቀው ተቀየረ እንዴ? በሉ አንግዲህ አሳ ጎርጉዋሪ አይደል ከነተረቱ ሁሉም እንዴት እየተጎዱ እንደኖሩ ያቅሙን ይጸፍ።ፈርዶብናል እነሱ ከረሱት ማስታወስ ምን ይከፋል።

ኢትዮጵያዊነት የሰውነት ከፍታ ነው። አማራነትም የብሄራዊ ስሜት ዋልታና ማገር ነው፤ አትውረድ !!!

ኢትዮጵያዊነት የሰውነት ከፍታ ነው። አማራነትም የብሄራዊ ስሜት ዋልታና ማገር ነው፤ አትውረድ !!!
ሰው ሆኖ መፈጠር የድንቅ አእምሮ ባለቤት መሆን ነው። ሰማየ ሰማያትን ቀዶ ማሰብ መቻል ነው። ይህችን አለም ድንበር አልቦ ማድረግ ነው። እንደ መላእክት በመንፈስ መነጠቅ ነው። እኛ ደግሞ በአባቶቻችን የደም ዋጋ የተገዛን የሰማእታት ልጆች ነን። መጫሚያ የሌላቸው የቀደሙት አባቶቻችን ከአራቱም ማእዘን እየፈሰሱ በከፈሉት ዋጋ ነው እዚህ ያደረሱን ስንል ዛሬ የቆምንበት አፈር በነሱ አጥንትና ደም ጭምር ተለውሶ የተሰራ ነው ለማለትም ጭምር ነው። እኛ ደግሞ ከዚህ አፈር ጋር በእትብታችን ጭምር የተገመድን እንደመሆናችን ከዚህች መሬት ብቻ ሳይሆን ከዚህ ማንነት ወደየትም አንሄድም ወደየትም አንወርድም። ይኽ ውበታችን ብቻ ሳሆን እንደ አንድ ሉአላዊ ህዝብ የሚያኖረን ዋስትናችንም ነው። ሰንኮፋው ወያኔና ኩባንያው ነው። መፍትሄው እሱን ነቅሎ መሄድ ነው። ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን ብለን የተስፋ ስንቅ የምንሰንቅና ተስፋችንም ስጋና ደም ገዝቶ እውን እንዲሆን እስከ ሲዖል ዳርቻም ቢሆን ለመጓዝ ቁርጠኛ መሆን እንጅ ከዚህ ራእይ መጉደል ጉዞውን የኋሊት ያደገዋል። በአባቶቹ የወገብ ልክ መሙላት ያቃተውና ወያኔ ሰፍሮ በሰጠው ማንነት እንዲያስብ የተሰራ ብቻ ሳይሆን በዚህም የሚኮራ ትውልድ ከዚህ አካሄድ ጀርባ የተጠመደለትን አደጋ ማየት የተሳነው ብቻ ነው። ሰው ከአመክንዮ ወርዶ ሁሉን ነገር በስጋና በደም ብቻ መመንዘር ሲጀምር ምን ያህል ከእውነት ጋር እንደሚጣላና ሜዳና ገደሉን መለየት እንደሚሳነው ዳር ቆሞ ለሚያየው ሁሉ ፍንትው ያለ እውነት ነው። ችግሩ እርሱ በጎሳ ተስቦ መለከፉ ብቻ አይደለም። መለከፉን አለማወቁ ነው፤ ሌላውም እንደሱ እንዲሆንለት እንቅልፍ ማጣቱ ነው። በሌላ አነጋገር ታምሜያለሁና እናንተም፣ ታመሙ ማለቱ ነው። ሁሉም ታሞ ታሞ አስተማሚ በሚጠፋበት ቤት ማን ጥርኝ ውሃ እንደሚያቀብልን ፈጣሪያችን ይወቅ።በጎረቤታሞች መካከል በተነሳ ግጭት ግለሰቦች በደረሰባቸው ልብ ሰባሪ ሀዘን ተግፍተው የፈጸሙትን የሃይል እርምጃ እንደ ሰው ሆኖ ከተቻለም እንደራስ ሆኖ መፍረድ ሲገባ ዝም ብሎ እርምጃ የተወሰደበት ሰው ምንም ይስራ ምንም ነገር ግን አማራ ብቻ ስለሆነ የሌላውን ጉዳት ባለማየት ብቻ ሳይሆን የተፈጸመውን ወንጀል ወደ ጎሳ ፖለቲካ በማውረድ እነሱ ለሚፈልጉት አላማ ማዋልና ህብረተሰቡንም በዚያው በኩል እንዲፈስ ማራገብ ወይ የጤና ጉዳይ ካልሆነ ከወያኔ አለማነስ ነው። አማራነት እኮ ፍትሃዊነት ነበር:: አማራነት እኮ ሰውን በአርአያ ስላሴ መፈጠሩን እንጅ በጎሳ መንዝሮ ያለማየት አቅም ነበር። አማራነት እኮ የካህኑ የመልከጸዴክ ልጅነት ነበር። አማራነት እኮ በሄንኖክ ተወክሎ በብሄረ ሔዋን ማእጠንት የሚሰዋ ህዝብ መሆን ነበር። ዛሬ እንደ ኤሳው ብኩርናቸውን ያቃለሉና በመለስ ዜናዊ ጫማ ልክ ጨንግፈው የተሰፉ ሁሉ ሁለት ልጅ በሆዷ ተሸክማ ስለተገደለችው እናት ጸጸትት የሚገልጥ አንዲት ጥርኝ ቃል ከ አፋቸው ሳይወጣ ስለተቃጠለ ንብረት ግን ብዙ ብለዋል። እኔ በእንዲህ አይነት ተፈጥሮ የማውቀው ቦኮሃራምን እና አጋዚን ነበር። የኔታ እንዳሉት ይኽ ነገር ለኔ ክሽፈት ነው። ከምእራባዉያን የዜና ማሰራጫ ቋቶች በሚወጣ ፕሮፓጋንዳ የተፈለገውን ያህል ተጽእኖ ማሳደር አልተቻለም ተብሎ ቢቢሲና ሲኤን ኤን የአረብኛ ጭምብል ለብሰው በኩዋታር ከተሙና አልጀዚራ ሆነው መጡ። ከሱኒዎች እምብርት ኩዋታር በሚፈልገው የራሱ ቋንቋ የሚረጨውን ሁሉ ገና ለገና አረብኛ ነው በሚል ጆሮውን የሰጠው አረብ ሁሉ አልጀዚራን ተከትሎ ወደ ሰናኦር ዘመን ማዝገም ከጀመረ ሁለት አስርተ አመታት ሊሞላው ነው። ኢራቅ፣ ሊቢያ ሶሪያ የመን አፍጋኒስታን ካርታ ላይ አሉ ማለት አይቻልም። ቱርክ ግብጽ ባህሬን ኩዋታርና ሳውዲ አረቢያ ደግሞ ከፊት መስመር ተሰልፈው ቀናቸውን እየጠበቁ መሆኑን ለማየት አራት አይን አያስፈልግም።ከዚህ ሳይማር ጥቂት ወደ ጽንፍ የተገፉ ሰዎች የሚጽፉትን ብቻ እየተከተለ የሚሄድ ማንም ቢኖር ጤናውን ይፈትሽ።

የቴዲ አፍሮ ቁጭት (ከኤርሚያስ ለገሠ – ቁጥር ሁለት)

ከኤርሚያስ ለገሠ (ቁጥር ሁለት)

Teddy Afro, by Ermias Legesse

ባለፈው ሳምንት  የቴዲ አፍሮተሞክሮ!” በሚል ርዕስ ዘለግ ያለ መጣጥፍ አቅርቤ ነበር። በመጣጥፉ ላይ የኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ሙያተኞች ከቴድሮስ ካሳሁን እና ከእሱ በፊትና በኋላ ከነበሩ (ካሉ) መስዋዕት እየከፈሉ ካሉ አርቲስቶች መቅሰም የሚገባቸውን ትምህርት ለማሳየት ሞክሯል። የኪነ-ጥበብ ሙያተኞች ስራዎቻቸውን ለህዝብ ሲያቀርቡ ራሳቸውን የሚያዩበት መስታዋት ምን ዓይነት ሊሆን እንደሚገባ ተመላክቷል። “የቴዲ አፍሮ ተሞክሮ” በሚለው ማስታወሻው እንደተገለጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ባጠቃላይ የኪነ -ጥበብ ሙያተኞች በልዩ ሁኔታ ከድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ሁለት ትላላቅ ተሞክሮዋችን ሊወስዱ ይገባል። የመጀመሪያው  አገራችን በአሁን ሰዓት ያለችበትን ሁኔታ በአግባቡ መገንዘብ ይሆናል። አርቲስቱ እንደገለጸው “ኢትዮጵያዊነት እና ብሄራዊ ስሜት አደጋና ፈተና ላይ ወድቋል ” የሚለው ቀዳሚ ቁም ነገር ይሆናል።  በድምፃዊው አልበምም ሆነ በቃለ መጠይቁ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ስሜት እጅግ ፈተና ውስጥ መግባቱን እንድናስብ እና እንድንወያይ ያደርገናል። አርቲስቱ እንደገለጸው በጋራ ጉዞአችን ላይ የገጠመንን ችግር ለመረዳት መፍቀድና መቻል ወሳኝ ጉዳይ ይሆናል። ተያይዘን መራመድ ካልቻልን፣ ተያይዘን እንወድቃለን የሚለውን አባባልም መረዳት መቻል የወቅቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ ለመገንዘብ ያስችላል። ማወቅ መሰልጠን ነው። መሰልጠን ደግሞ ወደፊት መራመድ ነው። በእርግጥ ወደፊት ለመራመድ ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ ነው ማለት አይደለም። እንዲያውም ወደፊት መውደቅ የተለመደ ክስተት ነው። ዶ/ር ታደሰ ብሩ “የስራ አመራር ጥበብና ተያያዥ ጉዳዮች” በሚለው መጽሃፋቸው ወደፊት የወደቀ ሰው በራሱ ላይ ስቆ፥ አቧራውን አራግፎ፥ እግሮቹን አሻሽቶ፥ ያደናቀፈውን ድንጋይ አንስቶ፥ ሃሳቡን አሰባስቦ በተነቃቃ መንፈስ መንገዱን ይቀጥላል ይሉናል። በእርግጥም ወደፊት መውደቅ ከስህተቶች ተምሮ ከቀድሞ የበለጠ ተጠናክሮ የመገኘት አቅም የሚፈጥር ነው። የቅድሚያ ቅድሚያ መልእክቱ ይሄ ነበር ።

የመጀመሪያ መጣጥፍ ላይ ከአርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን የምንወስደው ሁለተኛ  ተሞክሮ ተብሎ የቀረበው ሀገራችን አደጋ የገባችበት መሠረታዊ መንስኤውን እና ምንጩን የተረዳበት ነው። ድምፃዊው እንደገለፀው ባሳለፍነው ሩብ ክፍለ-ዘመን ኢትዮጵያዊነት በሁለት መንትያ መርዞች ሰለባ ሆኗል። አንደኛው በሃይማኖት መከፋፈል ሲሆን ፤ ተከታዩ መንትያ ደግሞ የጎሳ ፓለቲካ እየተስፋፋ መሄድ ነው። እርግጥም ዘረኛና አምባገነን ስርዓቶች ዘወትር ህዝቡን በአካል ብቻ ሳይሆን፣ በመንፈስም ቀፍድደውና ከሰው በታች አድርገው መግዛት ስለሚፈልጉ ሃይማኖትና የጎሳ ፖለቲካ ላይ ቢያተኩሩ ውጤታማ ይሆናሉ። በመሆኑም ሁለቱ ችግሮች የሚፈጥሩትን መመሰቃቀል አዋህደን ስንመለከት ትክክለኛውን የአገራችንን የተወሳሰበ ችግር እንገነዘባለን። አለበለዚያ አንደኛው ክፍል ብቻ ነጥለን የምንወስድ ከሆነ የችግሩ ምንጭ፣ ምንነትና ጥልቀት መረዳት አንችልም።

የህወሓት አገዛዝ ሃይማኖት ውስጥ ገደብ የለሽ በሆነ መንገድ አስር ጣቱን በመክተት በአላዋቂነት በመፈትፈቱ ምክንያት በአማኞቹ ዘንድ ከፍተኛ ልዩነት ተፈጥሯል። ጆሮአቸውን በጥጥ የደፈኑት እምነት አልባዎቹ ህወሓቶች የህይወታቸው መመሪያ በሆነው የማኪያቬሊ አስተምህሮ በመመራት የሃይማኖት ተቋማት ሠላምና መረጋጋት እንዳይኖራቸው አድርጓዋል። የእምነት ተቋማቱ አመራሮች ቤተ-መንግስቱን ከተቆጣጠሩት ጋር በመቆም ኢትዮጵያውያንን በጅምላ ሲታሰሩ ፥ ሲገደሉ ፥ ሲሰደዱ ድጋፍ ሲሰጡ እንጂ አንዲት የእንባ ዘለላ ከአይናቸው ሲወርድ አላየንም ። እነዚህ የሲኖዶሱም ሆነ የመጅሊሱ ቁንጮ አመራሮች የሚያራምዱት አቋም ከሃይማኖቱ ተከታዮች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሰማይ ቤቱ ፈጣሪ ሳይቀር ጦርነት ገጥመዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ኢትዮጵያዊያንን አቻችሎ የያዘው ማህበራዊ ክር በእነዚህ የሃይማኖት መሪዎች እየተዘመተበት ነው ። በማህበረሰቡ ዘንድ በፍራቻ የታጠረ ዝምታ እየበዛ በመሄዱ የተፈጠሩት ችግሮች እየተጠራቀሙ ከማንወጣው ማጥ ውስጥ እየከተቱን ነው። አሁን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኘው ሲኖዶስ የምንሰማው ጉድ በጣም ያስደነግጣል ። ሰሞኑን እንኳን ከፓትሪያርኩ አንደበት የወጣው ቃል ምን ያህል ሃይማኖታዊ እሴቶች እየተሸረሸሩ መሔዳቸውን የሚያሳይ ነው ። አቡነ ማቲያስ ከሸገር ሬድዮ ጋር በደረጉት ቆይታ “ ሙስናን ተው ማለት ከአንበሳ አፍ ስጋ እንደመንጠቅ ነው ፥ አቅሙም ጉልበቱም የለንም ” ነበረ ያሉት ። ይሄኛው የፓትሪያርኩ አነጋገር እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የገለጠልኝ ነገር እነዚህ የእምነቱ አባቶች እግዚኣብሄር የሌለባቸው ፥ የሸሻቸውና ሊጠጋቸው ያልፈለገ መሆኑን ነው ። ታዲያ ! በአባቶቻችን ዘንድ እንዲህ አይነት ለስጋ የተገዛ የዲያቢሎስ መንፈስ በወረደበት ሁኔታ በማህበረሰቡ ዘንድ ከባድ ወንጀሎች ቢበራከቱ ለምን ይገርመናል?… ወጣቱ በሚያደነዝዝ እፅና የጫት ሱስ ተጠምዶ ብናይ ለምን ይደንቀናል?… በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሃቀኝነት ፥ ታማኝነትና መልካም ስነ – ምግባር የሚባሉ እሴቶች ድምጥማጣቸው በጠፋበት ሁኔታ በህብረተሰቡ ዘንድ ተንኮል ፥ እርስ በእርስ መጠራጠርና ሌብነት ቢስፋፋ ለምን አዲስ ይሆንብናል ?

ከዚህ በተጨማሪ የጎሳው ፓለቲካ የፈጠረው የህልውና አደጋም በግላጭ መታየት ጀምሯል። እንደ ወራጅ ጎርፍ አደጋው መጣሁ መጣሁ እያለ ነው ።  የህወሓት አባላት የሆኑት የበኩር ልጆችና እና የእንጀራ ልጆች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የማራቶን እሩጫውን ጀምረዋል። እርግጥ ድምፃዊው እንዳለው ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተለኮሰ እሳት ተገልብጦ ለኳሹን ማጥፋቱ ታሪካዊ እውነታ ነው። ቢሆንም ግን አሁን ያለውን ተጨባጭ ውስጣዊ ችግር መቃኝት አስፈላጊም ጠቃሚም ይመስለኛል። የውስጣዊ ችግሩ መነሻና መድረሻው መታወቅና የትግሉ ማእቀፍ በአግባቡ መሰመር ይኖርበታል። ከድሮው የተለየ በመሆኑ።

***

ዛሬ ኢትዮጵያ የተጋረጠባት አደጋ በዋናነት ከውስጥ የሚመነጭ ነው። በዋናነት ማለቴን እንድታሰምሩልኝ እፈልጋለሁ ። በዘረኝነት ላይ የተሰነቀረው አምባገነንነት ባለመገታቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም፣ ሕልውናና አንድነት ዋስትና አጥቷል። የውስጥ ገዢዎቻችን ከየትኛውም ዘመን በከፋ ሁኔታ አገራችንን የሕሊና ህመም በሚፈጥር አስፈሪ ሁኔታ ላይ ጥለዋታል። ኃላቀርና እውቀት አልቦዎቹ ህውሓቶች ተስፍ አስቆራጭ በሆነ መልኩ ሃገሪቱ ዘርን መሠረት ባደረገ መልኩ እንድትከፋፈል አድርገዋል። የጎሳና የዘር ክፍፍሉ ከምድራዊ ሕይወት ተሻግሮ በእምነት ተቋማት ውስጥ ዘልቆ በመግባቱ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ከመንፈሳዊ መላሸቅ ጎን ለጎን ሃይማኖታው ውድቀት ተከስቷል። የተከበሩት ሲኖዶስና መጅሊሶች ለፓለቲካ ስልጣን ምርኩዝ ሆነው የሚያገለግሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ፓትሪያሪኩም ሆነ የመጅሊሱ መሪዎች ተጠያቂነት ለህውሓት የደህንነትና ፀጥታ ቢሮ ሆኗል።

የሆነው ሆኖ ኢትዮጵያ የተጋረጠባት አደጋ በወሳኝነት ከውስጥ ነው የተባለበት ምክንያት ይሄ ነው። የመጪውን ዘመን በፍራቻ እንድንመለከተው የሚያደርገው የድሮው ከውጭ ወራሪ ጋር የሚደረግ የብሔራዊ ነፃነት ትግል ሲሆን፤ ይህኛው ደግሞ በሃይማኖትና ጎሳ ከፋፍለው ከሚገዙ የውስጥ ኃይሎች ጋር የሚደረግ የነፃነት ትግል ነው። በዚህም ምክንያት የትግል አውድማው እጅግ ከባድና ቀድሞ ከነበረው ጋር ለየቅል የሚታይ ይሆናል። ዛሬ! ኢትዮጵያን እየከፋፈለ ያለው እንግሊዝ አይደለም። ዛሬ! በቅኝ ግዛት ሊይዘን የፈለገው ጣሊያን አይደለም። ዛሬ! አንገታችንን ሊቆርጡ የሚመጡት ደርቡሾች አይደሉም። ዛሬ! አምስት ኮከብ ስለው ኢትዮጵያን ሊበታትኑ የሚመጡት ሶማሌዎች አይደሉም።

***

ወደ ተነሳንበት ስመለስ የዛሬው መጣጥፌ መዳረሻ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎም ኪነ-ጥበብ ሙያተኞች ከድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁን ሊቀስሙት የሚገባ አንድ ተጨማሪ ተሞክሮ ለማከል በማሰብ ነው። ይኸውም ቴዲ አፍሮ “ኢትዮጵያ” በሚለው አልበምም ሆነ በተከታታይ በሰጣቸው ቃለ-መጠይቆች የገለጠው ሦስተኛ ቁምነገር ይሆናል። ስለ መቆጨት! ሰለመናደድ። አርቲስቱ ርዕቱ በሆነ አንደበቱ መቆጨት አለብን! መናደድ አለብን! ቁጭት ከሌለ ወደለውጥ ለመሄድ ኃይል አናገኝም ያለበት ይሆናል። ይህም ወቅታዊውን የአገራችንን ሁኔታ መገንዘብ መቻሉን የሚያመለክት ነው። በሌላ በኩል የሚቀጥለው ጉዞ ካለፈው ምን ያህል የከበደና የሚያስጨንቅ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በእርግጥም እንደዚህ አይነት ጠመንጃ ነካሽ ክፉ ስርዓት ለመገላገል በንዴት የተሞላ ተስፋ አስጨራሽ ትግል የሚጠይቅ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ነው። እልህ አስጨራሹ የሕዝብ ትግል ማዕከል ከፓለቲካ፣ ከኢኮኖሚና መንፈሳዊ እግረ-ሙቅ የመላቀቅ በመሆኑ በቁጭት መጓዝን ግድ ይላል። አረረም መረረም ሃገራችን የተደገሰላት የእርስ በእርስ እልቂት እየታወቀ ዝምታ ፋንዲያ እንጂ ወርቅ ሊሆን  አይችልም ።

እናም አርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን መቆጨት አለብን! መናደድ አለብን! ቁጭት ከሌለ ለውጥ የለም ብሎ ሲገልጥልን ምን ዓይነት መልዕክት እያስተላለፈልን እንደሆነ ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል። ሌላው ቢቀር ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገር በቀል ፋሽስቶች የተፈፀመው የጅምላ ግድያ፣ የጭካኔ በትርና ሰጥ ለጥ አድርጎ ለመግዛት የሚካሄደው አፈና ለምን አላስቆጨንም ብለን ከራሳችን ጋር ሙግት መፍጠር ችለናል ወይ? ብለን መጠየቅ ያስፈልጋል። የቅርብ ጊዜ ክስተቱን ብንወስድ እንኳን የመከላከያ እና የፀጥታ ኃይሉ ከህዝብ አብራክ እንዳልወጣ ሁሉ ህዝብን በጅምላ ሲጨፈጭፍ በስሜት ውስጥ ሆነን “ሞት ለገዳይ!” በማለት ህዝቡን አስቆጨን። ታዲያ መስከረም ሳያልቅ ለምን ወደ ሰገባው በፍጥነት ተምዘግዝገን ገባን ብለን ማንሳት ይኖርብናል። አርቲስቶቻችን ባቀነቀኑት የትግል መዝሙር ምክንያት ህዝቡን ከጫፍ እስከ ጫፍ በንዴት ፈንቅለን አስወጥተን ስናበቃ የራሳችንን እግር ለምን ጎተትን ብለን መወቃቀስ ይኖርብናል። እንደኔ እንደኔ ዛሬ የመወቃቀስና የመነቃቀፊያ ጊዜ ነው። ገና አልረፈደም። እንደውም በሃቅ እንነጋገር ከተባለ “እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል” በሚል የእንስሳይቱ ፍልስፍና የሚመራው የህወሓት አገዛዝ ከትላንት እና ዛሬ በከፋ ሁኔታ ነገ ከነገ ወዲያ የሚፈፅመው ወንጀል የከፋ ይሆናል። እናም ተወዲሁ እርምት ወስዶ በቁጭት መራመድ ያስፈልጋል። ዛሬም “ማንነት የራስ ነው፥ አገር የጋራ ነው፥ ቁልፍና ማሰሪያው፥ ኢትዮጵያዊነት ነው!” ከሚለው መዝሙር ጋር በተጓዳኝ “ሞት ለገዳይ” መቀንቀን ይኖርበታል።

እንግዲህ ከላይ በጥቂት የዘረዘርኳቸው ነጥቦች የሚያመላክቱን ነገር በርካታ ጉዳዮች ደም የሚያስተፋና ፀጉር የሚያስነጭ ንዴት የሚፈጥሩብን ሊሆን በተገባ ነበር። ከላይ እንደተገለጠው ባለፈው ሁለት ዓመት ብቻ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ኮንሶ፣ አኝዋክ፣ ሱማሌ ውስጥ የተፈፀመው ግፍ ኢትዮጵያ ውስጥ መወለድን እስከመጥላት የሚያደርስና ዘግናኝ ነው። ገደብ የለሽ የስልጣን ጥማት ተሳክረው በጥይት አርከፍክፈው በገደሉት የልጅ ሬሳ ላይ ወላጅ እናት መቀመጣን ስንሰማ “አናኛቱ (ለእኔ ያድርገው)” ማለት የሚገባ ነበር። ኢትዮጵያዊ አባት ለአሳር ነው የተፈጠርከው የተባለ ይመስል በመከራ ያሳደጋቸውን ሦስት ልጆቹን በአንድ ቀን በጥይት ተደብድበው ሬሳቸውን ሲታቀፍ መመልከት በድጋሚ “አናኛቱ” ያስብላል።…አናኛቱ !…ለእኔ ያርገው !!

***

በነገራችን ላይ ይሄ “አናኛቱ” በሚል ርዕስ የተቀነቀነው የቴዲ አፍሮ ዘፈን በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ምን ያህል ቁጭት እንደፈጠረ ለማወቅ ብዙ መጓዝ አልጠየቀኝም። ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ያሠፈረው ለዚህ አባባሌ በምሳሌነት ሊነሳ የሚችል ነው። የጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ ከፊል ጽሑፍ እንደዚህ ይላል።

“… የሌሎችን ስሜት ባላውቅም ቴዲ አፍሮ በሰሞኑ ዘፈኑ በአፋን ኦሮሞ ያዜማት ባለሁለት ስንኝ መልዕክት ቢያንስአስለቅሳኛለች። ሁለት የአፋን ኦሮሞ ስንኞች (“አኩማ ባቴ ሓፍቴ፤ ሙጫኮ በርባደቤ አዱን ዴቢን አቹማ ነፌ”) በእነዚህ የአማርኛ ስንኞች ሊገለፅ ይችላሉ (ትርጉም የእኔ)

አባትና ልጅ

ትመጣለች ብዬ ደጅ ደጁን ሳይ፣

ወድቃ ቀረች ልጄ አውራ መንገድ ላይ

ወንድ ልጄም ወጥቶ ሊፈልግ እህቱን

እርሱም ጎዳና ላይ ተቀማ ህይወቱን።

በሠላም ከወላጆቻቸው ተለየተው ወጥተው በጎዳና ላይ በወያኔ ጥይት ወድቀው ለቀሩት እህትና ወንድሞቼ  እንደገናእንዳለቅስ አድርጎኛልና!” ይለናል።… አይዞን በፍቄ!… አናኛቱ! … ለእኔ ያድርገው!

***

አርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን መቆጨት አለብን! መናደድ አለብን! ቁጭት ከሌለ ለውጥ የለም ብሎ ሲገልጥ ሌላ ማስተላለፍ የፈለገው ቁምነገር ያለ ይመስላል።  የህወሓት አገዛዝ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለው ንቀት ገደብ የሌለው መሆኑን ማሳየት። እርግጥ የህወሓትን ባህርያት ዘልቆ ለተመለከት አንድ የማይካድ ሃቅ ላይ ይደርሳል። ይኽውም ህወሓት ከፍጥረቱ ጀምሮ የተፈጠረበትን የበታችነት ስሜት ለመደበቅ ከሚጠቀምባቸው ስልቶች አንዱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን ንቀት ማሳየት ነው። ህወሓት የኢትዮጵያን ታሪክ አናንቆና በመቶ ዓመት ገድቦ ያሳያል። ህወሓት በደማቸውና ባጥንታቸው የዛሬዋ ኢትዮጵያ አውርሰው የሄዱትን ነገስታት የጦር አበጋዞች ያበሻቅጣል። አልፈው ተርፈው የኢትዮጵያን የምስረታ ሂደት እንደወረራና ቀኝ ግዛት በመቁጠር ከታሪክ ሂደትና ከሕብረተሰብ ዕድገት ጋር የሚጋጭ አድርጎ በማሳየት ነገስታትን አመድ አፋሽ ያደርጋል። ዛሬ ዛሬ ስብሃት ነጋን የመሳሰሉ የህወሓት የጡት አባቶች የተለየ አቋም ቢያራምዱም ፓርቲው ደደቢት ላይ ከተመሰረተ ጀምሮ ኢትዮጵያን በቀን ገዥነት የሚከስ ድርጅታው ፕሮግራም ቀርፀው ሲንቀሳቀሱ ነበር። “ያደቆን ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም” እንደሚባለው ዛሬም የአመለካከት ለውጥ ማምጣት አቅቷቸው ሲንቧተሩ የታያል። ለክፋትና ለዘረኛ አላማቸው ያለመታከትና ያለዕረፍት እስከ መጨረሻው ቤተሰብ ድረስ በመዝለቅ ሰንሰለታቸውን “አንድ-ለአምስት” በመዘርጋት ላይ ናቸው። ሌላው ቀርቶ የጫት፣ ካቲካላና ጠላ ቤቶች ወግ ከጊዜ መግደያነት ተሻጋግረው የጎሳ ፓለቲካና ትውልድ መከፋፈያ መድረክ ሆነው እንዲቃኙ ተደርገዋል። በምርቃናና ስካር መንፈስ ውስጥ ተኹኖ እንኳን አገዛዙን መተቸት የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

ይህም ሆኖ በእነዚህ ከይሉኝታ የተሰናበቱ ልበ-ወፍራሞች ድርጊት አንቆጭም። ተራ በተራ ሱሪያችንን ዝቅ አድርገው እየገረፉን በውስጣችን ንዴት የለም ። እየደረሰብን ባለው በትር የሞራል መላሸቁን ተከትሎ የፍርሃት ቆፈን ዙሪያችንን ከቦናል ። የብሎኬት ግድግዳ እያስገፉን “ እኛ ወያኔዎች አንዲህ ነን !” በማለት እያላገጡብን ቢያንስ የየጁን ደብተራ ቅኔና ቀራርቶ ማሰማት አቅቶናል ። እናቶቻችንን ፥ እህቶቻችንንና ሚስቶቻችንን መለ-መላቸውን እያስቆሙና ብልታቸው ውስጥ በረዶ እየጨመሩ እንደሚያሰቃዩ እየሰማን መናደድ አልቻልንም። ኧረ ለመሆኑ! አንዲት የፌስቡክ ጦማሪ “ራቁቴን አቁመው ተሳለቁብኝ” ከማለት ውጭ ምን እንድትነግረን እንፈልጋለን?… አንዲት የፖለቲካ እስረኛ “ጡቴን በኤሌክትሪክ ጠበሱት” ብላ ከመናገር በላይ ምን አይነት ማስረጃ ይገኛል?… ወንድ ልጅ “ብልቴን ስላኮላሹት ወደ ሚስቴና ቤተሰቦቼ አልሄድም ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ይወቅልኝ” ብሎ ኑዛዜውን ከማሰማት በላይ ሌላ ምን ይጠበስልን? እስቲ ለአንድ አፍታ ቆም ብለን አናስብ! ራሳችንን እንጠይቅ! ለምን መናደድ አልቻልንም?…. ለምን መቆጣት አልቻልንም?…. ለምን መቆጨት አልቻልንም?

***

ይህንን መጣጥፍ ለመቋጨት እፈልጋለሁ። መጣጥፉን እየከተብኩ ያለሁት በኢሳት ቢሮ ውስጥ በሚገኘው የሙሉጌታ ሉሌ መታሰቢያ መጽሃፍት ቤት በመሆኑ በእሱ አስተያየት ልቋጭ። አንጋፋው ብእረኛ በጦቢያ መጽሄት ላይ “ ሰው ስንፈልግ ባጀን “ በሚለው መጣጥፉ በቁጭት የተሞላ መናደድ ለስር ነቀል ለውጥ እንደ-ቅድመ ሁኔታ መታየት እንዳለበት ያስገነዝባል ። እርግጥም መናደድ ትልቅ ነገር ነው ። መናደድ ብንችል አንዱ የዚች ሃገር ማዳኛ የትግል መቅድም ይሆናል። ግን ለመናደድ ለመብሸቅና ከተቻለም እህህ ብሎ ደም ለመትፋት ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል ።ታዲያ! ችግሩ አንናደድም ።ከጊዜያዊ ብሽቀት ወጥተን ጨጓራችን እስኪላጥና ቆሽታችን ድብን እስኪል ንዴት የወለደው ቁጭት መፍጠር አልቻልንም ። እንደ መስቀል ወፍ ብቅ ጥልቅ የሚለው ንዴታችንም ወደ ተግባር መቀየር ተስኖታል ። ለምን ይሆን? ራሳችንን እንጠይቅ።

“ነፍጠኛ” – “ትምክህተኛ” – እየመጡ ላሉት መጽሐፎቼ መንደርደሪያነት !

(መላኩ አላምረው)

የዛሬ ሦስት ዓምት ነው። በአንድ መንግሥታዊ “የበጀት መዝጊያ” ስብሰባ ላይ (የመንግሥት ሠራተኛ በመሆኔ) ታድሜያለሁ። የስብሰባ አጀንዳው “የተቋሙ ያለፈው በጀት ዓመት አፈፃፀምና ቀጣይ አቅጣጫዎች” የሚል ሆኖ ሳለ ክቡር ሰብሳቢ በምንም በምንም እያሳበበና እያጠጋጋ እነዚህን “ነፍጠኛ” እና “ትምክህተኛ” የሚሉ ቃላትን ደጋግሞ በመጥራት አዛገኝ። “ነፍጠኛውና ትምክህተኛው የአማራ ሥርዓት እንዲህ አድርጎን… እንዲህ ፈጥሮን… ላለፉት ሺህ ዓመታት ብቻውን ተጠቅሞ… አሁን ዕድሜ ለኢህአዴግ ሁሉም እኩል ተጠቃሚ ሆነ…”… በቃ ይወርድብን ጀመር። አማላክ በፈቃዱ ከአማራ ክልል የፈጠረን ኢትዮጵያውያን (ያውም ሙልጭ ያልን የድሃ ልጆች) የዚህ ትችት ሰለባ መሆናችን ግርምምም ብሎኝ ስሰማ ቆየሁ። በኋላ የጥያቄና አስተያየት ዕድል ሲሰጥ እጅ ለማውጣት የቀደመኝ አልነበረም። ተሰጠኝ። በንዴት ተናገርሁ።
.
“ሲጀመር አማራ ልዩ ተቃሚ መሆኑ ያስቃል። ሲቀጥል ‘ነፍጠኛ’ እና ‘ትምክህተኛ’ የሚሉ ቃላትን ትርጉም ሳትረዱ ብዙ በማውራታችሁ ማፈር ነበረባችሁ።”
ታዳሚው ፀጥ አለ።
“ፀጥ አለ በእናንተ ቤት እነዚህ ቃላት ስድብ ናቸው። ታሳዝናላችሁ። ሳያስተውሉ የሚሰሟችሁን የእናንተ ቢጤዎችም ታስታላችሁ። ለእኔ ግን ነፍጠኝነት ጀግንነት ነው። አነጣጣሪነት፣ ኢላማ መችነት፣ ጠላት ድል ነሽነት። ምናልባት ይህ ስያሜ ለአማራው የተሰጠው በጣልያን ጊዜ ባደረገው ጠላትን ለይቶ የመምታት ጀግንነቱ ይሆናል። እናንተ እንደምትሉት በወንድሞቹ ላይ ግፍ የፈፀመ አማራ የለም። ሕዝብን በዚህ መልኩ መዝለፍ አላዋቂነት ነው። ቢገባችሁ ነፍጠኝነትን ለአሁኑ የድህነት ትግል በተጠቀማችሁበት። ሕዝቡ ሁሉ ነፍጠኛ ሆኖ ድህነትን እንዲዋጋ በሰበካችሁበት። በነፍጠኝነት አነጣጥሮ የድህነትን ጭንቅላት መትቶ መጣል ያባቶቻችን ልጆች ያደርገናል ባላችሁትና ለበጎ በተጠቀማችሁበት። ይህንን ቃል ላንድ ብሔር ስድብ ለማድረግ መሞከር ትርፉ ምን ይሆን? ነፍጠኛ ማነው? አዎ በላይ ዘለቀ ነፍጠኛ ነው። ጀግና አላሚ፣ ጠላትን አነጣጥሮ የሚመታ ነፍጠኛ። ግን በላይ ብቻ ነው? በፍጹም። ራስ አሉላ ነፍጠኛ ነው። ጠላትን ለይቶ የሚመታ ጀግና ነፍጠኛ። አብዲሳ አጋም ጀግና ነፍጠኛ ነው። ምነዋ ይህ ስም ላንድ ብሔር ተሰጠ? ለእኔ ግን ሁሉም ኢትዮጵያውያን ነፍጠኞች ነን። ለጠላት የማንበረከክ አልሞ ተኳሾች። ይህ ደግሞ አኩሪ እንጅ አሳፋሪ አይደለም። ስድብ ልታደርጉት የምትደክሙ ሁሉ ባለማወቃችሁ ልክ ራሳችሁን ትሰድባላችሁ። አዎ የነፍጠኛ ልጅ ነፍጠኛ ነኝ። አያቶቼ ጥይትን ወደ ጠላት ተኩሰው ነፃ ሀገር አስረከቡኝ። እኔ ደግሞ የፍቅር ባሩድን ታጥቄ የአንድነትን ፍላፃ በጥበብ እየተኮስሁ ዘረኝነትንና ጥላቻን አነጣጥሬ የምመታ ነፍጠኛ ነኝ። መቼም በዚህ ስም አላፍርም።
ትምክህተኛም ነኝ። ትምክህት እናንተ እንደምትሉት አይደለም። የአማራ ትምክህቱ አንዲት ሀገሩ እንጅ ሌላ ምንድነው? በሀገር የማይመካ እርሱ ምንድነው? ትምክህተኛ ልቦች ናቸው ለሀገር መስዋዕት እስከመሆን የፀኑት። ካሣ (አፄ ቴዎድሮስ) ሀገሩን አንድ ለማድረግ የተነሳው በትምክህተኝነቱ ነው። ለሀገሬ እኔ አስገልጋታለሁ ማለት ነው ትምክህት። ይህ ስህተት ነው? የበላይ ዘለቀ የአርበኝነት ስንቁም ትምክህት ነው። ሀገሬን ነፃ የማደርጋት እኔ ነኝ ብሎ ጠላትን እንዲወጋ ያደረገው ትምክህቱ ነው። ግን ትምክህተኞቹ እነርሱ ብቻ አልነበሩም። በመላው ሀገሪቱ ነፍጥ አንግበው ጠላትን የተዋጉ ሁሉ ልባቸው በትምክህት የተሞላ ልበ ሙሉዎች ነበሩ። ለሀገራችን ያለናት እኛ ነን… ብለው የተመኩ ጀግኖች ናቸው ነፃ ምድርን ያወረሱን። ትምክህት እንዴት ባለ ትርጉም ስድብ ሆነ? ለትምክህት ‘እኔ ብቻ’ የሚልን ራስ ወዳድነት ማን ሰጠው? ይልቅ ምናለ ትውልዱ ሁሉ በሀገሩ እንዲመካ ብታደርጉት። ሁሉም ልቡ በትምክህት ተሞልቶ ለዚህች ሀገር ያለናት እኛ ነን… ከድህነቷ የምናወጣትም እኛ… ቢል ምናለበት? የኃያላን ሀገሮች የብልጽግና ምሥጢር ትምክህተኝት መሆኑን ሳታውቁ ነው እንዴ ሀገር የምትመሩት??? ጃፓናውያን እንዳይስቁባችሁ… ጀርመኖችም እንዳይሳለቁባችሁ። ይልቅ ይህንን ትውልድ ከአንዲት ሀገር ትምክህቱ አውርዳችሁ ዘረኛ ስታደርጉት ነው ማፈር ያለባችሁ። በአንዲት ሀገር ትምክህት ያልተሞላና የተከፋፈለ ሕዝብ ይጠፋልና። ደግሞ ከአማራ ሕዝብ ራስ ውረዱ። እኔ አንዱ የዚህ ሕዝብ ልጅ ነኝ። በጣም ደሃ ቤተሰቦቼን ተምሬ ላግዝ የምለፋ ባተሌ ሆኜ እያለ ልዩ ተጠቃሚ ነበርህ ስትሉኝ እንዴት ልስማችሁ? የዘመዶቼን የኑሮ ሁኔታ እያወቅሁት ከልዩ ተጠቃሚ ሕዝብ እንደመጣሁ ስትነግሩኝ አልሰማችሁም። እኔ የተማርሁት ወንድሞቼ ከክልላቸው ርቀው በመሄድ የቀን ሥራ እየሰሩና እናት አባቴም እየተበደሩ ነው። ይህንን ያደርጉት ተመርቄ እንደምመልስላቸው ተስፋ አድርገው ነው። ያልመለስሁት ዕዳ አለብኝ። በዚህ ዕዳ ውስጥ የምኖር ተስፈኛ ወጣት በማንም ልሰደብ አይገባኝም። ሀገሬን የምወዳት በሀብቷ አይደለም። በሀገርነቷ ብቻ እንጅ።”
.
በስሜት ብዙ ተናገርሁ። ተሰብሳቢው በጭብጨባ አገዘኝ። ልቤ በወገኔ ተመካ።
እናም ከዚያች ዕለት ጀምሮ ስለ “ነፍጠኝነት እና “ትምክህተኝነት” አብዝቼ አስብ ጀመር። እነዚህን ቃላት ለበጎ ዓላማ መጠቀም እየተቻለ ለምን ለስድብነት እንደተመረጡ አልገባህ አለኝ። ማንም ምን ቢል ግን እኔ በእነዚህ ቃላት መሸማቀቅ እንደሌለብኝ ወሰንሁ። ወስኖ መቀመጥ ብቻም ሳይሆን “ነፍጠኛ እና ትምክህተኛ” ሆኜ ለሀገር አንድነትና ለሕዝብ ፍቅር የራሴን ድርሻ ለመሥራት ተነሳሳሁ። ምንም ነገር ባይኖረኝ ቢያንስ ሀገሬ በደሃ ገበሬዎቿ ግብር አስተምራ ያስጨበጠችኝ መጠነኛ እውቀት አለችኝ። ይህንን ለበጎ መጠቀም አለብኝ።
.
አዎ አባቶቼና አያቶቼ ነፍጠኞች ነበሩ። ጠላትን ለይተው አነጣጥረው የመቱና ነፃ ምድር ያስረከቡኝ። እኔም ነፍጠኛ መሆን እችላለሁ። አሁን ላይ ሀገሬን እየበከላት ያለን “ዘረኝነት” የሚባል ጠላት ለይሼ ለመምታት የፍቅርን አረር በጥበባዊ ስንኝ መተኮስ እችላለሁ። ድህነትም በነፍጠኞች ተለይቶ ሊመታ የሚገባው አደገኛ ጠላት ነው። ይህ ሁሉ ግን ያለ አንዲት ሀገር ትምክህት አይቻልም። በሀገሬ የምመካ ትምክህተኛም ነኝ። ለሀገሬ በጣም ያማስፈልጋት ውድ ልጇ ነኝ።
ብዕሬን እንደ ነፍጥ አነሳለሁ። የፍቅርን ባሩድ እታጠቃለሁ። የሀገሬን ትምክህት እደርባለሁ። እያነጣጠርሁ እተኩሳለሁ። የሀገር ልዩ ጠላቶችም ይመታሉ። ይህንንም ለማሳካት ሁሉንም አስተባብራለሁ። ልክ እነ በላይ ዘለቀ ከመላው ሀገሪቱ የተነሱ አርበኞችን አስተባብረው ጠላትን እንዳንበረከኩ… ለእኛም ይቻላል። እነ አብዲሳ አጋ በባዕድ ሀገር ቅኝ ግዛትን እንደታዋጉ ለእኛ ይቻላል።

ዘረኝነትን ለመውጋት ነፍጠኛ መሆንን የወደደ ሁሉ ሳያፍርና ሳይሸማቀቅ መነሳት አለበት። ዘረኝነት ሲሸነፍ ድህነትም እጅ ይሰጣል። በአንድነትና በፍቅር በታሰረ የተባበረ ክንድ የማይሸነፍ ጠላት የለም።
….
ይህንን ሁሉ የምለፈልፍላችሁ….. ከነገ ጀምሮ በፌስቡክ መተዋወቅ የሚጀምረው የመጀመሪያው መድበሌ “ስያሜ” ከእንዚህ ጉዳዮች ጋር የሚያያዝ መሆኑን ለመጠቆም ነው። (ሌላውም ቀጣይ መጽሐፌ ከእነዚህ ጉዳዮች አይርቅም።)
ርዕሱን መገመት ይቻላል….. የማይቻለው መድበሉን አለመግዛት ብቻ ነው።
መልካም ሰንበት።

“ነፍጠኛ” – “ትምክህተኛ” – እየመጡ ላሉት መጽሐፎቼ መንደርደሪያነት !

melaku alameraw

ፍረጃ….!!

 

የባለፈው ቅዳሜ ከ 3 ጉዋደኞቼ ጋር ለምን እራት አንበላም ብዮ ስላሰብኩ እና የተጣሉትን ሁለት ጉዋደኞቼን ለማስታረቅ በማሰብ በአንድ ሬስቶራንት ተገኝተን ነበር:: ግን እርቁ ያሰብኩትን ያህል ከባድ ሳይሆን ወድያው ገና ከመጀመሬ ”እረ እኛ ሰላም ነን … እንዲሁ ባለመግባባት ነው”… ብለው ነገሩን ባጭር አቀለሉልን:: እኔም ደስ አለኝ እራት ተበላና መጠጥ ጀመሩ ከዛ ኣንዳንድ መባባል አይጀምሩም….!?
ማን ይያዛቸው…. ቤቱ ታመሰ… ገላጋዮች መጡ እነሱ ማንን ፈርተው… እኔ በሃፍረት አንገቴን ደፋሁ…

እኔ እኮ የሚገርመኝ እንዴት ሰው በንግግር ማመን ያቅተዋል? ሁሌስ ጦርነት ለምን ይቃጣናል? በሃሳብ መረታት ድንቁርና በሃሳብ መርታትስ ምሁርነት አድርጎ የደነገገው ማነው?? ከሚያውቅ ሰው እኛስ የማናቀውን ብንማማር ነውሩ ምኑ ላይ ነው?

እዩት በየሚድያው አንድ አዋቂ ፣ ምሁር ወይም ባለሙያ ሰው ወጥቶ ሃሳቡን ቢያካፍል ሊያውም ከበቂ ማስረጃ ጋር ሰንቶቻችን ነን በቅንነት ሰምተን ነገ የተሻለ ሰው ለመሆን የምንጥረው? አንዳንዶቹማ አወቁም አላወቁም ወይም ቲንሽ ጥራዝ ነጠቆች…. የስድብ የጭቃ ጅራፋቸውን በማውረድ በረጅም ምላሳቸው ባዶ ጭንቅላታቸውን ያሳዩናል::

ሂስ መሰጣጣት ፣ መተቻቸት ፣ ወደ የተሻለ የእውቀት ደረጃ እንደሚያስኬድ እንዴት መረዳት ያቅተናል?
ሁሉም በአንድ ካልተፈረጀ ፣ ወይም የብዙሃኑ ሰፊ አፍ እና አላዋቂዎች ጭንቅላት ተርታ ካልሆነ… የግድ መንጉውጠጥ እና መሰደብ አለበት?

ያ ሰው አክባሪነታችን ፣ ደግ ፣ ሰው ቀና ብሎ የማያየው ፣ ፈርሃ እግዚአብሄር የነበረው ኢትዮጵያዊ ወዴት ሄደ??
በፖለቲካው ፣ በህክምናው ፣ በሳይንሱም ፣ በታሪካችን … ብቻ በሚነሱት ነገሮች ሁሉ ጭፍን ጥላቻ ያለ ምንም የመሞገቻ ሃሳብ ብቻ የስድብ ናዳ ማውረድ የእለት ተእለት ስራቸው ኣርገውታል::
ማነው እንግዲህ የሚመራን እና የምንሰማማበት? ማንስ ተናግሮ ነው የሚደመጥ ?
መቼም ይቺ ኢትዮጵያ ሃገራችን በጻድቃን ጸሎት እና በእግዚአብሄር ቸርነት ነው እንጂ እንደኛ አለመስማማት ገና ድሮ ተበታትነን በጠፋን ነበር::

ኣያንዳንዱ ሰው ይፈረጃል ፣ ስም ይወጣለታል ፣ ጥሩ አረክ ጥሩ ሰራህ ማለት ለኛ ሞታችን ነው በዛውም አለማወቃችን ይጋለጥብናላ…!

ሃገራችን መፈራረስዋ ህዝቡም እርስ በእርስ መተላለቁ የደም ጥማት ያለባቸውና እርኩስነት የተጠናወታቸው ፥ በውጭው አለም በተለያየ ቦታ ተቀምጠው የደሃውን እልቂት የሚሰብኩ ፥ ሰይጣን የተጠናወታቸው ፥ የጭራው ቁራጮች ”ወያኔ ህዝቡን በዘር ከፋፈለ”… ብለው እራሳቸው ደሞ ትልቁን ኢትዮጵያዊነት ትተው በጠባብ ጎጠኝነት እና መንደሬነት ተደራጅተው ዘርን ሲሰብኩ ሲታይ ከዚህ በላይ ምን የሚያም ነገር አለ?!!

የሃገራችንን ሰላም መሆን የማይፈልጉት አሜሪካኖች በአንድ በኩል ፣ አውሮፓውያን በሌላ በኩል ፣ እንዲሁም አረብ ሃገራት በሶስተኛ ወገን ለራሳቸው የተለያየ የግል ጥቅም ቲኒሽ ፍርፋሪ ለያንዳንዱ ጎጥ በመወርወር ህዝብን በሃይማኖት በዘር በመከፋፈል ፥ ”አንተ ተረግጠሃል….፣ ሌላው ጨቁኖሃል….ወዘተ” እያሉ የሚያደርጉብን ድራማ የሚገባን መቼ ይሆን?

እስኪ ሰለ ሊቢያ እናስብ ህዝቡ ኑሮው ከአውሮፓውያኑ በላይ ነበር የ ጋዳፊ ሃሳብ ከ ሃገሩ አልፎ ለአፍሪካ የሚሆን… ለምሳሌ:- ሳተላይትን ለአፍሪካ በማስገጠም በአመት የምንገብረውን ውድ የስልክና የኢንተርኔት ወጪ ሊቀንስልን ሌላው ደሞ አፍሪካውያን ወርቅ ሰጥተን የወረቀት የብር ኖት ሰለሚመልሱልን እሱ አግባብ እንዳልሆነና ወርቅን በወርቅ ማለትም ፥ ለምሳሌ ነዳጅ ከሊቢያ ቢፈልጉ በወረቀት ሳይሆን በወርቅ እንዲቀይሩ በማለቱ እድሜ ለነ እንግሊዝ በአማጽያን ስም ሰውየውን እንዳልሆነ አርገው ገለው ሃገሩን ዘርፈው ለማያባር የእርስ በእርስ ግጭት ዳርገው እነሱ እጃችውን አጣምረው እያዩ ነው::

ኢራቅ ታላቁዋ አሜሪካ ሳዳም ሁሴንን ሰቅላ ነዳጃቸውን ዘርፈው እሳካሁን የማይበርድ እሳት አቀጣጥለው መውጣታቸውን የቅርብ ጌዜ ትውስታ ነው::

በተባበሩት መንግስታት ህግ መሰረት ጦርነት ላለበት ሃገር መሳርያ መስጠትም መሸጥም ክልክል መሆኑ ስለሚታወቅ ሳውዲአረብያ ከጀርመን የገዛችውን መሳርያ ለሲርያ መንግስት ማስተላለፉዋን ሁሉም ሰው የሚያውቀው ታሪክ ነው::

እነዚህ ሰዎች እኮ ይችን አለም ቁማር እየተጫወቱባት ነው:: ”ሃበሻ ቢመቀኝ የአንድ ቀን እራትህን ነው ነጮቹ ሲመቀኙ ግን የዘላለም እራትህን ነው የሚነጥቁክ” አለ አንድ ወዳጄ … እውነቱን ነው!

እረ ኢትዮጵያውያን እንንቃ! ሃገራችን የእኛ እና የእኛ እኮ ብቻ ናት:: ምን ብንበጣበጥ በዙ ሺህ ሰው ቢያልቅ ማንም ዞር በሎ እንደማያየን የሴርያን ታሪክ አያየን መፍረድና መማር እንችላለን:: በሴርያ እስከ 465 ሺህ ህዝብ በጦርነቱ እንዳለቀ መረጃው ያመለክታል:: እረ ወገን ልቦናችንን ከፍተን ሰፋ አድርገን እንይ… ጥቂት ቁንጽል የሶሻል ሚድያ ሃሳብ እኛን ለምን ያናውጠናል?

እባካችሁ ሰው በሚመራን ሳይሆን በተሰጠን የማገናዘቢያ ህሊና እስኪ እንመርምር ፣ እናንብብ ፣ ለመረዳት እንሞክር መጽሃፉን ከሽፋኑ አይተን ሳይሆን መፍረድ ፣ደጋግመን አንብበን ቢሆን ጥሩ ነበር:: ያኔ ትክክለኛ ፈራጁ ማንም ሳይሆን እኛው እራሳችን ብቻ እንሆናለን::

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

Alex Ethiopia

cropped-soccer-ethiopia.jpg

Ethiopia blocks internet ‘to stop exam cheats’

Hands holding smartphones

/BBC News/ Internet access across Ethiopia has been blocked to prevent national exam papers leaking online, a government spokesman has claimed.

“The shutdown is aimed at preventing a repeat of leaks that occurred last year,” Mohammed Seid at the Office for Government Communications Affairs, told the Reuters news agency.

In 2016, the country banned access to social media sites after university entrance exams were posted online.

But some have queried this explanation.

“We are being proactive,” Mr Seid added, referring to exams that are due to finish on 8 June.

“We want our students to concentrate and be free of the psychological pressure and distractions that this brings.”

Mr Seid is reported to have said that only social media sites had been blocked, but sources in Ethiopia told the BBC that there was widespread internet disruption, affecting both mobile networks and fixed line internet services.

A state of emergency has been in effect in Ethiopia since October, following anti-government protests.

Mobile internet access has been disabled on other occasions recently, including a period of a few weeks last year.

Ethiopia blocks internet ‘to stop exam cheats’