ፍረጃ….!!


 

የባለፈው ቅዳሜ ከ 3 ጉዋደኞቼ ጋር ለምን እራት አንበላም ብዮ ስላሰብኩ እና የተጣሉትን ሁለት ጉዋደኞቼን ለማስታረቅ በማሰብ በአንድ ሬስቶራንት ተገኝተን ነበር:: ግን እርቁ ያሰብኩትን ያህል ከባድ ሳይሆን ወድያው ገና ከመጀመሬ ”እረ እኛ ሰላም ነን … እንዲሁ ባለመግባባት ነው”… ብለው ነገሩን ባጭር አቀለሉልን:: እኔም ደስ አለኝ እራት ተበላና መጠጥ ጀመሩ ከዛ ኣንዳንድ መባባል አይጀምሩም….!?
ማን ይያዛቸው…. ቤቱ ታመሰ… ገላጋዮች መጡ እነሱ ማንን ፈርተው… እኔ በሃፍረት አንገቴን ደፋሁ…

እኔ እኮ የሚገርመኝ እንዴት ሰው በንግግር ማመን ያቅተዋል? ሁሌስ ጦርነት ለምን ይቃጣናል? በሃሳብ መረታት ድንቁርና በሃሳብ መርታትስ ምሁርነት አድርጎ የደነገገው ማነው?? ከሚያውቅ ሰው እኛስ የማናቀውን ብንማማር ነውሩ ምኑ ላይ ነው?

እዩት በየሚድያው አንድ አዋቂ ፣ ምሁር ወይም ባለሙያ ሰው ወጥቶ ሃሳቡን ቢያካፍል ሊያውም ከበቂ ማስረጃ ጋር ሰንቶቻችን ነን በቅንነት ሰምተን ነገ የተሻለ ሰው ለመሆን የምንጥረው? አንዳንዶቹማ አወቁም አላወቁም ወይም ቲንሽ ጥራዝ ነጠቆች…. የስድብ የጭቃ ጅራፋቸውን በማውረድ በረጅም ምላሳቸው ባዶ ጭንቅላታቸውን ያሳዩናል::

ሂስ መሰጣጣት ፣ መተቻቸት ፣ ወደ የተሻለ የእውቀት ደረጃ እንደሚያስኬድ እንዴት መረዳት ያቅተናል?
ሁሉም በአንድ ካልተፈረጀ ፣ ወይም የብዙሃኑ ሰፊ አፍ እና አላዋቂዎች ጭንቅላት ተርታ ካልሆነ… የግድ መንጉውጠጥ እና መሰደብ አለበት?

ያ ሰው አክባሪነታችን ፣ ደግ ፣ ሰው ቀና ብሎ የማያየው ፣ ፈርሃ እግዚአብሄር የነበረው ኢትዮጵያዊ ወዴት ሄደ??
በፖለቲካው ፣ በህክምናው ፣ በሳይንሱም ፣ በታሪካችን … ብቻ በሚነሱት ነገሮች ሁሉ ጭፍን ጥላቻ ያለ ምንም የመሞገቻ ሃሳብ ብቻ የስድብ ናዳ ማውረድ የእለት ተእለት ስራቸው ኣርገውታል::
ማነው እንግዲህ የሚመራን እና የምንሰማማበት? ማንስ ተናግሮ ነው የሚደመጥ ?
መቼም ይቺ ኢትዮጵያ ሃገራችን በጻድቃን ጸሎት እና በእግዚአብሄር ቸርነት ነው እንጂ እንደኛ አለመስማማት ገና ድሮ ተበታትነን በጠፋን ነበር::

ኣያንዳንዱ ሰው ይፈረጃል ፣ ስም ይወጣለታል ፣ ጥሩ አረክ ጥሩ ሰራህ ማለት ለኛ ሞታችን ነው በዛውም አለማወቃችን ይጋለጥብናላ…!

ሃገራችን መፈራረስዋ ህዝቡም እርስ በእርስ መተላለቁ የደም ጥማት ያለባቸውና እርኩስነት የተጠናወታቸው ፥ በውጭው አለም በተለያየ ቦታ ተቀምጠው የደሃውን እልቂት የሚሰብኩ ፥ ሰይጣን የተጠናወታቸው ፥ የጭራው ቁራጮች ”ወያኔ ህዝቡን በዘር ከፋፈለ”… ብለው እራሳቸው ደሞ ትልቁን ኢትዮጵያዊነት ትተው በጠባብ ጎጠኝነት እና መንደሬነት ተደራጅተው ዘርን ሲሰብኩ ሲታይ ከዚህ በላይ ምን የሚያም ነገር አለ?!!

የሃገራችንን ሰላም መሆን የማይፈልጉት አሜሪካኖች በአንድ በኩል ፣ አውሮፓውያን በሌላ በኩል ፣ እንዲሁም አረብ ሃገራት በሶስተኛ ወገን ለራሳቸው የተለያየ የግል ጥቅም ቲኒሽ ፍርፋሪ ለያንዳንዱ ጎጥ በመወርወር ህዝብን በሃይማኖት በዘር በመከፋፈል ፥ ”አንተ ተረግጠሃል….፣ ሌላው ጨቁኖሃል….ወዘተ” እያሉ የሚያደርጉብን ድራማ የሚገባን መቼ ይሆን?

እስኪ ሰለ ሊቢያ እናስብ ህዝቡ ኑሮው ከአውሮፓውያኑ በላይ ነበር የ ጋዳፊ ሃሳብ ከ ሃገሩ አልፎ ለአፍሪካ የሚሆን… ለምሳሌ:- ሳተላይትን ለአፍሪካ በማስገጠም በአመት የምንገብረውን ውድ የስልክና የኢንተርኔት ወጪ ሊቀንስልን ሌላው ደሞ አፍሪካውያን ወርቅ ሰጥተን የወረቀት የብር ኖት ሰለሚመልሱልን እሱ አግባብ እንዳልሆነና ወርቅን በወርቅ ማለትም ፥ ለምሳሌ ነዳጅ ከሊቢያ ቢፈልጉ በወረቀት ሳይሆን በወርቅ እንዲቀይሩ በማለቱ እድሜ ለነ እንግሊዝ በአማጽያን ስም ሰውየውን እንዳልሆነ አርገው ገለው ሃገሩን ዘርፈው ለማያባር የእርስ በእርስ ግጭት ዳርገው እነሱ እጃችውን አጣምረው እያዩ ነው::

ኢራቅ ታላቁዋ አሜሪካ ሳዳም ሁሴንን ሰቅላ ነዳጃቸውን ዘርፈው እሳካሁን የማይበርድ እሳት አቀጣጥለው መውጣታቸውን የቅርብ ጌዜ ትውስታ ነው::

በተባበሩት መንግስታት ህግ መሰረት ጦርነት ላለበት ሃገር መሳርያ መስጠትም መሸጥም ክልክል መሆኑ ስለሚታወቅ ሳውዲአረብያ ከጀርመን የገዛችውን መሳርያ ለሲርያ መንግስት ማስተላለፉዋን ሁሉም ሰው የሚያውቀው ታሪክ ነው::

እነዚህ ሰዎች እኮ ይችን አለም ቁማር እየተጫወቱባት ነው:: ”ሃበሻ ቢመቀኝ የአንድ ቀን እራትህን ነው ነጮቹ ሲመቀኙ ግን የዘላለም እራትህን ነው የሚነጥቁክ” አለ አንድ ወዳጄ … እውነቱን ነው!

እረ ኢትዮጵያውያን እንንቃ! ሃገራችን የእኛ እና የእኛ እኮ ብቻ ናት:: ምን ብንበጣበጥ በዙ ሺህ ሰው ቢያልቅ ማንም ዞር በሎ እንደማያየን የሴርያን ታሪክ አያየን መፍረድና መማር እንችላለን:: በሴርያ እስከ 465 ሺህ ህዝብ በጦርነቱ እንዳለቀ መረጃው ያመለክታል:: እረ ወገን ልቦናችንን ከፍተን ሰፋ አድርገን እንይ… ጥቂት ቁንጽል የሶሻል ሚድያ ሃሳብ እኛን ለምን ያናውጠናል?

እባካችሁ ሰው በሚመራን ሳይሆን በተሰጠን የማገናዘቢያ ህሊና እስኪ እንመርምር ፣ እናንብብ ፣ ለመረዳት እንሞክር መጽሃፉን ከሽፋኑ አይተን ሳይሆን መፍረድ ፣ደጋግመን አንብበን ቢሆን ጥሩ ነበር:: ያኔ ትክክለኛ ፈራጁ ማንም ሳይሆን እኛው እራሳችን ብቻ እንሆናለን::

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

Alex Ethiopia

cropped-soccer-ethiopia.jpg

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s