ኢትዮጵያዊነት የሰውነት ከፍታ ነው። አማራነትም የብሄራዊ ስሜት ዋልታና ማገር ነው፤ አትውረድ !!!


ኢትዮጵያዊነት የሰውነት ከፍታ ነው። አማራነትም የብሄራዊ ስሜት ዋልታና ማገር ነው፤ አትውረድ !!!
ሰው ሆኖ መፈጠር የድንቅ አእምሮ ባለቤት መሆን ነው። ሰማየ ሰማያትን ቀዶ ማሰብ መቻል ነው። ይህችን አለም ድንበር አልቦ ማድረግ ነው። እንደ መላእክት በመንፈስ መነጠቅ ነው። እኛ ደግሞ በአባቶቻችን የደም ዋጋ የተገዛን የሰማእታት ልጆች ነን። መጫሚያ የሌላቸው የቀደሙት አባቶቻችን ከአራቱም ማእዘን እየፈሰሱ በከፈሉት ዋጋ ነው እዚህ ያደረሱን ስንል ዛሬ የቆምንበት አፈር በነሱ አጥንትና ደም ጭምር ተለውሶ የተሰራ ነው ለማለትም ጭምር ነው። እኛ ደግሞ ከዚህ አፈር ጋር በእትብታችን ጭምር የተገመድን እንደመሆናችን ከዚህች መሬት ብቻ ሳይሆን ከዚህ ማንነት ወደየትም አንሄድም ወደየትም አንወርድም። ይኽ ውበታችን ብቻ ሳሆን እንደ አንድ ሉአላዊ ህዝብ የሚያኖረን ዋስትናችንም ነው። ሰንኮፋው ወያኔና ኩባንያው ነው። መፍትሄው እሱን ነቅሎ መሄድ ነው። ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን ብለን የተስፋ ስንቅ የምንሰንቅና ተስፋችንም ስጋና ደም ገዝቶ እውን እንዲሆን እስከ ሲዖል ዳርቻም ቢሆን ለመጓዝ ቁርጠኛ መሆን እንጅ ከዚህ ራእይ መጉደል ጉዞውን የኋሊት ያደገዋል። በአባቶቹ የወገብ ልክ መሙላት ያቃተውና ወያኔ ሰፍሮ በሰጠው ማንነት እንዲያስብ የተሰራ ብቻ ሳይሆን በዚህም የሚኮራ ትውልድ ከዚህ አካሄድ ጀርባ የተጠመደለትን አደጋ ማየት የተሳነው ብቻ ነው። ሰው ከአመክንዮ ወርዶ ሁሉን ነገር በስጋና በደም ብቻ መመንዘር ሲጀምር ምን ያህል ከእውነት ጋር እንደሚጣላና ሜዳና ገደሉን መለየት እንደሚሳነው ዳር ቆሞ ለሚያየው ሁሉ ፍንትው ያለ እውነት ነው። ችግሩ እርሱ በጎሳ ተስቦ መለከፉ ብቻ አይደለም። መለከፉን አለማወቁ ነው፤ ሌላውም እንደሱ እንዲሆንለት እንቅልፍ ማጣቱ ነው። በሌላ አነጋገር ታምሜያለሁና እናንተም፣ ታመሙ ማለቱ ነው። ሁሉም ታሞ ታሞ አስተማሚ በሚጠፋበት ቤት ማን ጥርኝ ውሃ እንደሚያቀብልን ፈጣሪያችን ይወቅ።በጎረቤታሞች መካከል በተነሳ ግጭት ግለሰቦች በደረሰባቸው ልብ ሰባሪ ሀዘን ተግፍተው የፈጸሙትን የሃይል እርምጃ እንደ ሰው ሆኖ ከተቻለም እንደራስ ሆኖ መፍረድ ሲገባ ዝም ብሎ እርምጃ የተወሰደበት ሰው ምንም ይስራ ምንም ነገር ግን አማራ ብቻ ስለሆነ የሌላውን ጉዳት ባለማየት ብቻ ሳይሆን የተፈጸመውን ወንጀል ወደ ጎሳ ፖለቲካ በማውረድ እነሱ ለሚፈልጉት አላማ ማዋልና ህብረተሰቡንም በዚያው በኩል እንዲፈስ ማራገብ ወይ የጤና ጉዳይ ካልሆነ ከወያኔ አለማነስ ነው። አማራነት እኮ ፍትሃዊነት ነበር:: አማራነት እኮ ሰውን በአርአያ ስላሴ መፈጠሩን እንጅ በጎሳ መንዝሮ ያለማየት አቅም ነበር። አማራነት እኮ የካህኑ የመልከጸዴክ ልጅነት ነበር። አማራነት እኮ በሄንኖክ ተወክሎ በብሄረ ሔዋን ማእጠንት የሚሰዋ ህዝብ መሆን ነበር። ዛሬ እንደ ኤሳው ብኩርናቸውን ያቃለሉና በመለስ ዜናዊ ጫማ ልክ ጨንግፈው የተሰፉ ሁሉ ሁለት ልጅ በሆዷ ተሸክማ ስለተገደለችው እናት ጸጸትት የሚገልጥ አንዲት ጥርኝ ቃል ከ አፋቸው ሳይወጣ ስለተቃጠለ ንብረት ግን ብዙ ብለዋል። እኔ በእንዲህ አይነት ተፈጥሮ የማውቀው ቦኮሃራምን እና አጋዚን ነበር። የኔታ እንዳሉት ይኽ ነገር ለኔ ክሽፈት ነው። ከምእራባዉያን የዜና ማሰራጫ ቋቶች በሚወጣ ፕሮፓጋንዳ የተፈለገውን ያህል ተጽእኖ ማሳደር አልተቻለም ተብሎ ቢቢሲና ሲኤን ኤን የአረብኛ ጭምብል ለብሰው በኩዋታር ከተሙና አልጀዚራ ሆነው መጡ። ከሱኒዎች እምብርት ኩዋታር በሚፈልገው የራሱ ቋንቋ የሚረጨውን ሁሉ ገና ለገና አረብኛ ነው በሚል ጆሮውን የሰጠው አረብ ሁሉ አልጀዚራን ተከትሎ ወደ ሰናኦር ዘመን ማዝገም ከጀመረ ሁለት አስርተ አመታት ሊሞላው ነው። ኢራቅ፣ ሊቢያ ሶሪያ የመን አፍጋኒስታን ካርታ ላይ አሉ ማለት አይቻልም። ቱርክ ግብጽ ባህሬን ኩዋታርና ሳውዲ አረቢያ ደግሞ ከፊት መስመር ተሰልፈው ቀናቸውን እየጠበቁ መሆኑን ለማየት አራት አይን አያስፈልግም።ከዚህ ሳይማር ጥቂት ወደ ጽንፍ የተገፉ ሰዎች የሚጽፉትን ብቻ እየተከተለ የሚሄድ ማንም ቢኖር ጤናውን ይፈትሽ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s