ከስደት ምክንያቶች አንዱ….


 

ከእሙ ጋር አልፎ አልፎ ቅዳሜ ማታ እኔ ቤት ወይም እስዋ ጋር እየተገናኘን አንድ ሁለት እንላለን ፣ ካርታ እየተጫወታለን ፣ አልያም የሃገረኛ ፊልሞች እያየን እናመሻለን ::

እሙ ጨዋታ ትችልበታለች ቁም ነገርዋም ቀልድዋም አይጠገቡም:: ጠይም መልኩዋን እና ቁንጅናዋን ስለምወደላት እና ሁሌም ሰለማደንቅላት ደስ ይላታል

አንዳንዴ እንደውም…. ታውቂያለሽ አይደል ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ቢኬድ አንችን የመሰለ ቆንጆ እንደማይገኝ እላታለሁ….

ሂድ ወገኛአሁን ዞረህ ያየህ አትመስልም?”… ትላለች እየሳቀች እና እየተሽኮረመመች

አንድ ምሽት ግን ከሃገር ለምን እና እንዴት እንደወጣች ጠየኩዋት::…

ትንሽ ወደ ሁዋላ መለስ ብላ እንደማሰብ ካለች በሁዋላ ……የመጀመርያ ባለቤቴን ሽሽት ነው…” አለችኝ

ማለት…. ….እንዴት? ብዬ ጥያቄዬን አከታተልኩት:: ያው በዝርዝር እንደታወራኝ ሰለፈለኩ

ይኁውልህ ሰውየው በእድሜ በጣም ትልቅ…. ያለተማረ….. ግን በጣም ሃብታም እና የጊዜው ሰው እንደሚባሉት ነበር:: አባታችን በልጅነታችን ስለሞተ እናታችን በጣም ተቸግራ ነበር ያሳደገችን:: የዚህ ሰውየ እኔን የማግባት ሃሳብ ሲመጣ ቤተሰባችን የታየው በሰውየው ሃብት እነሱ ሃብታም መሆን እንጂ የእኔ በእድሜ ማነስም ሆን ጉዳቴ የታየው ማንም አልነበረም::

ተጋብተን ሁለት ቀን እንኩዋን ከእኔጋ አላሳለፈም:: አምሽቶ ይመጣል ፥ ከፈለገ ያደራል ፥ ሲያሻውም ሳምንት ለስራ ነው በሎ ቆይቶ ይመጣል ማንም እሱን የመጠየቅ መብት የለውም ::

ለኔም ትንሽዬ ቡቲክ ቦሌ አካባቢ ከፍቶልኝ ስለነበር ያው እቃ ለማምጣት ወደ ዱባይም ወደ አውሮፓም መውጣት እንደምፈልግ በግድ ሰለጨቀጨኩት ይዞኝ ይሄዳል ቀን አብረን እቃ ማየት ካለብን አብረን እናያለን ማታ ግን የትም ከማንም ጋር እኔን ሆቴል አስቀምጦ ሲማግጥ ያድራል::

በዙ ጌዜ ቻልኩት በሰው አስመከርኩት በሽማግሌ አስለመንኩት እሱ ግን ገንዘብ ስላለው ማንንም አይፈራምም እኔንም ማስፈራራቱን ቀጠለ:: ሞቅ ሲለው እንደውም መሳሪያውን ያወጣና….. ”አርፈሽ ካልተቀመጥሽ በእዚህ እግርሽን ላሳጥረው እንደምችል እና ማንም እንደማይጠይቀኝ ታውቂያለሽ አይደል? ይለኝ ነበር….. አንጀቴ ቢያርም የግድ ለቤተሰቦቼ ስል መታገስ እንዳለብኝ እራሴን ለማሳመን ሞከርኩ::

የመጨረሻ ቀን ግን በስልክ ደውሎ ሻራተን ሆቴል ጋዝ ላይት ነኝነይ”… በሎኝ ስደርስ ሞቅ ብሎታል ከሰዎች ጋር ያሽካካል :: ለኔም አዘዘልኝ እኔ የማላውቅቸውንም ሰዎች ካልጠጣችሁ እያለ ይጋበዛል:: ለኔ ከእቤት መውጣቴን ብወደውም እሱን በእንዲህ አይነት ሁኔታ ማየት ግን ደስታየን አቀዝቅዞት ነበር::

ብዙም ሳይቆይ በጆሮዬ ጠጋ አለና ሚኬሌ እኮ ሞተ”… አለኝ:: ሰምቼዋለሁ ግን ስለሰከረ ስም ተሳስቶም መሰለኝ

ምን?… ብየ በድንጋጤ ጠየኩት ሚኬሌ ማለት የእሱ የቅርብ ጉዋደኛው ፣ በማንኛውም ችግር ጊዜ ከጎኑ የሚቆምለት ፣ ብዙ ውለታን የዋለለት ፣ የእኛ ትዳር እንዳይፈርስ ሁሌ የሚጥር ፣ መካሪው ፣ የልቤ ጉዋደኛ የሚለው….. ሞቶ እሱ ምንም ሳይመስለው እኔንም ጨምሮ መሸታ ቤት….. ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ ነው

መኪናዬን ጠዋት ተበድሮኝ ወደ ክፍለ ሃገር ሲሄድ ተገልብጦ ሞተእስኪ ይታይሽ አዲስ መኪናየን እኮ ነው ድምጥማጡዋን ያጠፋት”… እያለ በመኪናው መገልበጥ ይበሳጫልይሳደባል … እራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም

የልብ ጉዋደኛህ ሞት ነው የሚያሳዝንህ…? ወይስያንተ ቆርቆሮ መጎዳት ነው የሚያሳዝንህ? ሳላስበው ጮኩ

እንደ እብድ እየበረርኩ ወደ ውጭ ወጣሁ እግሬ ግን መራመድ አልቻለም:: የሰው ልጅ ህይውት እንደ ድንገት ወጥቶ መቅረት ፣ ደግ የማይበረክተበት ምድር ፣ ለተቸገረ ልቡ ሁሌ የሚራራው ፣የቤተሰብ ሃላፊነቱ ፣ የአምስት ወር ነፍሰ ጡርና በቅርቡ ያጫት ፍቅረኛ ያለችው ሚኬሌ….. መሬት ላይ ወድቄ ሆዴን በእጄ ጭብጥ አርጌ ይዤ ማልቀስ ጀመርኩ::

እየትንገዳገደ አጠገቤ ደረሰ

ምነውሌላ ግንኙነት ነበረሽ እንዴ?… እንዴህ የሚያደርግሽ…” እየተንተባተበ መርዛማ ንግግሩን ተፋው….

ይህን ስሰማ እራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም ያን ያህል ጉልበት ሁላ ከየት እንዳገኘሁ አላውቅም ብቻ በጥፍሬ ፣ በጥርሴም ቦጫጨኩት…. ሰዎች ቢይዙኝም ማቆም ግን አልቻልኩም::

አንተ ውሻ….. አተት ልክስክስ…. እኔን…? እንደወንድም በሚሳሳልህ ጉዋደኛህ እ….. እንባየ ይረግፋል…. በግድ በሰው ግልግል በታክሲ ጭነው እናቴ ቤት አደረሱኝ:: ሌሊቱን ሙሉ ሳለቅስ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነጋ:: በንጋታው የሚኬሌን ቀብር እንኩዋን መሄድ አልቻልኩም ምክንያቱም ይሄን ሰውየ ለአንድ ሰከንድ የማይበት አቅም አልነበረኝም::ምን ማድረግ እንዳለብኝ ብዙ አሰብኩ በዙ አወጣሁ አወረድኩ…. በመጨረሻም ስደት!!…. በአልተቃጠለው የጣልያን ቪዛ የእሱን አምስት ሳንቲም ሳልነካ እናቴንም እንኩዋን የት እንደሄድኩ ሳልነግር እና ሳልሰናበት ከሃገር ወጣሁ…..

እሙ ይሄን ስትነግረኝ በተመስጦ እየሰማሁዋት ሳላሰበው የእኔም እንባ እየወረደ ነበር

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s