የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ መደበኛ ስብሰባ በ 05.05.18 በኑረንበርግ ከተማ ተካሄደ


News Report by Alemayehu kidanewold

Photo by Michael Mekonnen

በየሶስት ወሩ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ መደበኛ ስብሰባውን በ 05/05/2018 በኑረንበርግ ከተማ አካሄድዋል::

 

ስብሰባው ከ ቀኑ 2pm ሰአት ብዛት ያላቸው የድርጅቱ አባላት ወቅታዊ ስለሆነው የሃገራችን ሁኔታ በሰፊው ተወያይተዋል::

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ መደበኛ ስብሰባው የሃገራችን ኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ በዴያስፖራው ልፋት በስደት የሚገኙ ኢትዮጵያን ለፍትህ ፣ ለዴሞክራሲና ለአንድነት በተለያዩ ታላላቅ መድረኮች፣ ሰላማዊ ሰልፎች ፣ ተቃውሞዎች ድምጹን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለብዙ አመታት ያሰማ ሲሆን ይህም ድካም ጥሩ ተስፋዎችን ይዞ መምጣቱን አመላክቶዋል::

 

በተለያዩ የሃገሪትዋ እስር ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች ፣ ጋዜጠኞች እና አክቲቪስቶች ከእስር ተፈተዋል::

አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የቀሩትን ብዛት ያላቸውን የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ያለ ምንም ቅደመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንዲሁም የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁን እንዲያነሳና ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲያሰፍን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ጥረቱን እነደሚቀጥል አስታውቆዋል::

አዲሱ ጠቅላይ ምንስትር ዶ/ር ኣብይ ኣህመድ በህዝብ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የመጡ ባይሆንም ለሃገራችን ህዝቦች እያደረጉ ያለውን የማቀራረብ የማስማማት እና ሃገራችን ከገባችበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች የሚታደጉዋት እንዲሆን የጀመሩት መልካም መንገድ ድርጅታችን ጊዜ ሊሰጣችው እና በሚደረገው የዴሞክራሲ ግንባታም እገዛ ማድረግ እንዳለበት ተወያይተዋል::

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s