Archives

የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪዎች ታሰሩ

የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪዎች ታሰሩ

በጎንደር ከተማ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ሰማያዊ ፓርቲ ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት በመቃወም እሁድ ጥር 25 ለማድረግ ያቀደውን ሰልፍ እያደናቀፉ ነው፡፡ የፓርቲው ሰልፍ አስተባባሪዎች ስለ ሰላማዊ ሰልፉ ለማሳወቅ ወደ ከንቲባው ጽ/ቤት በሄዱበት ወቅት ከቢሮ ቢሮ ሲያጉላሉዋቸው ከቆዩ በኋላ በፖሊስ መያዛቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ፓርቲው ላቀደው ሰልፍ ዝግጅት ወደ ጎንደር ያቀናው የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ኃላፊ ኢንጅነር ጌታነህ ባልቻ፤ እንዲሁም በሰሜን ጎንደር ዞን የፓርቲው የዞን ሰብሰቢ የሆነው አቶ አግባው ሰጠኝን በፖሊስ መያዛቸው ታውቋል፡፡ ወከባው የሚጠበቅ መሆኑን የገለጹት የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳ፤ ጎንደርና አካባቢው እንዲሁም ከዋናው ጽህፈት ቤት የሚገኙት የፓርቲው አደረጃጀቶች በወከባው ሳይደናገጡ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡