Archives

የኢህአግ ዘብ /EPPFG/ የዚህን አመት የመጨረሻ መዝጊያ ስብሰባውን አዳሄደ

 

Reported by Alemayehu Kidanewold

Photo by Michael Mekonnen

በኑረንበርግ ከተማ በ 02 /12 /2017 ከቀኑ በ 14.00 ሰአት የኢህአግ ዘብ /EPPFG/ ስብሰባ አቶ ልዑል ቀስቅስ የድርጅቱ ሊቀመንበር በንግግር ከፍተወታል::

አቶ ልዑል በአመቱ የተሰሩትን ጠቅላላ የሰራ ዝርዝር እና በህወሃት መንግስት የመብትና ነጻነት ረገጣ እንዲሁም ሰላም ማጣት የሚሰደደውን ህብረተሰብ በተቻለ መጠን በሰው ሃገር እንግልት እና ችግር እንዳይገጥመው ድርጅቱ ሃልፊነቱን በተጉዋዳኝ እየተወጣና ወደፉት በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል::

አቶ ልዑል አስረግጠውም እንደተናገሩት ወያኔን ለማስወገድ ስንታገል ግን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ልንተባበር እንደማንችልና ከማንኛውም ሃገር ጋር ሃገራችንን ለመሸጥ እና ወደባሰ ብጥብጥ እንደትገባ የማድረግ የሞራል በቃት እንደሌለን አሰረደተዋል::

የኢትዮጵያ ወዳጆች መስለው የራሳቸውን አጀንዳ አራምደው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከጥንትም ጀምሮ ቢሞከርም እስካሁን በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ታፍራና ተከብራ የኖረችውን ሃገር በግልጽ እንደምናያቸው ሰዎች ለስልጣን ጥማትና ለፍርፋሪ ገንዘብ ብለን በምንም መንገድ ድርድር ልናደርግ እንደማንሞክር በስብሰባው ተገልጾዋል::

የህወሃት መንግስት በየጊዜው ቆዳውን እየቀያየረ ዘርን ከዘር ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት የራሱን የመንደርተኝነትን አስተሳሰብ በህዝቡ ላይ በመርጨት እድሜውን ያራዘመ ቢሆንም ህብረተሰቡ እና ድርጅታችን ይህንን በንቃት በመከታተል ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተገልጾዋል::

በሌላው አጀንዳ በአሁኑ ሰአት በሃገራችን ስላለው ሁኔት የብሄር ግጭት በመንግስት የተወጠነ እና የተሰራ ነው” Grahm P. በጻፉት ጥናታዊ ጽሁፍ በመነሳት አቶ ቢክሰኝ ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰተውበታል::

ሰብሰባውንም የባየር ሊቀመንበር አቶ ቢክሰኝ ሃይለ ልኡል ፣ የቩርዝቡርግና አካባቢው ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ ኪዳነወልድ እና አቶ ዮሃንስ ትካኤር ጌትነት መርተውታል:: ስብሰባውም 16.00 ሰአት ላይ ተጠናቁዋል::