Archives

የግንቦት 20 በዓል 23ኛዓመትበአዲስአበባስታዲየም ሊያከብር ነው

news

ግንቦት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደርመንግስየወደቀበት 23ኛ ዓመት የግንቦት 20 በዓልገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማክበር መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

ኢህአዴግ የዘንድሮውን የግንቦት20 በአልለየትየሚያደርገውሕዝቡበተፈጠረውልማትሙሉበሙሉተጠቃሚበመሆኑነውብሎአል፡፡

ኢህአዴግመራሹመንግስትህዝቡንበቀንሶስትጊዜእንደሚያበላውቃልየገባለትቢሆንም፣ የህዝቡ ኑሮእጅግአሽቆልቁሎእንደሚገኝ፣  በአንጻሩጥቂትየሥርዓቱሹማምንትበሙስናናብልሹ አሠራርከገቢያቸውበላይሐብትአፍርተውታግለንለታልየሚሉትንሕዝብመልሰውፍዳየሚያሳዩበትአፋኝሥርዓት እየተጠናከረመምጣቱን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንደሚናገሩ ዘጋቢያችን ገልጿል።

ስርአቱበተቆጣጠራቸውየሕዝብሚዲያዎችእናየመንግስትንብረቶችያለክልካይሲጠቀምበትየሚታይሲሆንበአንጻሩተቃዋሚዎችሰልፍለማካሄድእንኩዋንያልቻሉበት፣በሕዝብመገናኛብዙሃንከፍለው  ማስታወቂያማስነገርያልቻሉበትየፖለቲካስነምህዳርመፈጠሩአንዱየግንቦት 20 ፍሬመሆኑን  አስተያየትሰጪዎችአስረድተዋል፡፡

ኢህአዴግ ለበአሉ ድምቀት ሲል የአስተዳደሩወረዳዎችናየቀድሞ ቀበሌሠራተኞችናካድሬዎችቤትለቤትበመሄድሕዝቡበነቂስእንዲወጣጥብቅማሳሰቢያ መስጠታቸውን አዲስ አበባዋዘጋያቢችንያነጋገረቻቸውነዋሪዎችአረጋግጠውላታል።

ካድሬዎቹበየቤቱበመሄድበሰልፉላይቢያንስከአንድቤትአንድሰውመገኘትእንዳለበትማሳሰቢያከመስጠትጀምሮየሚገኘውንሰውስምእናስልክቁጥርስጡንእያሉሲመዘግቡታይተዋል፡፡

በተጨማሪምለሰልፉ 50 ብር አበልና ሰርቪስመኪናመዘጋጀቱንበመግለጽነዋሪውንለማግባባትምጥረትእያደረጉመሆናቸውንለማወቅተችሎአል፡፡

ትናንት የአዲስአበባመስተዳደርባስተላለፈውትእዛዝመሰረት ደግሞ   የከተማውሁሉምየመንግስትሰራተኞች  ከሰዓትጀምሮየመንግስትስራዘግተውወደኤግዚቢሽንማዕከልእንዲሄዱ ተደርጓል፡፡

ማንኛውምሰራተኛመስሪያቤትውስጥእንዳይቀርበየኃላፊዎችጥብቅመልእክትየተላለፈለት ሲሆን፣  ከሰዓትጀምሮሰራተኛውየመንግስትስራዘግቶበከተማመስተዳድሩበኩልለከተማአንበሳአውቶቡስበተላለፈውመልእክትመሰረትሰራተኛው ወደ ማእከሉ ተጉዞ  የግንቦትሃያየትግልታሪክፎቶዎችንናዶክመንተሪዎችንእንዲያይተደርጓል።

ከቦታውማንምሰውእንዳይቀርየስም ቁጥጥር ይደረጋል በመባሉ ሰራተኛው ስራ ዘግቶ ተገኝቷል። ኢህአዴግ በአዲስ አበባ እየገጠመው የመጣውን ተቃውሞና ተቃዋሚዎች በቅርቡ ያካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ አስደንግጦታል የምትለው ዘጋቢያችን፣ ምናልባትም ህዝቡን አስገድዶ በማስወጣት አሁንም ድጋፍ እንዳለው ለዲፕሎማቲክ ኮሚኒቲው ለማሳየትና ለመጪው ምርጫ ለመዘጋጀት መሆኑን ገልጻለች።

የግንቦት20 በአል ዛሬ በደብረብርሃን ህዝቡ በሰልፍ ወጥቶ እንዲያከብር የተደረገ ሲሆን፣ ምንም የፖለቲካ እውቀቱ የሌላቸው የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳይቀር ተሰልፈው እንዲያከብሩ ተደርጓል። የኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡን እያስገደዱ ሰልፍ እንዲወጣ ማድረጋቸውን የስፍራው ወኪላችን ገልጿል።

ነገ በአዳማ በሚካሄደው ሰልፍ ላይም ካድሬዎቹ ህዝቡ በስፋት እንዲወጣ እየቀሰቀሱ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ ግንቦት20ን በተመለከተ የተለያዩ ሰዎች አስተያየቶችን በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች እያሰፈሩ ነው። ሃብታሙ ዘውዱ ” ግንቦት20 ግልጹ ደርግ በድብቁ ደርግ” የሚል አስተያየት ሲሰጥ፣ አቤ ቶክቾው በበኩሉ ” ኢህአዴግከዚህበፊትደርግበእርሷእናበሌሎችላይሲያደርግየነበረውንአንድበአንድ፤ ዛሬበተቃዋሚዎች፣በጋዜጠኞችእናበነጻሃሳቢዎችላይእየፈጸመችውነው።ልዩነቱደርግአታድርጉብሎቀድሞያስጠነቅቅነበር፤ኢህአዴግደግሞአድርጉብላታሳስትናሲያደርጉጉድታደርጋለች። ዛሬምበእስርቤቶቻችንእነቀሽገበሩአሉዛሬምበየእስርቤቱእነአሞራውታስረዋል።የግንቦትሃያ ”ሰማህታት” የተሰዉትደርግንደምስሶደርግንለመቅዳትከሆነየበሃይሌአባት፤ ”ምንትሸጣለህትንባሆትርፍህምንድነውኡሁኡሁ” ያሉትነገርነውየተከሰተብን!” ብሎአል።

አገኘሁ አሰግድ ደግሞ ” አሁንአሁንስ “እንደጀመርንእንጨርሰዋለን!” ሲሉሕዝቡንእየመሰለኝነው!›› ሲልአቤጉበኛንአስታወሰኝ፤አቤጉበኛብዙጊዜሲጽፍ ‹‹ሰፊውየኢትዮጵያህዝብ›› ማለትያበዛል፤እናምአንዴ ‹‹ሰፊውህዝብ›› ማለትምንማለትነውተብሎሲጠየቅአቤእንዲህብሎመለሰአሉ፤ ‹‹ሰፊውህዝብማለትማብትገድለውብትገድለውየማያልቅማለትነው፡፡›› ብሎአል።

ወይኔ ሃገሬ የተባለው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ” ግንቦት20 ኢትዮጵያን ለመበታተን በወያኔ መራሹ መንግስት አማካይነት የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት የተረገመ ቀን ነው” ሲል፣ ነጻነት ይበልጣል ደግሞ ” የአንድ ቀን ስልጣን ቢኖረኝ የግንቦት 20 እለት ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አድርግ ነበር” ብሎአል።

የገዢው ፓርቲ ደጋፊ የሆነው ሳባዊ ደሳለኝ ደግሞ ” ነገ የቅድስቷ አገሬ የኢትዮጵያ ልደት ቀኗ ነው”  በማለት እለቱን አሞካሽቷል።

ከዚሁ ዜና ሳንወጣ ጠ/ሚ ሃይለማርያም  ደሳለኝ ግንቦት20 የብሄር የመድብና የግለሰብ መብቶችን በማረጋገጥ በኩል አስተማማኝ መሰረት እንዲኖረው አድርጓል ብለዋል።

“የድሮውንቁስልእያነሱመነጠልንየሚቀሰቅሱናየድሮውአስተዳደርበድጋሚስልጣንላይእንዲወጣየሚሹአካላትቢኖሩምየብሄርብሄረሰቦችአንድነትናፍቅርግንአሁንምደምቋል” ማለታቸውን የገዢው ፓርቲ ልሳን ፋና ዘግቧል።

“በመድብለፓርቲስርዓቱየህግየበላይነትንየሚፈታተኑየፖለቲካፓርቲዎችንአካሄድማስተካከልያስፈልጋል” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም አክለዋል። የፓርቲዎችን አካሄድ በምን መንገድ እንደሚያካሂዱት የገለጹት ነገር የለም።