/ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ/
ዞን ዘጠኝ የአራማጆች እና ጦማሪዎች ኢ-መደበኛ ቡድን ነው፡፡ ቡድኑ በአብዛኛው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ
በጦማሩ አስተያየቶችንና ትንታኔዎችን በማስፈር እና በየሦስት ወሩ የበይነመረብ ዘመቻ በማካሄድ
የአራማጅነት ሥራ ይሠራል፡፡ ከተመሠረተ ጀምሮ በአንድ ዓመት ውስጥ ሦስት ዘመቻዎችን (በሕገ
መንግሥቱ ይከበር፣ የሐሳብ ነጻነት ይከበር፣ እና የሰላማዊ ሰልፍ ይከበር በሚል) ያካሄደ ሲሆን ከ150
በላይ ጽሑፎችንም በጦማሩ በኩል አስተናግዷል፡፡
ከነዚህ ጦማሮች መካከል አብዛኛዎቹን በዚህ ጥራዝ ውስጥ ያዘጋጀናቸው ሲሆን፣ በወጡበት ቅደም
ተከተል ከማዘጋጀት ይልቅ በየርእሰ ጉዳዩ በማሰባሰብ አንባቢ በመረጠው ርዕስ ላይ አትኩሮ እንዲያነብ
በማድረግ አሰናድተነዋል፡፡ ይህንን በምናደርግበት ሰዓት የዞን ዘጠኝ አባላት የጻፉትን በሙሉ ስማቸውን
ሳንጠቅስ ያስተናገድን ቢሆንም፣ ከሌሎች ሰዎች ተልከውልን በጦማራችን ያስተናገድናቸውን ጽሑፎች
ጸሐፊዎች ግን ገልፀናል፡፡
ጽሑፎቹ በተለያዩ ጊዜ የተጻፉ እንደመሆናቸውና የተጻፉበት ጊዜንም የሚያንፀባርቁ በመሆናቸው ብሎም
ጦማሩ ላይ የሰፈሩበትን መልክ ሳንቀይር የሰበሰብናቸው በመሆኑ ያለፈባቸው ነገሮች ሊያጋጥሙ
ይችላሉ፤ በተጨማሪም ጥቃቅን የአርትኦት እንከኖች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አንባቢዎች፣ እነዚህን ክፍተቶች
እየሞሉ እንዲያነቡ ከይቅርታጋ እንጠይቃለን፡፡
ጽሑፎቹን ሰብስበን በኤሌክትሮኒክ ኮፒ ማስቀመጥ ያስፈለገን፣ ለወደፊቱ ማነፃፀሪያ ይሆናሉ ብለን
በማመናችን መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
መልካም ንባብ!
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ከታች ያለውን Pdf ይጫኑ
Zone9 – Compiled Book of Year One
Email: zone9ners@gmail.com
Twitter: @zone9ners